ኢትዮጵያ የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ለማምጠቅ ለአለም አቀፉ የሳተላይት ድርጅት ጥያቄ አቅርባ ምላሽ እየጠበቀች ነው።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲም በኮሙዩኒኬሽን ማምጠቅ ዙሪያ የማማከር አግልሎት ከሚሰጠው ዩ ቴል ሳት ከተባለው የፈረንሳይ ኩባንያ ጋር ስምምነት በ13 ሚሊየን ዩሮ ስምምነት ተፈራርሟል። በስምምነቱ መሰረት ዩ ቴል ሳት የቅድመ እና ድህረ ሳተላይት ማምጠቅ ጉዳዮች ላይ የማማከር አገልግሎት ይሰጣል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መሃመድ እድሪስ እንደተናገሩት፥ ኢትዮጵያ ለማምጠቅ ያሰበቺው ሳተላይት ለቴሌኮሙዩኒኬሽን እና ለቴሌቪዥን ስርጭት አገልግሎት መጠቀም የሚያስችል ነው፡፡

Related stories   በኢትዮጵያ ከፍተኛ መረጃ የመሸከም አቅም ያላቸው ማዕከላት ሊገነቡ ነው

ይህ ፕሮጀክትም አሁን ላይ ሀገሪቱን ለሳተላይት ኪራይ እያስወጣት ያለውን እስከ 1 ቢሊየን ብርን ያስቀርላታል ነው የተባለው፡፡ ከዚህም ባሻገር ደህንነቱ የተጠበቀ የመረጃ ቅብብሎሽ እንዲኖር ያስችላልም ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፡፡

ሳተላይቱን ለማምጠቅ ከሁለት ዓመት በፊት ሂደቱ የተጀመረ ሲሆን፥ ዛሬ የተፈረመው ውልም ለፕሮጀክቱ እውን መሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል፡፡ ይህን ለመተግበር ግን ከዓለም አቀፉ የተሌኮሙዩኒኬሽን ማህበር ፈቀድ ማግኘት ይጠበቅባታል፡፡

Related stories   አትሌት ለተሰንበት ግደይ በቶክዮ ኦሎምፒክ ትሳተፉለች!!

ይህም ማለት ሀገሪቱ ለህብረቱ ፍሪኩዌንሲ እና የሳተላይት ማስቀመጫ ቦታ እንዲሰጣት የሚያስችል ጥያቄን ከአንድ ዓመት በፊት አቅርባለች፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን የህግ ማዕቀፎች የሚያስፈልጉ ሲሆን፥ ህብረቱም ጥያቄ ያቀረቡለትን ሀገራት ጥያቄ ካላችሁ ብሎ የተወሰነ ጊዜ እየጠበቀ ነው።

ከዚህ አንጻርም ህብረቱ የሚስፈልጉትን ጉዳዮች በማገናዘብ ፈቃድ የሚሰጣት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ፈቃዱን ካገኘች በኋላ ሳተላይቱን ከሚያመጥቅ ድርጅ ጋር በመስማማት ሳተላይቱን የምታመጥቅ ይሆናልም ብለዋል አቶ መሃመድ፡፡

Related stories   ዝነኛው የቴሌቭዥን መርሀ ግብር መሪ ላሪ ኪንግ አረፈ

ይህ እውን ከሆነም ሃገሪቱ የምትከፍለውን ኪራይ ከማስቀረት ባሻገር ለሌሎች ሀገራት እና ድርጅቶች የምታከራይ ይሆናል ብለዋል፡፡ በአፍሪካ ግብጽ እና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ አራት ሃገራት የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት አላቸው።

 (ኤፍ ቢ ሲ)

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *