ኢትዮጵያ ሀገራችን ታዳጊ ሀገሮችን በተለይ አፍሪካን እንደ ቅርጫ የተቀራመቱት ቅኝ ገዥዎችና ወራሪዎችን ጥቃት መክታ የግዛት አንድነቷንና ሉዓላዊነቷን መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ለማንም ባዕዳን ወራሪ ኃይል ሳትደፈርና ሳትገዛ የኖረች የማንነታችንና የክብራችን መግለጫ ናት። ዮሐንስ በመተማ፣ ቴዎድሮስ በመቅደላ፣ ምኒልክ በአድዋ እየተባለ የሚነገርላቸው፣ የሚጻፍላቸው፡ የሚዘፈንላቸው ነገስታቶች በሀገር አንድነትና በኢትዮጵያዊነት ማንነት ወራሪን ያሳፈሩና ዓለምን ያስደነቁ ኢትዮጵያዊነት የክብርና የአንድነት ተምሳሌትነቷን ያስፃፉና ያስተረኩ እስከዛሬም ሆነ ወደፊት ይህ ማንነታቸውን ታሪክ የሚያወሳላቸው ነገስታት ናቸው።

በነዚህ ነገስታቶች የአገዛዝ ዘመን የሀገር አንድነትንና የግዛት ነፃነትን በማስከበር ደረጃ በየጊዜው ስማቸው የሚጠራ ጀግኖችን ሀገራችን አስመዝግባለች። ዶጋሌ ሲነሳ አሉላ አባ ነጋ፡ መድፍ ሲነሳ ፊታውራሪ ገበየሁና ባልቻ አባ ነፍሶ፡ ስቅላት ሲታወስ በላይ ዘለቀ፡ ብልህነት ሲጠቀስ እቴጌ ጣይቱ፣ ሞኝነት ሲዜም ደጃዝማች አያሌው ብሩ፣ እምነት ለነፃነት ሲነሣ አቡነ ጴጥሮስ መሰል ጊዜ ያበቀላቸው ጀግኖች በዝማሬው፣ በተረቱ፣፡ በግጥሙ፣ በተውኔቱ ሲታወሱ ኖረዋል።

ኢትዮጵያ የተበታተነ የዘመነ መሳፍንት አገዛዝ ታሪክ አስመዝግባ በአንድ ማዕከላዊ መንግሥት ሥር ትተዳደር ዘንድ የተደረገው ትግልና የእርስ በርስ ጦርነት እንደማንኛውም ዓለም የታሪኳ አንዱ ገጽታ ቢሆንም ከሦስት ሺህ ዘመን በላይ የሚወስደን ታሪካችን ከበርካታ ሀገራት ቀዳሚ ሥፍራን ያስይዛታል። የዚህ ታሪክ ተረካቢ ነገስታት በሀገር አንድነት ከጥያቄ ባይገቡም ኢትዮጵያን በልማትና ዕድገት ጎዳና በማራመድ ለቀጣይ ትውልድ አርኣያ የምትሆን ኢትዮጵያን አቅጣጫ ማስያዙና መሰረት መጣሉ ላይ ብዙ የሚቀራቸው ነበር። ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን ለዕድገት፣ የልጆቿን ጀግንነት ለልማትና ብልጽግና ትጠቀምበት ዘንድ ለትውልድ መሠረት የሚጥል አገዛዝ ማግኘት ተስኗታል። ምኒልክ በአድዋ፣ የኢትዮጵያ አርበኞችና፣ ጀግኖች በፋሽስት ወረራ የተቀዳጁትን ድል ለሀገር ዕድገትና ልማት ለማዋል አልታደለችም። ya_tewlid_vol_4_no_1_yekatit_2009

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *