2017-02-11ዛጎል ዜና፡- የኦሮሞ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ኦነግ ሃይሉ ተበታትኖ፣ አመራሩ ተከፋፍሎ፣ ደጋፊዎቹ ግራ ተጋብተው ያለ ድርጅት ነው። ከሁሉም በላይ ደጋፊዎችን ተስፋ ያስቆረጠው ኤርትራ ገብቷል የተባለውን ሰራዊት በሚመሩት ክፍሎች መካከል እንኳን ስምምነት አለመኖሩ ነው። ኤርትራ በረሃ አሉ የሚባሉት እነዚሁ ክፍሎች መከፋፈላቸው እንጂ የመከፋፈላቸው ዋና ምክንያትና እና መነሻው ግልጽ ሆኖም አያውቅም። በዚህና በሌሎች ሰፊ መነሻዎች ይመስላል አሁን ወደ “መፍትሄ” እየተጠጉ መሆኑ እየተሰማ ነው።

ኤርትራ ያለውን ሃይል ከሚመሩት አቶ ዳውድ በስተቀር አሁን አሁን የተቀሩት ” ትግሉን ወደ አገር ቤት” እያሉ ነው። አቶ ዳውድ ኢብሳንና በስራቸው የዋቀሩት ‘አካባቢ ተኮር ነው’ የሚባለውን አመራር በጥቅሉ ” የኢሳያስ ኦህዴድ ” እያሉዋቸው ነው። ነገሩን ዳር ሆነው የሚመለከቱ አካላትም ቢሆኑ አስመራ ያለው የኦነግ ክንፍ ምንም ሳይፈይድ አርጅቷል። ” እንኳን ሌላውን ነጻ ሊያወጣ ለራሱም መውጪያ የሌለው ነው” ሲሉ ወዶ ገብቶ የተዘጋበት ሲሉ ይጠሩታል። የኢሳያስ መደራደሪያ መሳሪያ አድርገው ይስሉታል። አቶ ዳውድ ይለፍ ያልጻፉለት ማንኛውም የኦነግ አባል ከኤርትራ ንቅንቅ ማለት አለምቻሉ ደግሞ ትግሉን ” ግዞት” አድርጎታል። አቶ ዳውድ ግን ይህንን አይቀበሉም። ይልቁኑም ቀሬውችን አደራጅተን አገር ቤት ተነስቶ የነበረውን ትግል እንደመሩት ያስረዳሉ።
የህወሃት ኦህዴድና የኢሳያስ ኦህዴድ
የህወሃት ኦህዴድ አሁን ጨፌ ያለውና ምርኮኛ ወታደሮችን፣ ኦሮሚኛ ተናጋሪዎችን፣ ኦነግ የነበሩና የተከረበቱትን አሰባስቦ የተዋቀረ፣ እየቆየ ሲሄድ ሁሉም ዓይነት አቋም ያላቸው የተሰገሰጉበት ድርጅት ነው። አሁን በግምገማ እነደተረጋገጠው ኦህዴድ ሲሰፋና የተለያዩ ዓመለካከት ያላቸው አመራር ላይ ሲቆዩ ድርጀቱ በመንፈስ ሌላ ሆነ።
የኢሳያስ ኦህዴድ ኤርትራ ተቀምጦ ወታደራዊ ልምምድ ሲያደርግ በቪዲዮ የሚታይ፣ ሃኪም በረሃ ብቻ ያዘዘለት፣ ወዴትም መላወስ የማይችል። ዓላማው መደራደሪያ የሆነ እንደሆነ ራሳቸው አፍቃሪ ኦነጎች የሚስማሙበት እውነት ነው። የአንድ ወጣት ዕድሜ ስልጠና ላይ የኖረ ሃይል እንደሆነ የሚጠቁሙት ክፍሎች፣ ይህ ሃይል እንደ ከሸፈ ቀለሃ ይቆጥሩታል። dawde
የሁለቱም ዓይነት ኦህዴዶች አስፈላጊነት ለስልጣን ማስጠበቂያና ስልጣንን ተከትሎ ለሚገኘው የኢኮኖሚ የበላይነት ነው። የዚህ መረጃ ምንጭ እንደሚሉት ” ህወሃት ኢሳያስ ላይ ነቀቶባቸው፣ ውይም በደንብ እስኪደራጅ ጠብቆ ሲሸኛቸው ያሰባስቡት የኦነግ ሃይልም ሆነ አገር ቤት በሹም ሽርና በግምገማ እየተወዛወዘ ያለው ኦህዴድ ተፈላጊነታቸው በሌሎች ስም ራስን ከፍ ለማድረግ ብቻ ነው”
አዲሱ መንገድ
ኦነግ አራትና አምስት ቦታ ተሸንሽኖ አስርት ዓመታቶችን ኖሯል። ዛጎል ያነጋገራቸው እንደሚሉት ኦነግ የተበታተነው ሆን ተብሎ በደባና ራሳቸውን ለግዞት አሳልፈው በሰጡ አመራሮች ልልነት ነው። ለዚህም ግንባር ቀደሙ ተዋናይ ኢሳያስና የእሳቸው ወኪሎች ናቸው። ይህን እውነት አሁን ቢዘገይም ወደ መግባባት ላይ እያዳረሰ ነው።
እናም አዲሱ መንገድ ይህን የተበተነውን ሃይል ማሰባሰብ ነው። ከዚህ ቀደም የተለያዩ ንግግሮች ተካሂደዋል። አሁንም በመካሄድ ላይ ነው። የሎንዶን የዛጎል የመረጃ ሰው እንዳሉት የገላሳ ዲልቦና የአባ ነጋ ጃራ ኦነግ ለመዋሃድ እየተነጋገሩ ነው።
የመዋሃዱ ውና ዓላማ ኤርትራ ተቀምጦ ” ላም አላኝ በሰማይ” የሚለውን የዳውድ ኢብሳን ኦነግ ተሰፋ ቢስ ትግልና የትግል ስልት ወደ ጎን በማለት ሁሉም ትግሉን ወደ አገር ቤት እንዲመለስ ለማስቻል ነው። ጉዳዩ ሲጠናቀቅ በይፋ መግለጫ እንደሚሰጡ የተናገሩት የመረጃው ሰው ” አገር ቤት በየአቅጣጫው ሃይል አለ። ችግሩ ያለው የአመራሩ መበታተንና ወጥ ትዕዛዝ አለመኖሩ ነው። ይህ ከተስተካከለና የተበተነው ኦነግ ወደ ቀድሞ ህብረቱ ከተመለሰ ሁሉም ቀላል ነው” ሲሉ ተስፋቸውን ይገለጻሉ።
ሌሎች ብሄረሰቦችን የማካተት ጉዳይስ በሚል ለተጠየቁት ” የኢትዮጵያ ችግር እጅግ በቀላሉ የሚፈታ ነው። የፖለቲካ አመራሮቹ ቀና ቢሆኑና የወደፊቱን ችግር ባግባቡ ቢያሰሉት አዲስ ኢትዮጵያን ፈጥሮ መኖር ይቻላል። ግን አይፈለግም” በለዋል። የኦሮሞ ህዝብ የተዋለደ፣ በርካታ ብሄሮች የተካተቱበት መሆኑንን ያስታወቁት እኚሁ ሰው ” የቀድሞ ጉዟችን ትምህርት ሆኖናል” ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።
አቶ ዳውድ ኢብሳን መንካት ለምን አስፈለገ? ለተባሉት ” አንነካውም። ግን ፋይዳ የሌለው ጉዞ እንደሚጓዝ እኛ ህብረት ስንፈጥር ራሱ ይረዳዋል። ከቻለ ከግዞት ወጥቶ ትግሉን ይቀላቀላል። አለያም እዛው … ” ሲሉ ተጨማሪ ማብራሪያ እንደማያስፈለግ አስታውቀዋል።
እሳቸው ይህን የበሉ እንጂ ኦነግ ካሁን በሁዋላ እንደገና ታድሶ፣ አንድ ሆኖ፣ ህብረት ፈጥሮ፣ አንድ አመራር አቁሞ በአገር ቤት የሚካሄደውን ትግል ለመምራት አስቸጋሪ እንደሚሆን፣ በዚህም ላይ እነ ጁሃር መሐመድ የሚያካሂዱት ጽንፍ የወጣ ፖለቲካና ” ንጹህ ኦሮሞ” በማለት የደም ምርመራ ለማድረግ የተዘጋጀ አካሄድ ኦነግ በቀላሉ እምነት እንደማያስገኝለት የሚናገሩ አሉ። በዚህ አይነቱ አካሄድ ቁጥራቸው በሚሊዮን የሚቆጠር የተዋለዱ ኦሮሞዎችም አይስማሙም።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

ፎቶ – ገላሳ ዲልቦ በወጣትነት

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *