አሌክስ ዛንቼዝና ኦዚልን ኮንትራታቸውን እንዲያራዝሙ ድርድር እየተደረገ መሆኑንን አርሰን ዌንገር ገልጸዋል። ቬንገር የቀረበላቸውን የሁለት ዓመት ኮንትራት አስምልክቶ ለጊዜው ውሳኔያቸውን አላሳወቁም።

“ለጊዜው ከስምምነት አልደረስንም” ሲሉ ሳንቼዝን አስመልክቶ ለተጠየቁት መልስ መስጠታቸውን ቢቢሲ ስፖርት ነው የዘገበው። ለቶክ ቤልን ስፖርት ሲናገሩ ደግሞ  አሁን ቀሪ ውድድር ላይ ትኩረት ለማድረግ መስማማታቸውን አመልክተዋል። የኮንትራት ማራዘሙን ጉዳይ ከውድድር በሁዋላ እልባት እንደሚያደረግበት ገልጸዋል።

የኦዚልም ጉዳይ ተመሳሳይ መሆኑንን ያስታወቁት ዌንገር፤ ስምምነት ላይ ሳይደረስ ምንም ማለቱ ጥሩ እንዳልሆነ አመልክተዋል። በክለቡ የምቆይበት ጊዜ ምንም ቢሆን ለክለቡ/ ለሃላፊነታቸው በቁርጠኛነት እንደሚሰሩ ነው የተናገሩት። አርሰናል ከሲቲ በመጪው እሁድ እንደሚጫወቱ ይታወቃል።

ይህ በንዲህ እንዳለ የተለያዩ መግናኛዎችና ታብሎይዶች አርስናል በርካታ ተጫዋቾችን ጠራርጎ እንደሚያስወጣ ወይም አብዮት እንደሚካሄድ፤ በሌላ በኩል ደግም ምትክ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ሩጫ መጀመሩን እየዘገቡ ነው። ከአርሰናል ጋር በዘውውር ስሙ ያለተነሳ ተጫዋች ስለሌለና ሚዲያዎቹ የማሻሻጥ ስራም ስለሚሰሩ አርሰናል ሊገዛቸው ያሰባቸውን ተጫዋቾች መዘርዘሩ ብዙም አግባብ አይሆንም።

ባየር ሙኒክ በደርሶ መልስ 10 ጎል ያቀመሳቸው አርሰን ዌንገር ባለፉ ባገደሙበት ተቃውሞ ቢጎርፍባቸውም፣ ፓሪስ ሴንት ዠርመን የሁለት ዓመት ኮንትራት አዘጋጅቶ ኑልኝ ማለቱም ተሰምቷል። እሳቸው ግን አርሰናልን ስለመልቀቃቸው በግልጽ ከመናገር ተቆጥበው ” ጠበቁ” ባይ ሆነዋል። ከማሰልጠን ስራም እንደማይርቁ አስታውቀዋል።

አርሰናልን ክለብ በማድረግ ረገድ ሊረሳ የማይችል ተግባር ያከናወኑት የ67 ዓመቱ ዌንገር  የነዋልኮት፣ ቼምበርሊን፣ ዊልሼር፣ ራምሲ… አንድ ላይ መነሳት በሽያጭ የከሰሩዋቸውን ተጨዋቾች ተከተው ክለቡን ያነሱታል የሚል ተስፋ ሰንቆላቸው ነበር። ያሰቡት ሳይሆን ቀርቶ ዛሬ ላይ ደርሰዋል። አሁን ላይ ደግሞ ብር አውጥቶ የበሰለውን መግዛቱ ላይ ትኩረት ለማድረግና ቀጣዩን ዓመት የተሟላ ቡድን የመስራት እቅድም እንዳላቸው በግልጽም ባይሆን በተዘዋዋሪ ምልክት እየታየ ነው። ክለቡም ቢሆን ገባታ ላይ ያስቀመጠውን የሁለት ዓመት ኮንታራት ማራዘሚያ ስለማንሳቱ ያለው ነገር የለም። ይልቁኑም የዶርትመንት አሰለጣኝ አርሰንን ሊተካ ድርድር ላይ ነው የሚለውን ዜና ፍጥኖ ነው ያስተባበለው።

አርሰናል ተጨዋቾች መካከል ሽረ እንደተጀመረና የመጫወት ፍላጎት ሁሉ የሌላቸው ተጫዋቾች እንዳሉም አስተያየት እየተሰጠ ነው። አለን ሺረር እንዳለው በዌስት ብሮሚች ጋር በነበረው ጨዋታ አሌክስ ሳንቼዝ ብቻ ነው ሲፋለጥ የነበረው። ሌሎቹ የመታገል ስሜት እንኳን አይታየባቸውም ነበር ነው ያለው።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *