የሚከተለውን ጽሁፍ “ዩንየን ኦሮምያ” ከሚባል የኀዋ ሰሌዳ ላይ ነው ያገኘሁት። የተጻፈው በእንግሊዝኛ ሲሆን ለአንባብያን በሚመች መልኩ ወደ አማርኛ መልሸዋልሁ። ተቀዳሚ ጥሁፉን ለማጣቀሻነት የምትፈልጉ ካላችሁ ከዚህ ጥሁፍ ግርጌ ላይ ያለውን ማስፈንጠሪያ መጠቀም ይቻላል። መልካም ንባብ! (Translated by GM Melaku)

***************************************************************************
ስለኦሮሞ ብሄራዊ የነጻነት ንቅናቄ (ኦነግ መሆኑ ነው) የመጨረሻ ግብ ብዙ ተብሏል፤ ከበቂ በላይ ጽሁፎችን ተጽፈዋል። እስካሁንም አስፈላጊ የሆኑ ውይይቶች በመካሄድ ላይ ሲሆኑ በሁለቱ አበይት የኦነግ ዓላማዎች ላይ በኦሮሞ ብሄርተኞች መካከል ያለውን ል ዩነት ለማጥበብም ስራዎች እየተሰሩ ናቸው። በተወሰኑ አዲስ ባይደሉ ነገር ግን ቀጣይነት እንዲኖራቸው በምንገልጋቸው ጉዳዮች ላይ መወያየትን መረጥኩ። በመጀመሪያ የኦሮሞ ብሄራዊ የነጻነት ትግል የጋራ ግን ምን እንደሆነ ራሳችንን እንጠይቅ? የሁላችንም መልስ ባንድ አፍ “የኦሮሞ ህዝብ ትግል ከባዕድ ወራሪ አገዛዝ ራሱን አላቆ የወደፊት እጣ ፋንታውን በራሱ የመወሰን መብትን መጎናጸፍ ነው” እንደምንል ጥርጥር የለኝም። ይህ የጋራ የመስማሚያ ሰነዳችን እንዳለ ሆኖ የኦሮሞ ህዝብ ከነጻነት ማግስት ሊያሳካቸው የሚፈልጋቸው ሁለት የተለያዩ ግቦች እንዳሉ በቡድንም ሆነ በተናጠል ያስተዋልነው ጉዳይ ነው። እነርሱም የኦሮምያ ነጻ መንግስት ወይም የተባበረች ኦሮምያ ናቸው። ሁለተኛው አማራጭ በብዛት ኦሮምያ ባለበት ኢትዮጵያን ዲሞክራሲያዊ ማድረግ እየተባለ ይነገራል።

እነዚህ ሁለት ጽንሰ ሃሳቦች ይገቡን ዘንድ አንባቢዎቸ ከዚህ በፊት ስለ ገዳ ኦሮምያና የተባበረች ኦሮምያ (ታላቋ ኦሮምያ) የጻፍኳቸውን መጣጥፎች መዳሰሱ ተገቢ ነው። ገዳ ኦሮምያ ስል በዘልማድ የምናውቃትን ኦሮምያ (ኦነግ የሳለውን ካርታ) የሚባለው የኦሮሞ መሬት ማለቴ ነው። በሃሳብ ደረጃ ላይ የሚገኘው የተባበረች ኦሮምያ ጽንሰሃሳብ በሶስቱን የፖለቲካ ጎራዎች (በአንድነቶች፣ በፌደራሊስቶች (ሱቱፋን)ና በኦሮሞ ብሄርተኞች ) ዘንድ ለጊዜውም ቢሆን ተቀባይነትን አላገኘም። የኢትዮጵያዊነት አቀንቃኞች ኢትዮጵያን ስልታዊ በሆነ መልኩ የማጥፋት ሴራ ነው በማለት የስም ለውጡን (ከኢትዮጵያ ወደ ኦሮምያ) በጽኑ አውግዘውታል። ሱቱፋኖቹ እኛንኑ የወደፊት አድራጊ ፈጣሪና ኦሮሞነትን በግዳጅ ሌሎች ነገዶች ላይ ለመጫን ያሰብን ያስመስለናል በሚል በስያሜ ለውጡ ደስተኞች አይደሉም (ለውጡን ግን ይፈልጉታል የሚል አዝማሚያ አለው ጥሁፉ)። ጽንፈኛ የኦሮሞ ብሄርተኞች የስም ለውጡ የሀገሪቱን አይቀሬ መበታተን ለመታደግ የተጠነሰሰ ሴራ ነው በሚል በጥርጣሬ ነው የሚያዩት።

ኦሮምያን ያካተተ የተባበረች ኦሮምያን ግብ ያደረጉ አብዛኞቹ ልክ እንደአቢሲኒያውያን ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ጠብቀው ለማቆየት የሚሹት ናቸው። ቅኝ ገዢዎች ፊንፊኔን አዲስ አበባ ኦሮምያን ኢትዮጵያ ብለዋታል። የአማራ ሊቃውንት ላለፉት 80 ዓመታት ዐማራነታቸውን ከኢትዮጵያዊነታቸው ብብት ውስጥ ወሽቀውታል። በተመሳሳይ መልኩ የትግሬ ሊቃውንት የአማራን ፈለግ በመከተል ከ 1983 ጀምሮ ትግሬነታቸውን ኢትዮጵያዊነት ውስጥ ደብቀውታል። የኦሮሞ ጽንፈኞች በአሁኑ ሰዓት መስቀለኛ መንገድ ላይ ይገኛሉ፡ ልክ እንደ አማራና ትግሬ ሊቃውንት ኦሮሞነታችን ኢትዮጵያዊነት ዉስት ደብቀን የበላይነታችን እንቀዳጅ ወይስ ጨከን ብለን (የፈጀውንም ፈጅቶ) ኢትዮጵያን ኦሮምያ ብለን ለራሳችን እንጥቅልላት በሚል። እኔ ሁለቱንም አማራጭ መጥቀም ያሻል ባይ ነኝ። የአለም አቀፉን ማህበረብ ጋርም ሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሌሎች ነገዶች ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ስንቀርብ የኢትዮጵያውነትን ለምድ መልበስ በእጅጉ ጠቃሚ ነው። ከኦሮሞ ህዝብ ፊት ስንቀርብ ግን የስም ለውጡ ላይ ማተኮሩ (ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ አጥፍቶ ኦሮምያ ማድረግ) ለጉሮሮ ተስማሚ ነው። የኦሮሞ ህዝብ ትግልስ ነጻነቱን መቀዳጀትም አይደል? በነጻ ኦሮምያም ሆነ በተባበረች ኦሮምያ!

ኢትዮጵያ የሚለው ስም ስልጣንና ከስልጣን ጋር በተያያዘ የፖለቲካ ጥቅም ላስገኘለት ለቅኝ ገዥው በቀና የሚታይ ቢሆንም በግዛቱ ስር የጭቆናን ቀንበር ለተጎንጩ ቅኝ ተገዥዎች የጨቋኝነት ተቀጽላ ያለው ነው። ለዚህም ነው “እኛ ከአሰራሩ እንጅ ከስሙ ምን አለን?” የሚሉ የኦሮሞ ብሄርተኞች ሃሳብ ውሃ የማይቋጥረው። ስሙ ምንም ፋይዳ ከሌለው አቢሲኒያውያን ስለምን ኢትዮጵያ ወደ ኦሮምያ እንደገና መሰየምን ስለ አብሮነታና ስለሚሳሱለት የሃገር ዳር ድንበር ሲሉ ለምን አሜን ብለው አይቀበሉም ?? እኔ የኦሮሞ ብሄርተኞች የሃገሪቱን ስያሜ ብቻ ሳይሆን የሃገሪቱን ተቋማትም እንደገና መሰየም አለባቸው ባይ ነኝ። ለምሳሌ “በኢትዮጵያ አየር መንገድ” ፋንታ “የኦሮምያ አየር መንገድ”፤ “በኢትዮጵያ ቡና” ፋንታ “የኦሮምያ ቡና”፤ “የኦሮምያ ብሄራዊ ቡድን” ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወዘተ ሁሉም በየተራ መለወጥ አለባቸው። ስያሜው መሰረት የሚያደርገው ደግሞ ሁሉም ተቋማት ፊንፊኔ ኦሮምያ ውስጥ መገኘታቸው ነው። ስለሆነም የኦሮሞ ዜጎች ልክ ፊንፊኔን እንደምንጠቀመው ሁሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የስም ለውጡን ማጧጧፍ አለባቸው።የስም ለውጡን ለማድረግ የማንንም ይሁንታም ሆነ ፈቃድ እንሻም።

ያለማንም ፈቃድ አዲስ አበባን ፊንፊኔ እንዳልናት ሁሉ ኢትዮጵያንም የተባበረች ኦሮምያ ስንላት ከጠቅላዩ የአማራው ሊቃውንት ኢትዮጵያ፤ ከአሁኒቷ የአፓርታይድ የትግሬ ኢትዮጵያና የወደፊት የገዳ ኦሮምያ ነጥለን ማየት አለብን። የትኛውን አይነት እንጠቀም የሚለው የሚወሰነው ደግሞ በነጻነት የሚያስበው የወደፊቱ የኦሮሞ ህዝብ ይሆናል። የኦሮሞ ሱቱፋናውያን (ፌደራሊስት) በድፍረት የተባበረች ኦሮምያን በመቀበል ፋንታ ኢትዮጵያ የሚል ስያሜን ለማስቀጠል መከጀል ግራ ሊያጋባን አይገባም። ፍላጎቱ መምጣት ያለበት ከአንድነት ሰባኪ አቢሲኒያውያን እና ተገንጣይ ጽንፈኛ የኦሮሞ ብሄርተኞች በሚያነሱት ፍላጎትና ስምምነት ይሆናል። የባቢሎናውያንን ስለኢትዮጵያ ያለውን ግርታ ለማጥራት የሚከተሉትን ትርጓሜዎች ደጋግመን እንይ
1) ለግሪካውያን ኢትዮጵያ ማለት የጥቁሮች ምድር የሚኖሩ የተቃጠለ የሚመስል ፊት ያላቸው ሰዎች የሚኖሩበት አገር ነው
2) ለአይሁዳውያን ከግብጥ በስተደቡብ የሚገኘው የኩሾች ምድር ማለት ነው
3) ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአፍሪካ ቀን ያለች አገር ናት
4) እንደ ፕሮፌሰር ሜጋሎማቲስ (የቱርክ ዜጋ ነው) ከሆነ ደሞ ኢትዮጵያ ከአቢሲኒያውያን ዉጭ ያለው የኩሾች ምድር ነው
5) ለአቢሲኒያውያን ሊቃውንት ደግሞ ኢትዮጵያ ማለት አቢሲኒያና የበላይነት ስርዓቷ ነው።
6) ለድሮ ስርዓት ናፋቂዎች ኢትዮጵያ ማለት አማራ ማለት ነው
7) አሁን ላሉት የትግሬ የግዥ መደብ፤ ኢትዮጵያ የህወኃይ የቅኝ ግዛት ጭምብል ናት።

የመጀመሪያውን ትርጉም ስናይ ሁሉም ጥቁሮች ኢትዮጵያዊያን ሊባሉ ይችላሉ። ኢትዮጵያዊነት የሚለው ሃይማኖትም በሰሜን አሜሪካና የተጀመረ በደቡብ አፍሪካ የተጀመረ የጥቁር ሰዎች እንቅስቃሴ ነው። ሁለተኛና አራተኛውን ትርጓሜ ስናይ ደሞ ኢትዮጵያዊነት ከአቢሲኒያውያል ይልክ ለኦሮሞዎች ይበልጥ ተስማሚ ነው። የሶስተኛው ትርጉም ጃዋር ሞሃመድ እንዳለው በኦሮሞ ላይ የተጫነ ማንነት ወደሚለው ያጋድላል። የመጨረሻ ሶስት ትርጓሜዎች ኢትዮጵያን በስሯ የሚኖሩ ህዝቦች የጋራ ማንነት ለማስመሰል ሲባል የተቀመሙ ናቸው። ለዚህም ነው ስሙ በከፊል የኦሮሞ ብሄርተኞች ዘንድ የተወገዘ የሆነው። ስለወደፊቷ ኦሮምያ ስናወራም አሁን ኢትዮጵያ የምትባል ሃገርን ሙሉ በሙሉ ኦሮምያ ብለን ሰይመን የሚኖረውን አገር ማለታችን ነው። ያ ውሳኔ እስኪወሰን ድረስ የኦሮሞ ዜጎች ኦሮምያ ብለው መጥራት ሲችሉ ሌሎቹ ነገዶች ኢትዮጵያ ብለው መጥራት ይችላሉ። ይህ በሌሎች ሀገሮችም ያለ ነው፤ ለምሳሌ ጀርመንን እንውሰድ ጀርመኖች አገራቸውን ደችላንድ ብለው ሲጠሩ አሜሪካውያን ጀርመኒ ፈረንሳውያን አለማኝ ብለው ይጠሯቸዋል።

Related stories   ህወሓት፤ የኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ጠላት!

የነጻ የኦሮምያ ግዛት ምስረታም ይሁን የተባበርች ኦሮምያ (የስም ለውጡ) ትግላችን ዳር ለማድረስ አሁን ያለውን ጨቋኝ ገዥ ለማስወገድ ወሳኝ ሃይል ያስፈልገናል። ይህን ለማድረግ ደግሞ በመካከላችን ያለን ል ዩነት ወደጎን ከማድረግና ሌሎች የተጮቆኑ ነገዶች ጋር የጠነከረ ትብብር ማድረግ ወሳኝ ይሆናል። ይህን ትብብር ለማግኘት ለሌሎች የተጨቆኑ ብሄሮች የይስሙላ የፌድራል ስርዓት ማባበያ ጠፍጥፎ በመስራት የኦሮሞ ፌደራሊስት ብሄርተኞች ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። ይህኛውን የነጻነት መስመር ለመከተል ከወሰንን የተባበርች ኦሮምያን በሚከተሉት አምስት አብይት ውሳኔዎች ማሳካት ይቻላል። ይህን መንገድ መከተሉ በስፋት የሚቀነቀነው ኢትዮጵያዊነት ኦሮሞነትን እንዳይበርዝ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ማድረጉ ወሳኝ ነው
1) ከህወሃትና ከማንኛውም የአገራዊ የበላይነትን ከሚቆናጠጥ ማንኛውም ሃይ ነጻ መውጣት በሪፈረንደም የራሳችንን ነጻ ግዛት ወይም የተባበረች ኦሮምያን ለመመስረት ያግዘናል።
2) ሁለተኛውን መንገድ ከመረጥን ኦሮምያ (የጀግኖች ምድር) በኢትዮጵያ ፋንታ የአገሪቱ ስም እንዲሆን ማድረግ
3) ዲሞክራሲ እስከ የራስን እድል በራስ እስከመወሰን የሚሉ የፖሊቲካ ጨዋታዎችን የሃገሪቱ ህገ ደንብ ውስጥ ማካተት
4) ኦሮምኛ ቋንቋን በአማርኛ ፋንታ ያገሪቱ ተቀዳሚ ቋንቋ ማድረግ
5) ኦዳ (የዋርካው ስእል) የአገሪቱ ሰንደቅ አላማ ላይ ማስቀመጥ

የነዚህ አምስቱ ቅድመ ሁኔታ መሟላት ብቻ ወደ ዘላቂነት ወዳለው ፌደራላዊ ስርአት ሊያመራ እንደሚችል ጽኑ እምነታችን ነው። አቢሲኒያውያንን ጨምሮ ሌሎች ነገዶች እነዚህን መቀበል ካልቻሉ ወይም የኦሮሞ ብሄርተኞች ቅድመ ሁኔታዎችን ለድርድር ማቅረብ ሳይችሉ ከቀሩ ነጻ የገዳ ኦሮምያ መመስረቱ አይቀሬ ነው። ያ እንዳይሆን ማድረግ የሚችለው የአንድነት ሃይሎችና የኦሮሞ ፌደራሊስት ብሄርተኞች የሚያደርጉት ትብብርና ስምምነት ነው።

የተባበረች ኦሮምያን ጽንሰ ሃሳብ ሁሉም የአገሪቱ ዜጎች የሚስማሙበት ከሆነ፤ ሁሉም የነጻነት ታጋዮች ባንድ ላይ ህውኃትን ለመጣል መረባረብ እንጀምራለን። ከህውኃት ውድቀት በሁዋላ ስለሚኖረን የዲሞክራሲያዊ አገር የጋራ ሰነዶች እናዘጋጃለን። ለዚህ ዓላማ ስንል ከህወኃት በፊት የነበሩትን የታሪክ ገጠመኞች ለታርክ ባለሙያዎች ከህወኃት ውድቀት ስለሚኖረው ሁኔታ ለህዝብ ትተን ላሁኑ ህወኃትን ስለመጣል ትኩረታችን እንዲሆን መርጠናል። ህወሃት ከተወገደ በሁዋላ የኦሮሞ ዜጋ ሁለት አማራጮች አሉት የገዳ ኦሮምያይ ከቅኝ ግዛት ማስለቀቅ ወይም የተባበረች ኦሮምያን ዲሞክራሲያዊት ማድረግ። የኦሮሞ ህዝብ ራሱ እስከወሰነ ድረስ አንዱ ከሌላው የተለየ ጉዳትም ይሁን ጥቅም የለውም። ሁለት የቅንጦት መኪኖችን የመምረጥ አይነት ነገር ነው (ማርቸዲስ ወይስ ቢ ኤም ደብልዩ)

በመጨረሻም፧ የምንመርጠው የገዳ ነጻ ኦሮምያም ሆነ የተባበረች ኦሮምያ የኦሮሞ ህዝብ በኦሮምያና በኦሮሞነት መስማማት አለበት። ኢትዮጵያዊነት ሃበሻዊነት የሚል ስሜት ያዘለ፤ አቢሲኒያዊ ብሄርተኝነትና ኦሮሞነትን የሚቃወም ስለሆነ አንቅረን ልንተፋው ይገባል። ለዚህም ነው በሙሉ ልባችን “የመጀመሪያውን የኦሮሞ እንቅስቃሴ” የደገፍነው። ያ ንቅናቄ ተገንጣይና ፌደራሊስት የኦሮሞ ብሄርተኞች እኩል ያሳተፈ ነበር። የፕሮጀክቱ ባለቤቶች አንድነት አቀንቃኝ ኦሮሞዎች ቢሆኑም በክብር የሚያራምዱት ግን ተገንጣይ ብሄርተኞች ናቸው። ይህ ንቅናቄ በሁለቱ የኦሮሞ ብሄርተኝነት ጎራዎች መካከል የማይታረቅ ልዩነት እንደሌለ ያስመሰከር ንቅናቄ ነበር። ሃሳቤን በዘወትር ጸሎቴ ልደምድም ፤ በኢትዮጵያዊ ጭንብል ለተጀቦነው አቢሲኒያዊነትን ለመዋጋት ዋቃ (ያምላካቸው ስም) የኦሮሞነትን የጋራ ንቅናቄ ይባክልን።
አመሰግናለሁ!

source – https://www.facebook.com/mesganaw.andualem.5/posts/262506824201778

Alternative to Independent Oromia is Union Oromia

More than enough has been written about an ultimate goal of the Oromo national liberation movement. Still, the necessary discussion on this issue is going on and the discord among Oromo nationalists regarding the known two objectives is also obvious. Here, I want to discuss in short on the ideas which are not new as such, but for the sake of continuity. Firstly, let’s ask ourselves: what is the common objective of the Oromo national liberation struggle? No question that we all may automatically reply that the objective of the Oromo people is freedom from the alien rule and to exercise self-determination on the national future destiny. This being our common ground, yet we do observe among Oromo public that there are two specific post-freedom goals pursued by individuals and groups in Oromo community: an independent Oromia and a union Oromia  – this second option being usually told as “democratization of Ethiopia”; i.e democratized Ethiopia = de facto Oromia.

To comprehend what I mean by the two concepts, I would like readers to look at the articles I wrote till now to define Gadaa Oromia and Union Oromia (Great Oromia). By Gadaa Oromia, I just mean the conventional Oromia (the map given by the OLF), which was also named as Oromoland and Gadaa Oromia in my previous opinions. Despite the intentions implicitly put in the hitherto articles, the concept of Union Oromia is rejected by all three political movements in the empire: Ethiopianists, Federalists and Oromianists. Ethiopianists vehemently oppose the name change (Ethiopia to Oromia) for they thought it is a “systematic way of deleting the glorious name of Ethiopia.” Federalists are not happy about the move for they are very cautious not to be suspected as the future authoritarians to impose Oromummaa on other nations. Oromianists are very suspicious for they thought that the suggestion is a subtle way of saving the empire from the indispensable disintegration.

Those who want to achieve an integrative union Oromia actually tend to use the name Ethiopia as a trademark just as the Abyssinians used to instrumentalize the name until now. The colonizers just named our Finfinnee as Addis-Ababa, and our Oromia as Ethiopia. Amhara elites are hiding their Amharanet behind Ethiopiawinet for more than 80 years, while Tigrean elites are doing the same masking of Tigrawinet behind Ethiopiawinet since 1991. Now, the dilemma for Oromianists is whether trading with the name Ethiopia like the Abyssinians are doing or whether boldly re-naming the whole country as Oromia, whatever risk it may entail. I do recommend using both: towards the international community and when approaching other nations in the empire, it is possible to make business using the name Ethiopia, whereas the concept of Oromia is more palatable for Oromo nationals. So, it is necessary to weigh the advantage and disadvantage (calculate the benefit and cost) of using the name Ethiopia as a trademark. After all, common goal of Oromo nation is freedom to get a chance for referendum on: own Oromo state vs union Oromia state.

Related stories   እውነትን ለሥልጣን መናገር !! ሳማንታ ፖወር - ለኢትዮጵያ ዘር ፖለቲከኞች መከላከል አቁሚ!

The name Ethiopia is positively connotated for the colonizers, who enjoyed the privilege of power and profit within this political community in relation to the name, whereas it is negatively associated with all the variables of oppression for the colonized people, who suffered under the empire’s system of domination and who thus fought against the empire. That is why the argument of some Oromo nationalists, who usually say “what matters is the content, not the name,” does not hold water. If the content is what matters, then Abyssinianists should have easily accepted the re-naming of Ethiopia as Oromia just for the sake of promoting unity and keeping territorial integrity they are craving for. I think Oromo nationals should move further and rename not only the country, but also the whole of its institutions. For instance, we just can call ‘Oromian Airlines,’ instead of Ethiopian Airlines; ‘Oromian coffee,’ instead of Ethiopian coffee; ‘Oromian international sport team,’ instead of Ethiopian sport team, … etc. This re-naming is actually based on the fact that all the institutions are based in Finfinnee, Oromia. So, Oromo nationals should feel free and use this new re-naming just as we did use the name Finfinnee, despite the official name of Addis-Ababa. We do not have to wait for any permission or recognition from Abyssinian authorities or from anybody else.

When we will be able to rename the whole country as Oromia without waiting for any permission or recognition, just as we did to Finfinnee, then we can clearly differentiate the past assimilative Ethiopia of Amhara elites and the present apartheid Ethiopia of Tigrean rulers from the future possibilities of an independent Gadaa Oromia of the pro-independence Oromo or an integrative Great Oromia of the pro-union Oromo, which can be achieved based on free will of the future free Oromo people and free other peoples in and around Oromia. The matter of fact that Oromo federalists tend to instrumentalize the name Ethiopia, instead of boldly accepting the demand of claiming Oromia should not confuse us here. The demand actually should come from pro-unity Abyssinians or other nations and pro-independence Oromoians need to make the same offer, so that both the demand from Abyssinians and the offer from Oromians can match. To clarify the Babylonic confusion regarding the name and use of Ethiopia, we have to repeatedly look at the following seven definitions:

1) for ancient Greeks, the country called Ethiopia was where those with “burnt face” lived, i.e. the land of blacks, which included the whole of Africa;

2) for Biblical Jews, it is the land of Cush located south of Egypt;

3) for international community now, it is the currently existing state in Horn of Africa;

4) to people like Prof. Megalommatis, Ethiopia is equivalent to non-Abyssinian part of Cushland;

5) for Abyssinian elites, Ethiopia simply means Abyssinia including its system of domination;

6) for nostalgic and conservative politicians of the empire, Ethiopia is same as being Amhara; and,

7) for the currently ruling class of Tigreans, Ethiopia is a mask for the TPLF’s colonial rule.

According to first definition, the whole blacks can claim to be called Ethiopians, thus the religion called Ethiopianism was black movement commenced in both North America and South Africa. Taking the second and fourth definitions into consideration, the name Ethiopia is more appropriate for the Oromo (Cushites) than Abyssinians, who claim to be from Semitic origin. Third definition was – which Jawar Mohammed regarded as an identity ‘imposed on the Oromo.’ The last three definitions are contaminations which made this name, Ethiopia, be seen as not appropriate, if we want to use it as a common identity for all nations in that empire. That is why the name is rejected by part of Oromo nationalists. When we talk about future possible Oromia, it actually means re-naming of Ethiopia as Oromia based on the future free will of peoples in the country. Till that decision of nations, Oromo nationals can call the country Oromia, whereas at the same time others call it Ethiopia. That a certain country does have two or more names at a time is not new. For instance, Germans call their country Deutschland, whereas Americans call it Germany and French people name it Allemagne … etc.

Related stories   “ወያኔ እየሠራው ባለው ግፍና በደል ትግራይ ከፍላ የማትጨርሰው ዕዳ እየተቆለለባት ነው!”ሲሉ ሰምቼ…

Be it Oromo nationalists struggle for either an own Oromo state or a union Oromia state, we need an indispensable force to get rid of the currently ruling oppressive regime. To get such effective force, there is no better alternative to the imperative unity of purpose among Oromo nationalists as well as an important alliance with forces of other oppressed nations. In order to get such alliance, those who struggle for an integrative union Oromia will have more chance for their goal is the same as forging ‘new federal democratic Ethiopia,’ which is the wish of most oppressed nations in the empire. If we really opt for this version of liberation process, in which both unity and integrity of union Oromia will be kept intact, we will definitely have basic decisions on five areas as shown below.

It is fact on the ground that despite this goal of union Oromia, the ongoing campaign of Ethiopiawinet (Ethiopian nationalism) to dilute Oromummaa (Oromo nationalism) is a futile exercise. If keeping territorial integrity of the union will be chosen by Oromo people, then we need to move on and struggle to realize the following five important virtues: 1) freedom from the hegemonist TPLF and from any sort of national domination so that we can decide per referendum on an own Oromo state vs a union Oromia state; 2) if we opt for the second, then Oromia (land of the braves) to be name of the future true federation, replacing Ethiopia (land of the burnt face); 3) democracy, including the national self-determination, to be future rule of political game in the federation/union; 4) Afan Oromo to be primary working language of federal government in the union; 5) Odaa to be central part of flag for the union. Only fulfillment of these five parameters can be a possible guarantee for the future long-lasting multinational federation. If the other nations, including Abyssinians, fail to put this demand forward and/or Oromians fail to give this offer, further push for an independent republic of Gadaa Oromia is inevitable. It is up to the pro-unity forces to choose and demand an integrative union Oromia in order to avoid disintegration of the union, which will be caused by an eventual independent Oromo state.

If all other nations agree on this concept of union Oromia, all freedom fighters in the empire can cooperate on basic principles of freedom from TPLF and democracy after TPLF. For this purpose, let’s leave the past pre-TPLF events to professional historians and the future post-TPLF eventualities to the public verdict, so that we can concentrate now on how to get rid of the present oppressive regime. After getting rid of the fascist and racist regime, Oromo nation surely do have two good alternatives from which we can choose: decolonization of Gadaa Oromia and democratization of Union Oromia (“democratization of Ethiopia”). For Oromo people, there is no disadvantage in both options, as long as the decision will be made per Oromo’s public verdict. It is just as a choice between the first-class cars,  if one does have enough money to buy one of the luxury cars, such as Mercedes and BMW. That is why denouncing union Oromianists as “betraying Ethiopianists” is logically and morally wrong.

Last, but not least, be it that we will opt for either independent Oromo state or union Oromia state, now all Oromo nationals should agree on Oromia and Oromummaa. Ethiopiawinet, in a sense of Habeshawinet (Abyssinian nationalism), which is opposing Oromummaa, should be vehemently rejected. That is why we wholeheartedly supported the ‘Oromo first movement.’ This movement was actually a common project for both pro-independence and pro-union Oromianists. By the way, main carrier of the project are  pro-union Oromo nationalists, whereas those who are most proud of the movement are pro-independence nationalists. That is why this project has classically and successfully shown how the two groups of Oromo nationalists do not actually have an irreconcilable conflict as they have usually tried to portray their image. I have personally never believed in such irreconcilability of the conflict, and I have always tried to show the common denominator of the two groups, i.e freedom from domination and self-determination of Oromo nation per referendum. Now, I just would like to conclude my opinion with my usual prayer: may Waaqa help us promote this common movement of Oromummaa against Abyssinianism masked with Ethiopiawinet!
Galatooma

https://unionoromia.wordpress.com/2017/03/11/alternative-to-independent-oromia-is-union-oromia/

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *