በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በአስገደ ጽምብላ ወረዳ የተገነባው ፋብሪካ በምስፍን ኢንዱስትሪያን ኢንጂነሪንግ የተሰራ ነው። የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ አቶ ፀጋዬ አሰፋ፥ ፋብሪካው በመጪው ሚያዚያ ወር ላይ በሙሉ አቅሙ የማምረት ሥራውን ይጀምራል ብለዋል። ፋብሪካው በቀን 4 ነጥብ 5 ኪሎ ግራም ወርቅ የማምረት አቅም እንዳለውም አቶ ፀጋዬ አስታውቀዋል። ፋብሪካው ሙሉ ለሙሉ ማምረት ሲጀምር ለ200 ሰዎች ቋሚና ጊዚያዊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርም ስራ አስኪያጁ መግለጻቸውን የፋና ዘገባ ያስረዳል።

ኢዛና ወርቅ የህወሃት የንግድ ተቋም ኤፈርት ከሚያስተዳደራቸው ኩባንያዎች መካከል አንዱ ነው። ኤፈርት እጅግ ግዙፍ የንግድ ኢምፓየር የገነባ የፓርቲ ንብረት ሲሆን አቶ ስብሃት እንዳሉት ከአፍሪካ ትልቁ ነው። የአማራው የንግድ ደርጅት ጥረት በቅርቡ የባህር ዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቅናሽ አድርገውለት እነዲገዛ መወሰኑ የሚታወስ ነው። የዳሽን ቢራም የጥረት ንብረት መሆኑ አይዘነጋም። ኦህዴድ የሚያስተዳድረውና በራሱ ክልል ማዳበሪያ እንኳን በወጉ መሽጥ ያልቻለውና  ኮንጎ ጫማ ሲያስመጣ የነበረው ቱምሳ ኢንዶውመንት መሳቂያ ሲሆን፣ የድቡቡ የንግድ ድርጅት ምን ንብረት እንዳለውም በወጉ  አይታወቅም።

 

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *