አውስትራሊያዊው ግለሰብ ባለፈው አመት ነበር የ1 ሚሊየን ዶላር ሎተሪ የደረሳቸው። ይሁን እንጂ አሸናፊ ያደረጋቸውን የሎተሪ እጣ ቁጥር የያዘ ትኬት ሀሴታቸውን እውን ሳያደርግ እምጥ ይግባ ስምጥ ሳይታወቅ ይጠፋባቸዋል። ደስታቸው በአንዴ የደበዘዘው እኚህ ግለሰብ ላለፉት 14 ወራት የሎተሪ እጣውን ሲያፈላልጉ፤ ሲያስፈልጉ ይከርማሉ። ይህ ጥረታቸውም ተሳክቶ ከሰሞኑ ጠፍቶ የነበረው የሎተሪ እጣ ትኬት በአስገራሚ አጋጣሚ ተገኝቷል።

ስማቸው ያልተጠቀሰው እድለኛ መኪናቸውን እያፀዱ በነበረበት ወቅት ነው የአሸናፊ ቁጥሩን የያዘውን የዕጣ ኩፖን ከአንድ ዓመት በኋላ ያገኙት። ግለሰቡ ሎተሪውን የገዙት ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ ነበር፡፡ የትኬቱ መገኘት ግለሰቡ ከ1 ሚሊየን 20 ሺህ በላይ የአውስትራሊያ ዶላር ወይም 780 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ሽልማቱን ለመቀበል አስችሏቸዋል።

ለ414 ቀናት ያህል የሎተሪ ቲኬቱን የት እንዳስቀመጥኩት ማስታወስ አለመቻሌ በመጠኑም ቢሆን አስከፍቶኝ ነበር ያሉት እኚህ አውስትራሊያዊ፥ በሰሞኑ አጋጣሚ ከመጠን በላይ መደነቃቸውን ነው የተናገሩት፡፡ ገንዘቡን ማግኘት እንደምችል ባውቅም አልተጨነቅኩም ምክንያቱም አሁን ተሳክቶልኛል ብለዋል፡፡ 1 ሚሊየን 20 ሺህ የአውስትራሊያ ዶላሩን ለልጃቸው ቤት መግዣ የተበደሩትን ገንዘብ ለመመለስ እና ለልጅ ልጆቻቸው የትምህርት ቤት ክፍያ እንደሚያውሉት ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ  በምህረት አንዱዓለም ፋና ብሮድካስቲንግ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *