“Our true nationality is mankind.”H.G.

ኢትዮ ቴሌኮም ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ተዘረፍኩ አለ

መደበኛ ስልኮችን ከውጭ በህገወጥ መልኩ ካስገቡት መሳሪያ ጋር በማስተሳሰር በሚደረግ ማጭበርበር ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ማጣቱን ኢትዮ ቴልኮም አስታወቀ። የኩናንያውን የኮርፖሬት ስራ አኪያጅ አቶ አብዱራሂም አህመድን ጠቅሶ ፋና እንደዘገበው በህገወጥ የሚከናወነው ዝርፊያ የታወቀው በ1994 ዓ ም ነበር።

አሁን በዘግባው ላይ ባይገለጽም በቴሌኮም ዘርፍ የራሳቸውን የማስተላለፊያ መሳሪያ በመኖሪያቸው ተክለው በህገወጥ ስልክ የሚያስደውሉ የነበሩና ድርጅቱን በቢሊዮን ብሮች የዘረፉ በቁጥጥር ስር ውለው ነበር። እነዚሁ ግለሰቦች በዋናነት አገሪቱን ከሚመራው ኢህአዴግ ጋር አብረው የሚሰሩና የስርዓቱ ቅርብ ሰዎች እንደነበሩም በወቅቱ መዘገቡ አይዘነጋም። ከአገር የኮበለሉ እንደነበሩና ከጉዳዩ ጋር በቀጥታ ተያያዥነት ያላቸው ግን ያለተነኩም አካላት ነበሩ። በዛሬው የፋና ዘገባ በወቅቱ 14 ሰዎች መያዛቸውን ከማስታወሱ በቀር በዝርዝር ያለው ነገር የለም።

አገሪቱ ማግኘት የሚገባትን ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ እንደምታጣ የጠቆሙት ሃላፊው ባለፉት ስድስት ወራቶች ብቻ 12 ሰዎች በፖሊስ ቁጥትር ስር መዋላቸውን አመልክተዋል። ሃላፊው በግርድፉ በቴሌኮም ማጭበርበር ከማለት ውጪ በየትኛው ዘርፍ፣ እንዴትና በምን መመልኩ ማጭበርበር እንደሚፈጸም አላስረዱም። ፋናም በዜና ሃተታው አላብራራም።  የፋና ሙሉ ዘገባ ይህንን ይመስላል።

Related stories   ወደ ድርደር ? ከታንክ ወደ አህያ የወረደው ትህንግ በማን ሊወከል?

ኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ በሚፈጸም ማጭበርበር ምክንያት በየዓመቱ ማግኘት የሚገባትን ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ እንደምታጣ ተነገረ። ኢትዮ ቴሌኮም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጸው፥ የቴሌኮም ማጭበርበርን ለመቆጣጠር በቴክኖሎጂ የታገዘ የመከላከል ስራዎች እየተከናወኑ ነው።

የኩባንያው የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱራሂም አህመድ፥ መልኩን እየቀያየረ የመጣው የቴሌኮም ማጭበርበር ተግባር ከመደበኛ ስልክ ወደ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ትኩረቱን እንዳደረገ ተናግረዋል። የወንጀል ድርጊቱ በሃገራዊ ደህንነት ላይ የሚያሳድረው ተፅእኖ ቀላል እንዳልሆነ የገለጹት አቶ አብዱራሂም፥ በእንዲህ መልኩ ገቢዉን የሚያገኙ አካላትም በአብዛኛው ለሽብር ድርጊት የሚያውሉ መሆናቸውን አለም አቀፍ ተሞክሮዎች ይጠቁማል ብለዋል።

Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት " ጁንታው" እጅ ሳይገባ ተያዘ

ከሀገር ውስጥ ጀምሮ በመላው አለም መረባቸዉን የዘረጉ ህገወጥ አካላት ሀገሪቱ ማግኝት የሚገባትን ገቢ እያሳጧት ይገኛሉ ያሉት አቶ አብዱራሂም፥ በዚህ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦችን አድኖ ለህገ ለማቅረብና የወጣውን አዋጅ በማስተግበር ረገድ በዚህ አመት የተሻለ ውጤት መመዝገቡን አብራርተዋል።

ባለፉት ስድስት ወራትም 12 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው በህግ እንዲጠየቁ ተደርጓል ብለዋል። ከፌደራል ፖሊስ እና ከብሄራዊ መረጃ መረብ ደህነት ኤጀንሲ ጋር በመሆን ወንጀሉን በጥምረት ለመከላከል እየተሰራ ሲሆን፥ በህገ ወጥ ተግባሩ ላይ የተሰማሩ ተጨማሪ አካላት ላይ የተጀመረው ምርመራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አቶ አብዱራሂም ገልፀዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሶስት ወራት በቴሌኮም ማጭበርበር ከኢንተርኔት የባከነ ገቢ መጠንን ከ2 በመቶ በታች ለማድረስ አቅዶ 0 ነጥብ 13 በመቶ ማድረሱን አስታውቋል።

Related stories   “…ለዛሬ ብለን ነገን ከምናበላሽ፣ ለነገ ስንል ዛሬን እንሠዋ” አብይ አህመድ

የአሰራር እና ሲስተም ቁጥጥር ማከናወን፣ የሁሉም ደንበኞች የውል ስምምነት በመረጃ ቋት ውስጥ እንዲያዝ ማድረግ እና ከቴሌኮም ኦፕሬተሮች ጋር የውል ስምምነትን ማጠናከር እንዲሀም ሀገር አቀፍ የዲጅታል መታወቂያን ማዘጋጀት ለችግሩ በመፍትሄነት የተቀመጡ ናቸዉ።

ለደንበኞች አሰተማማኝ አገልግሎት መስጠትም ቀጣይ ትኩረት የሚሰጠው ተግባር ነው። ተቋሙ እነዚህን ተግባራት በተጠናከረ መልኩ በማከናወን እየተፈጸሙ ያሉ ማጭበርበሮችን በመከላከል ሃገሪቱ ተገቢውን ገቢ እንድታገኝ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

ኢትዮ ቴሌኮም ዘርፉ ለአጭበርባሪዎች የተጋለጠ መሆኑ የደረሰበት በ1994 ዓ.ም እንደሆነ ነው ከኩባንያው ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው። በወቅቱም 14 ግለሰቦች መደበኛ ስልኮችን ከውጭ በህገወጥ መልኩ ካስገቡት መሳሪያ ጋር በማስተሳሰር መንግስትን ከፍተኛ ገቢ እንዳሳጡ በመረጋገጡ በህግ እንዲጠየቁ ተደርጓል።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0