ሌሊሳ የኦሎምፒክ ጀግና፣ ኢትዮጳያዊ፣ ለአክራሪነት የማይመች፣ በማንም ያልተወሰደ፣ ያመነበትን ያደረገ…. ልበ ሙሉ አገር ወዳድ እንደሆነ በተደጋጋሚ የተነገረለት። አጀንዳውና እምነቱ የሰብአዊ መብት መከበር የሆነ… እንደ ረጅም እርቀት ሯጭነቱ አርቆ የሚያስብ የሚሉት፣ ስሜቱንና እምነቱን በትክክለኛው ቦታ የገለጸ ሰላማዊ ታጋይ ተብሎ የተሞካሸ፣ በሪዮ ኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ፣ በወገኖቹ ደግሞ ይክብር የህሊና ዙፋን የተሸለመ፤ ለሌሎች ምሳሌነቱ የሚያበራ… ቃላት ተመርጠው ለክብሩ የዋሉለት… ዓለም ያነገሰው እሱ ግን ሁሉን ትቶ ለወገኖቹ ድምጽ የሆነ፣ የዘመኑ የጎድሳ በሽታ ያላለፈበት….. ሁሉም ” ይህን ልብህን አይቀይረው” እያሉ ምርቃትና ጸሎት የሚያደርጉለት፣ ከሃብት ስፋት የህሊና ልዕልና የባስበት … ቤተሰቦቹን በስደት ምድር ተገናኘ፣ አገኛቸው!! ልጆቹን ሳመ፣ የልጆቹን እናት … ደስ ብሎኛል አለ። እንኳን ደስ አለህ!!

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *