ኢትዮጵያ በህገወጥ የማዕድን ሀብት ንግድ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እያጣች ነው

ኢትዮጵያ በህገወጥ የማዕድን ሀብት ንግድ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እያጣች ነው

ባለፉት ስድስት ወራት ወርቅን ጨምሮ ከማዕድን ሀብት 719 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት ቢታቀድም ማሳካት የተቻለችው 105 ሚሊዮን ዶላር ብቻ መሆኑ ተጠቆመ።

ለዕቅዱ አለመሳካት ወርቅን ጨምሮ በማዕድን ዘርፍ የኮንትሮባንድ ንግድና ህገ ወጥ ዝውውር እየተስፋፋ መምጣቱ ዋነኛ ምክንያት መሆኑን የማዕድን፣ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ባለፉት ስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ከክልል የዘርፉ መስሪያቤቶች ጋር ለመምከር ትናንት በአዳማ ከተማ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ነው ይህ የተገለፀው። በዚሁ ወቅት የማዕድን፣ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር አቶ ሞቱማ መቃሳ እንደተናገሩት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአገሪቱን የውጭ ምንዛሬ አቅም ለማሳደግ እየሰራ ነው።

ለኢንዱስትሪ ግብአትነት የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎች በአገር ውስጥ ተመርተው የውጭ ምንዛሬ እንዲያድኑ በማድረግ የአገሪቷን የምንዛሬ ፍላጎት እጥረት ለመቀነስም እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በነዳጅና በተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ሥራ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እየታዩ ቢሆንም ወርቅን ጨምሮ በማዕድን ዘርፍ የተያዘው ዕቅድ ግን በኮንትሮባንድና በህገወጥ ዝውውር ምክንያት ችግር እንዳጋጠመው ተናግረዋል።

Related stories   የ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ

በአገሪቷ ስምንት ትላልቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ተሰማርተው እየሰሩ መሆናቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ፥ የተወሰኑት የተፈጥሮ ጋዝ በማግኘታቸው ምርቱን ለአገር ጥቅም ለማዋል የ700 ኪሎ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ መተላለፊያ ቧንቧ መስመር ለመዘርጋት የሚያስችል ጥናት መጠናቀቁን አስረድተዋል።

በዓመት በአማካይ 2 ነጥብ 6 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ወጪ በማድረግ ነዳጅ ወደአገር ውስጥ እየገባ መሆኑን አስታውሰው፥ የአገር ውስጥ አማራጮችን በመጠቀም የውጭ ምንዛሬ ወጪውን ለመቀነስ 6 የባዮ ዲዝል እና 5 የኢታኖል ማምረቻ ተቋማት በመገንባት ላይ መሆናቸውን ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

በሚኒስቴር መስሪያቤቱ የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር አቶ ገረመው ነጋሳ በመድረኩ ላይ ባቀረቡት የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻፀም ሪፖርት ላይ እንደገለፁት ከወርቅ ብቻ በባህላዊ አምራቾችና በኩባንያዎች አማካኝነት 17 ሺህ ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ በማቅረብ 348 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት ታቅዶ ነበር ።

Related stories   የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አገር ለማተራመስ በህቡዕ የተደራጁ በርካታ ግለሰቦችን ከነመዋቅራቸውና መስሪያዎቻቸው በቁጥጥር ስር አዋለ፤

ክንውኑ ከዕቅዱ በ243 ሚሊየን ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ደግሞ በ43 ሚሊየን ዶላር ያነሰ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ገረመው እንዳሉት በመጀመሪያው ስድስት ወራት ወርቅን ጨምሮ ከማዕድን ሀብት 719 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት ዕቅድ ተይዞ ቢሰራም ማግኘት የተቻለው 105 ሚሊየን ዶላር ብቻ ነው።

ዘርፉ በዘንድሮ ዓመት ብቻ ለ95 ሺህ 280 ሰዎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም የተፈጠረው የሥራ ዕድል ግን ለ28 ሺህ 761 ሰዎች ብቻ መሆኑ ተመልክቷል።

Related stories   ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ!

ለዕቅዱ አለመሳካት የዓለም የወርቅ ዋጋ መቀነስ፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ተፈጥሮ የነበረው አለመረጋጋት፣ የፌዴራልና የክልል ድጋፍና ክትትል ማነስ፣ የሎጂስቲክ ውስንነትና ሌሎች ተግዳሮቶች አስተዋጽኦ ቢኖራቸውም በዋናነት ወርቅን ጨምሮ በማዕድን ላይ ያንዣበበው የኮንትሮባንድና ህገ ወጥ ዝውውር መሆኑን ኃላፊዎቹ አመልክተዋል።

በኮንትሮባንድ ንግድ የተሳተፉት ወርቅን ከብሔራዊ ባንክ በተሻለ ዋጋ በድብቅ ገዝተው ከአገር በማስወጣትና ከሽያጩ በሚያገኙት ዶላር የፍጆታ ዕቃዎችን ገዝተው በማስገባት የውጭ ምንዛሬው እንዲባክን በማድረግ ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

“ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውም አንዳንዶቹ የሚሰበስቡትን ወርቅ እየቀነሱ ለብሔራዊ ባንክ ማስገባታቸው ችግሩ እንዲባባስ አድርጎታል” ብለዋል።

የችግሩ አገራዊ ጉዳት አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ በፌዴራል ደረጃ የማዕድንና የነዳጅ ኮንትሮባንድና ህገ ወጥ ንግድ መከላከል ኮሚቴና ኮማንድ ፖስት በክልሎችም ተመሳሳይ አደረጃጀት ተፈጥሮ የመከላከል ሥራ መጀመሩተገልጿል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *