ሃብታሙ አያሌው ከቪ.ኦ.ኤ. ጋር ያደረገዉን ቃለ -ምልልስ በሃዘንና በብስጭት ስሜት ዉስጥ ሆኜ ተከታተልኩት።በወገኖቻችን ላይ የደረሰዉንና እየደረሰ ያለዉን ሰቃይና መከራ ከዚህ በፊት በሥማ -በለው ሰምቼው የማውቅ ቢሆንም የግፉን ፅዋ በዓይኑ ካየ ሰው፣ በአካልና በመንፈስ ከተቀበለ ሰው መስማት ህመሜን አባባሰው።
በቃለ -መጠይቁ መካከል በማዕከላዊ እስር -ቤት ውስጥ የዘረኛው ወያኔ መንግስት ጀሌዎች ከሚፈጽሟቸው አሰቃቂ ኢ-ሰብዓዊ ዎንጀሎች መካከል በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ምክንያት ሊገልጻቸው ያልፈለጉና ያልተናገራቸው አንዳሉ ጠቅሷል። በበኩሌ ግፍንና በደልን በዝርዝር መናገርና በፅሁፍም ማስቀመጥ ተገቢና አስተማሪ ነው የሚል የግል አቋም አለኝ።”ምን አይነት በደሎች እየተፈፀሙበት እንዳለ የማያውቅ ህዝብ እንዴት ለትግል ይነሳል ?” የሚል ጥያቄ ስለሚያጭርብኝ። ስለሆነም ሀብታሙ ለወደፊቱ ይፋ ያወጣዋል ብየ እጠብቃለሁ።ለአሁኑ ግን ወደ እኔ መላ-ምት ልመለስ።
እንደ አይሁድ ሰውን በመስቀል ላይ ሰቅሎ ከማሰቃየት የበለጠ ፣ የወንድ ብልት ላይ ሁለት ኪሎ የሚመዝን ፕላስቲክ ሙሉ ውሀ አንጠልጥሎ ከማኮላሸት የበለጠ ፣ ኩላሊትን አየደበደቡ ሽንትን ከማሸናት የበለጠ ፣ ሰው በለበሰው ልብስ ላይ እንዲፀዳዳ ከማድረግ የበለጠ ምን ሊያደረጉ ይችላሉ ? የሚለዉ ህሊናየ ውስጥ ተመላለሰብኝ ፣ እረፍትም ነሳኝ።ሃብታሙን እንዳይናገረው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የከለከለው የግፍ አይነት ምንድን ነው ? ኢትዮጵያዊ አድርጎት የማያውቅና ሊናገረው የተፀየፈው ፣ ወያኔ ግን የሚፈፅመው የተለየ የማሰቃያ ዘዴ ምንድን ነው ? አለመናገሩስ ጥቅምና ጉዳቱ ምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄወችን ህሊናየ መልስ እንዲሰጠኝ ተሟገትኩት።
ከብዙ ሙግት በኋላ ግን መቼም ወያኔ ኮርጆ እንጂ አዲስ ነገር ፈጥሮ አያውቅም በማለት በአንድ ወቅት የአሜሪካ ነጮች ጥቁሮች ላይ ይፈፅሟቸው የነበሩ ግፎችን የሚያትት ፅሁፍ እንዳነበብኩ አስታውሼ ደግሜ ለማየት ተገደድኩ።
ብዙወቹ ሃብታሙ የዘረዘራቸው ማሰቃያዎች በአሜሪካ ጥቁሮች ላይ በግልፅና በአደባባይ ተፈፅመዋል። አንዳንዶቹ ከዚያም የከፉ ናቸው።ሃብታሙ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ዘሎታል ብየ የምጠራጠረውን ፣ ወያኔ ግን እንደሚፈፅመው ከዚህ በፊት በሌላ ሰው አንደበት ሠምቸው የማውቅ ፣ በአሜሪካ ጥቁሮች ላይ የተፈፀመና ለነፃነታቸው የሚያምፁና ብዙሀኑን ጥቁር የሚያሳምፁ ባሮች ላይ የተፈፀመ ድርጊት ተመለከትኩ።እንግዲህ ወያኔ “ጌታ” የኢትዮጵያ ህዝብ “ባሪያ” መሆኑን አንድ በሉልኝ።
ብዙወቻችን በዚህ ዘመን ያሉ የአሜሪካ ጥቁሮች ፤ በተለይም የራፕ ሙዚቃ አቀንቃኞች የሚያዘወትሩት፤ “MOTHER FUCKER” የሚለዉ ፀያፍ -ቃል እንዲሁ የመጣ ሊመሥለን ይችላል ። ነገር ግን አይደለም።የቃሉ አመጣጥ ነጭ የባሪያ ጌታ የጥቁርን ቤተሰብ ለማሸማቀቅና ስነ-ልቦናዊ ስብራት ደርሶበት ሰጥ-ለበጥ ብሎ እንዲገዛ የልጆች እናት የሆነችን ጥቁር ሴት በልጆቿ ፊት ይደፍራታል።ይህን የሚያደርገው ልጆቹ ደፋሪውን የባሪያ ጌታ “ጌታዬ” እንጅ “አባቴ” ብለው እንዳይጠሩት ጭምር ነው።ታዲያ ይሄንን የባሪያ ጌታ “MOTHER FUCKER” እንጅ እንዴት “አባቴና “ “ጌታዬ” ይበሉት!!

የጥቁሮች ስቃይ በዚህ አያበቃም። የባሪያ ንግድ ተቀዛቅዞ ከአፍሪካ የሚጋዘው ጥቁር መጠኑ ሲቀንስና ከመግዛት ይልቅ ማራባት የሚሻል እንደሆነ ሲረዱ ጥሩ ተክለ-ሰውነትና ቁመና ያላቸውን ወንዶችና መውለድ የሚችሉ ሴቶችን መርጠው ፊታቸውን በመሸፈን ያለምንም ምርጫ ሩካቤ- ሥጋ እንዲፈፅሙ ያደርጏቸው ነበር።እንግዲህ ከእናቱም ከእህቱም ጋር የፈፀመ ይኖራል።ከእናቱ ጋር የፈፀመውን “MOTHER FUCKER” እንጅ ምን ይበሉት!!

ሶስተኛውና ከሁሉም የከፋው ግን ወያኔ በዚህ ዘመን ይፈፅመዋል እየተባለ የሚወራበት ፣ ሃብታሙ በአንደበቱ ሊናገረው የዘገነነው ግፍ ነው ብየ አስባለሁ። በአካልና በስነ-ልቦና የተሻሉ ወንድ ባሮች ብዙሀኑን ባሪያ በሚያሳምፁበት ጊዜ ሞራላቸው ተሰብሮ አንገታቸውን ደፍተው እንዲገዙ ለማድረግ የፈረጠመ ጡንቻ ባላቸው ሌሎች ባሪያወች በብዙሀኑ ፊት እንዲደፈሩ ይደረግ ነበር።ከዚያ በኋላ ጌቶቻቸውን ቀና ብለው የማየት ብቃት አይኖራቸውም።

የኢትዮጵያ ህዝብ ጌታ ነኝ ብሎ የሚያምነው ወያኔ ይሄንን አያደርግም ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው።ሃብታሙ ባይነግረንም ከሌላ ሰው አንደበት ሰምቼው የማውቅ ግፍ ነው።አለመናገር ኋላ -ቀርነት እንጅ ጨዋነት ነው ብዬ አላምንም።ያልተናገርነውን ነገር የጋራ መፍትሄ ልናመጣለት አይቻለንም።የጠላታችንን እኩይ ተግባር በግልፅ በመናገር ህዝባችንን እናንቃ።ጥቅሙ ስለሚበልጥ ይመስለኛል ነጮቹ በየመንገዱ “IF YOU SEE SOMETHING ,SAY SOMETHING” የሚሉት።

ውቢት ኢትዮጵያ ፌስ ቡክ የተገኘ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *