የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት ስድስት ወራት ከ2 ነጥብ 3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ አገኘ። የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ባንኩ የውጭ ምንዛሬውን ያገኘው በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትየጵያውያን ወደ ሀገር ውስጥ ከላኩትና ከወጪ ንግድ ነው።

በዚህም መሰረት 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላሩ ከውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ውስጥ የላኩት ሲሆን፥ ቀሪው ገንዘብ ደግሞ ከወጪ ንግድ የተገኘ ነው። ባንኩ በየአመቱ የውጭ ምንዛሬን ለማሳደግ የተለያዩ ማበረታቻዎችን መዘርጋቱን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፥ ከእነዚህም ውስጥ ያለዋስትና ብድር እንዲያገኙ ማድረግ እና በአነስተኛ የወለድ መጠን ብድር ማመቻቸቱን ለአብነት አንስተዋል።

Related stories   Let’s See the Proof of “Ethnic Cleansing” in Ethiopia, New York Times!

በወጪ ንግድ የተሰማሩ ባለሃብቶች የአገልግሎት ክፍያ (ሰርቪስ ቻርጅ) እንዳይከፍሉ መደረጉም ሌላኛው ማበረታቻ መሆኑን ነው የጠቆሙት። በየአመቱ ከፍተኛ የውጨ ምነዛሬ ላስመዘገቡ ባለሃብቶች እና ድርጅቶች እውቅና እና ሽልማት መሰጠቱም ባለሃብቶች በዘርፉ የበለጠ ተሳታፊ እንዲሆኑ እያደረገ መምጣቱን ገልፀዋል።

በዚህ አመት በአጠቃላይ ከ5 ነጥብ 5 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ነው የታቀደው። ቀሪ ስድስት ወራትም በተለይም የግብርና ምረቶች የሚሰበሰቡበት እና ወደ ውጭ የሚላኩበት በመሆኑ እቅዱን ለማሳካት ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል አቶ በቃሉ። ባንኩ በወጪ ንግድ ዘርፍ ከ1 ሚሊየን እስከ 100 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ የውጭ ምንዛሬ ያስመዘገቡ 127 ድርጅቶች እና ባለሃብቶችን ዛሬ ሽልማት አበርክቶላቸዋል። ድርጅቶቹ እና ባለሃብቶቹ በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በማምረቻ፣ በአበባ እና በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ናቸው።

Related stories   “ወያኔ እየሠራው ባለው ግፍና በደል ትግራይ ከፍላ የማትጨርሰው ዕዳ እየተቆለለባት ነው!”ሲሉ ሰምቼ…

ፋና ብሮድ ካስቲንግ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *