May 9, 2021

ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

ብአዴን – አመራሮቼና አባሎቼ ህወሃትን ተጠራጥረውት ነበር አለ፤ … ይህ ዝንባሌ የሚቀጥል ከሆነ ” መስመርህን ለይ ” አይባልም፤

Image result for displaced amhara people ethiopiaኢህአዴግ አባል ድርጅት የሆነው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) በዚህ ወር ባሳተመው፣ “አብዮታዊ ዴሞክራሲ-ብአዴን” መጽሔት፣ በክልሉ በተነሳው ረብሻ፣ አመራሮቼ እና አባሎቼ እህት ድርጅታቸውን [ህወሓት] ተጠራጥረውት ነበር አለ።

ብአዴን በፃፈው ሰነድ፣ የትምክህት አስተሳሰብና ተግባር ከመቸውም ጊዜ በላይ ገኖ የተስተዋለበት ወቅት መሆኑን አስታውሶ፤ “ከወልቃይት ሕዝብ ማንነት ጋር ተያይዞ በተነሳው ውዝግብም አመራሮችና አባላት ቀጥታ በማያገባቸው ጉዳይ ገብተው ሕዝቡን ለጉዳት የዳረጉበት እንደሆነ በግምገማ ተረጋግጧል። በወልቃይት ማንነት ዙሪያ ባለቤቶቹ ከቦታው እያሉና ጥያቄ ካላቸው በራሳቸው ታግለው መብታቸውን ሊያስከበሩ እየቻሉ፣ የሌሎች አጀንዳ በሆነ ጉዳይ ተስቦ በመውጣቱ ወይም ቀጥተኛ አግባብ በሌለው ጉዳይ ውስጥ ገብቶ አካባቢን የሚያተራምስ መጥፎ ውድቀት ውስጥ እንደገባ በግምገማችን ተረጋግጧል፤” ብሏል።

amhara women
ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ “አመራሮችም ሆኑ አባላት በተዛባ መረጃ ላይ ተመስርተው እህት ድርጅቱን ተጠራጥረዋል። የአፈጻጸም ችግሮችን በማንሳት ዴሞክራሲያዊና ፀረ-ዴሞክራሲያዊ ኃይሎችን ቀላቅለው ተመልክተዋቸዋል። የትምክህት ኃይሉ፤ አመራሩን ለመከፋፈል ሲንቀሳቀስ የጠላት አስተሳሰብን ተሸክሞ አራግቧል። ተደራጅቶ መመከትና መታገል ሲገባው፣ አይቶ እንዳላየ በተደራዳሪነት ተመልክቷል። ከሁሉም ብሔሮች የተነሱ ጥገኞችን መዋጋት ሲገባው፣ “የእኛና የእኛ ያልሆነ” በሚል ሸፍኖ የመሔድ አስተሳሰብ፣ የአመራሩ ትምክህተኛ አመለካከትና ተግባር አንድ ማሳያ ሆኖ ታይቷል። የራሱ ብሔር ጥገኞችን ቅድሚያ ትኩረት ሰጥቶ በሚፈለገው ደረጃ አልታገለም። በህዝቦች መካከል ዴሞክራሲያዊ አንድነት እንዲጠናከር የሰራው ስራ ደካማ ነው። ብዝሃነትን የማይቀበሉና የዴሞክራሲ አንድነት እንቅፋት የሆኑ አስተሳሰቦችና ተግባራትን በብቃት አልታገላቸውም። የአክራሪነትና የጠባብነት አመለካከቶችንና ተግባራት፣ ከባቢያዊና ጎጠኝት በተለያዩ ደረጃዎች የሚስተዋሉ ሲሆኑ፣ እነዚህን ችግሮች የታገለበት አግባብም ወጥነት አልነበረውም፤” ሲል አስቀምጧል።
Image result for tplf logoእንዲሁም የቅማንት ብሔረሰብን የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄን በወቅቱ አይቶ በዴሞክራሲያዊ አግባብ መፍታት ሲገባው፣ የትምክህት አስተሳሰብና ተግባር በመበራከቱ ምክንያት፣ በወቅቱ ሳይፈታ ከመቅረቱም በላይ ብዙ ጉዳት ደርሷል፤ ሲል የነበረውን ሁኔታ ይፋ አድርጓል። አያይዞም፣ ትምክህት በአስተሳሰብና በተግባር ጣራ ነክቶ ችግር እየፈጠረ በነበረበት ወቅት፣ አዲስ ነገር እንዳልተፈጠረ አድርጎ አቃሎ የማየት ችግር መስተዋሉን በሰነዱ አስፍሯል።
ብአዴን-ኢሕአዴግ የሕዝቦች ብዝሃነት ተከብሮ በብዝሃነት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ አንድነት እንዲረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ተጋድሎ አካሂዷል። ይሁንና በአመራሮችና በአባላቱ ውስጥ ይህንኑ ዴሞክራሲያዊ አንድነት የሚፃረሩ አስተሳሰቦችና ተግባራት ሲራመዱና ሲፈጸሙ ተስተውሏል፤ ሲል ድርጅቱ ገልጿል።
ድርጅቱ ወደኋላ መለስ ብሎም፣ “ብአዴን-ኢሕአዴግ የመጀመሪያ የመስመርና አፈጻጸም ግምገማ ተሀድሶ ባካሄደበት ወቅት፣ ልማታዊ ዴሞክራት ኃይሎች ሰዎችን ከማሕበራዊ መሰረታቸው፣ ልማታዊ ከሆነውና ልማታዊ ካልሆነው መሰረታዊ ባህሪያቸው ተነስተው፣ ሰዎችን የማቅረብ ወይም የማራቅ፣ የመጠራጠር ወይም እምነት የማሳደር ባህሪያት ይኖራል እንጂ፤ በብሔርና በሃይማኖት ማንነታቸው ላይ ተመስርቶ አይመለከትም። አብዮታዊ ዴሞክራቶች ከማሕበራዊ ወገንተኝነት ተነስተው ለሰፊው ሕዝብ መብትና ተጠቃሚነት ወግነው ይሰለፋሉ።”
ድርጅቱ በሰነዱ ላይ ትምክህትና ጠባብነትን ለመታገል ባስቀመጠው አቅጣጫ ላይ እንዳሰፈረው፣ “የዴሞክራሲያዊ የአስተሳሰብ ትግል መድረክ ማዘጋጀት ብቻውን በቂ አይደለም። በሳል በሆኑ የሀሳብ ክርክሮች የትምክህት አስተሳሰብን ለመንቀል ቆርጦ መታገል ይጠይቃል። ከዚህ በተቃራኒ የአስተሳሰብ ችግሮችን ዴሞክራሲያዊ ባልሆነ አግባብ “በቆርጦ መጣልና በጥሎ ማለፍ” አግባብ ለመፍታት መሞከር “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ” አይነት ሁኔታ ያመጣል። የአስተሳሰብ ችግሮች በቆርጦ መጣልና በጥሎ ማለፍ ለመፍታት መሞከር፣ አስተሳሰቡን በብዙ እጥፍ ከማራባት በመለስ ከስር መሰረቱ አይነቅልም።” ሲል አሳስቧል።                                         Related image
“ይህ ማለት ብዝሃነት በሰፈነበት አገራችን፣ ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ስራ ሰርቶ በተግባር የሕዝቡ ሕይወት እየተቀየረ እንዲሄድ በሚያስችል አግባብ የአስተሳሰቡ ትግል ብቻውን ለውጥ ሊያመጣ አይችልም። የእውነት መገለጫውና ማቸነፊያው መሳሪያ ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ተግባር፣ ተጨባጭ የሕዝብ ተጠቃሚነት ነው። በዚህ ላይ የተመሰረተ የትምክህትና የጠባብነት ትግል የሰመረ ይሆናል። ይህንን ትግል የማጧጧፍ ሒደት ዴሞክራሲ ይሁን ስንል፣ ሌላ ስራ የሌለ ይመስል ትምክህትንና መሰል ኋላቀር አስተሳሰቦችን እያራገቡ መኖርን የመረጡ አመራሮችና አባላት ካሉ፣ በቂ የሀሳብ ትግል ከተካሄደና ይኸው ዝንባሌ የሚቀጥል ከሆነ “መስመርህን ለይ” መባል የለበትም፤ ማለት እንዳልሆነ ሊሰመርበት ይገባል፤” ሲል ሰነዱ የመጨረሻውን አማራጭ አስቀምጧል።

Related stories   የ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ

ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ- ምስል ዝግጅት ክፍሉ

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0
Read previous post:
“ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ በስማቸው የተመዘገበ የንግድ ድርጀት የላቸውም” አቶ ግርማ ብሩ

የሚድሮክ ግሩፕ ባለቤት ሼኸ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ በስማቸው የተመዘገበ የንግድ ድርጅት እንደሌለ በአሜሪካን ባለ ሙሉ...

Close