“Our true nationality is mankind.”H.G.

የገቢዎችና ጉምሩክ የቀድሞ ከፍተኛ ኃላፊዎችና ታዋቂ ነጋዴዎች ተከላከሉ ተባሉ

  • አርሶ አደሯ ተጠርጣሪ በነፃ ተሰናበቱ

የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተርና ምክትል ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ፣ ስድስት ከፍተኛ ኃላፊዎችና ታዋቂ ነጋዴዎች በመዝገብ ቁጥር 141356 በቀረቡባቸው ከባድ የሙስና ወንጀል ክሶች እንዲከላከሉ፣ ሰኞ የካቲት 13 ቀን 2009 ዓ.ም. የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት ብይን ሰጠ፡፡

የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በጥቅምት ወር 2006 ዓ.ም. የመሠረተውን ክስ ሲመረምር ከርሞ በመዝገቡ ላይ ብይን ለመስጠት ተደጋጋሚ ቀጠሮዎችን የሰጠ ቢሆንም፣ የካቲት 13 ቀን 2009 ዓ.ም. ብይን ሲሰጥ ነዋሪነታቸው በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን በአዳሚ ቱሉ የሆኑት የ59 ዓመቷ አርሶ አደር ወይዘሮ ሽቱ ነጋሽ ኢዶ፣ ከተከሰሱበት የሙስና ወንጀል መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ አስታውቋል፡፡

ወይዘሮ ሽቱ የተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን አዳማ ቅርንጫፍ የፍተሻ ክፍል ኃላፊ የነበሩት የእንጀራ ልጃቸው አቶ ያለው ቡላ፣ በሕገወጥ መንገድ ያገኙትን ንብረትና ገንዘብ በመሰወር፣ በሥራ ላይ በማዋልና ሕጋዊ አስመስለው በማዋል ተጠርጥረው ነበር፡፡ ነገር ግን ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ የሚያስረዱለት ምስክሮችም ሆነ የሰነድ ማረጋገጫ ሊያቀርብባቸው ባለመቻሉ በነፃ ተሰናብተዋል፡፡ ወይዘሮ ሽቱ በተጠረጠሩበት ወንጀል ከሦስት ዓመታት በላይ በማረሚያ ቤት ቆይተዋል፡፡

Related stories   የኦነግ ከፍተኛ አመራር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ

ሌሎቹ ተከሳሾች አቶ መላኩ ፈንታ፣ አቶ ገብረ ዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ፣ አቶ አሞኘ ታገለ፣ አቶ ተመስገን ጉላል፣ አቶ እሸቱ ግረፍ፣ አቶ ያለው ቡላ (ሁሉም የባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት ከፍተኛ ኃላፊዎች የነበሩ ናቸው)፣ ታዋቂ ነጋዴዎቹ ደግሞ አቶ ነጋ ገብረ እግዚአብሔር፣ አቶ ከተማ ከበደ፣ አቶ ጌቱ ገለቴ (በሌሉበት) እና አቶ ገብረ ሥላሴ ገብሬ ናቸው፡፡

Related stories   በሃሰተኛ ሰነድ ሾፌር ሆኖ የጫነውን ከ6 ሚሊዮን በር በላይ የምያወጣ ቡና የዘረፈው ዕምነት አጉዳይ ተፈረደበት

ሁሉም ተከሳሾች ተከላከሉ ሲባሉ ከቀረቡባቸው ስድስት ክሶች መካከል አቶ መላኩ ፈንታ በአንደኛ ክስ ብቻ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 411 (1ሐ) መሠረት እንዲከላከሉ ተብለዋል፡፡ ሌሎቹ ተከሳሾች ዓቃቤ ሕግ ያቀረበባቸውን የሰውና የሰነድ ምስክሮች ማስተባበል ባለመቻላቸው፣ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 411 (1ሐ) እና (2) መሠረት እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ ብይኑን የሰጠው በሁሉም ተከሳሾች ላይ ነው፡፡ ኃላፊዎቹ ከነጋዴዎችና አስመጪዎች ጋር በመመሳጠር ከጂቡቲ ወደብ ወደ ሚሌ የተጓጓዙ የንግድ ዕቃዎች፣ ከሚሌ እስከ መዳረሻ የፍተሻ ጣቢያ ድረስ ሳይፈተሹ እንዲያልፉ መመርያ መስጠታቸውን ዓቃቤ ሕግ በምስክሮቹ ማስረዳት መቻሉን አስታውቋል፡፡

በሁለተኛ ክስ አቶ አሞኘና አቶ ተመስገን (የባለሥልጣኑ ኃላፊዎች የነበሩ)፣ አንድ ነጋዴ የሕፃናት ጫማዎች ለማስመጣት ‹ዲክለር› አስደርጎ የአዋቂ ጫማ ማስመጣቱ በፈታሾች የታወቀ ቢሆንም፣ ተከሳሾቹ ከአስመጪዎቹ ጋር በጥቅም በመመሳጠር ያለምንም ዕርምጃ እንዲያልፍ በማድረግ ሥልጣናቸውን አላግባብ መገልገላቸውን ተጠቅመዋል በማለት ዓቃቤ ሕግ ክስ አቅርቦባቸው ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ሲመረምር ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ ሊያስረዳባቸው አለመቻሉን በማረጋገጡ፣ መከላከል ሳያስፈልጋቸው ሁለቱም በነፃ እንዲሰናበቱ ብይን ሰጥቷል፡፡

Related stories   የኦነግ ከፍተኛ አመራር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ

በሦስተኛ ክስ አቶ ያለው ቡላ 10,000 ብር ጉቦ መቀበላቸው ስለተመሰከረባቸው፣ የተጠቀሰባቸው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 411(1ሐ) እና (2) ወደ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 411(1ሐ) ተቀይሮ እንዲከላከሉ ተብለዋል፡፡ ሌሎቹ ተከሳሾች የተመሠረተባቸውን ክስ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 411(1ሐ) እና (2) መሠረት እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቷል፡፡ የመከላከያ ዝርዝራቸውንም የካቲት 20 ቀን 2009 ዓ.ም. እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡

ሪፖርተር – ታምሩ ጽጌ

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0