የኦታዋ ካናዳ ነዋሪ ናቸው። ካናዳ ብዙ አመት ኖረዋል። ኮምብሎቻ ነው ተወልደው ያደጉት። ኮምቦላቻ ወሎ አይደለም። ኮምብሎቻ ሃረረጌ። በድረዳዋና በሃረር ከተማ መካከል የምትገኝ ከተማ። አሁን ኦሮሚያ ተብሎ በዘር በተሸነሸነው ክልል ዉስጥ ያለች ከተማ።

እኝህ ሰው፣ ትክክለኛ ስማቸውን ቀይሬ፣ ለዚህ ጽሑፍ ስል አቶ አሸናፊ ብዬ እጠራቸዋለሁ። ከብዙ አመት የካዳና ኑሮ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ይመለሳሉ።፡ካናዳ በቁዩበት ወቅት ትልቅ ደረጃ የደረሱ ሰው ናቸው። “የተወለድኩባት አገር ምን ደረጃ ላይ እንዳለች ሄጄ አይቼ ቀረዉ ዘመኔን፣ ያለኝን ገንዘብና እውቀት እዚያ ማጥፋት እፈለጋለሁ” በሚል ሀሳብ ሁኔታዉን መጀመሪያ ለማየት በሚል ወደ ኮምቦልቻ ያቀናሉ።

የሶማሌ ዳያሌክት ያለው ኦሮምኛ ፣ ኮቱኛ የሚባለውን ልክ እዚያ እንዳለው የአገሬ ሰው ይናገራሉ። አቶ አሸናፊ እዚያ ሲደርሱ አንዳንድ ወጣቶች ከበቧቸው። ስማቸውን ሲናገሩ ወዲያው የወጣቶቹ ስሜት ተቀያየረ። “አማራ እዚህ ምን ሊያደርግ መጣ ? ” በሚል ። እኝህ ሰው አባታቸው የወሊሶ ተወላጅ የነበሩ ፣ አስተማሪ ሆነው ኮምብልቻ ሄደው የነበረ የጨቦ ኦሮሞ ነበሩ። እናታቸው ደግሞ ሻሸመኔ ተወልደው ያደጉ የጤና ባለሞያ ነበሩ። ጉራጌ። እዚያው ኮምቦልቻ ታጋብተው ነው አቶ አሸናፊን እና ሌሎች ልጆቻቸውን የወለዱትና ያሳደጉት። ሆኖም ለነዚህ የኮምቦልቻ ወጣቶች አቶ አሸናፊ “አማራ” ተደርገው ነው የተወሰዱት።

Related stories   በሳሊቫኪርና በሪክ ማቻር መካከል እያገረሸ ያለውን ቅራኔ እየተባባሰ በመምጣቱ በደቡብ ሱዳን አዲስ ግጭት እንዳያገረሽ ተሰግቷል

የነበረው መንፈስ ጥሩ አልነበረም። ወዲያው አቶ አሸናፊን የሚያወቁ አንድ የኮምቦልቻ ነዋሪ ተጠርተው መጡ። ትክክለኛ ስማቸውን ቀይሬ አቶ አብዲ በሚል ስም እጠራቸዋለሁ። ገና ሲተያዩ፣ በኮቱኛ እያወሩ፣ እየተሳሳሙ፣ እየተቃቀፉ ሊላቀቁ አልቻሉም።፡አቶ አብዲ በሕመም ምክንያት በጣም የተጎዱ ስለነበረ፣ አቶ አሸናፊ የጥንት ጓደኛቸውን ሲያዩ አለቀሱ። ወዲያው ተያይዘው ወደ አቶ አብዲ ቤት ሄዱ። ጫማ ወለቀ። ሱሬ ወለቀ። ሽርጥ ተደረገ። ብዙ ጫት መጣ። ሁለቱም እንደ ድሯቸው መጫወትና ማውራት ጀመሩ። ትንሽ ይላቀሱና ፣ ቆይተው ደግሞ ይሳሳቃሉ።

ድንገት በር ተንኳኳ፣ ጠመንጃ የያዙ ወጣቶች የኦህዴድ አክራሪዎች መሆናቸው ነው፣ “ይሄ ሰዉዬ ከየት ነው የመጣው።ፖሊስ ጣቢያ መሄድ አለበት።መጠየቅ አለበት” አሉ። አቶ አብዲ መሬት ላይ ወድቀው መለመን ጀመሩ። “የኛው ሰው ነው። ወዳጃችን ነው” እያሉ እድሜ ዘመናቸውን በኖሩባት ከተማ፣ የጥንት ወዳጃቸውን ለማዳን ያልሆኑት ነገር አልነበረም። እግዜር ረድቷቸው የኦህዴድ ታጣቂዎች “ላንተ ስንል የዛሬን አልፈናል” ብለው እየተሳደቡ ሄዱ። በዚህ ሁሉ ግርግር አቶ አሸናፊ ያዩትን የሰሙትን ማመን አቃታቸው። የእትብታቸው መቀበሪያ የሆንችዋ ኮምቦልቻ፣ እንድልብ ሲሮጡባት፣ ሲፈነጥዙባት የነበረችዋ ኮምቦልቻ ፣ ቀሪ ዘመኔን፣ ገንዘቤን እውቀቴን ለርሷ አጠፋለሁ ያሉላት ኮምቦልቻ በሯን ዘጋችባቸው።

Related stories   “ጣልያኖችም ሆኑ እንግሊዞች ቅኝ ግዛትን ለማስቀጠል ህዝቡን በዘር መከፋፈልን እንደ አንድ ስልት ይጠቀሙ ነበር” -አቶ ታቦር ገረሱ ዱኪ

አቶ አሸናፊ ሳምንት ለመቆየት ሄደው በነጋታው መኪና ተሳፈረው ሄዱ።ከተማዋ ድንበር ላይ ሲደርሱ፣ ሾፌራቸውን አቁም አሉት። መኪናዋ ቆመች። ወጡ። ለጥቁት ደቂቃ ቆም ካሉ በኋላ “ቱቱቱ” ብለው ሁለተኛ ላይመለሱ ምለው ጉዟቸውን ወደ ድረዳዋ አቀኑ።

እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅ፣ ማን ነው ለእረፍት ፣ ለመዝናናት፣ ለኢንቨስትመን.. ብሎ አሁን ሃረር፣ አሰበ ተፊሪ፣ ነቀምቴ፣ አምቦ ..የሚሄደው ? ሰው ሁሉ የሚሄደው ወደ አዋሳ፣ ወደ ባህር ዳር ፣ ወደ ደብረ ዘይት ወደ መሳሰሉት ነው። ትላንት vibrant የነበሩ አሁን ኦሮሚያ በምትባለው ክልል ያሉ ከተሞች(አዲስ አበባ ዙሪያ ካሉት ከነ አዳማና ቢሾፍቱ ከመሳሰሉት በስተቀር) አሁን ሞተዋል። ዘረኝነት የበዛበት አካባቢ በመሆናቸው።

Related stories   “በአጣዬ እና አካባቢው በተፈፀመው ወንጀል ተጠያቂ የሚሆኑ አካላት ለፍርድ ይቀርባሉ” ኮማንድ ፖስቱ

አቶ አሸናፊ ፊታቸው ከኮምቦልቻ እንዳዞሩት ሌላውም ፣ በአገሩ፣ ኢትዮጵያዊ ሆኖ እንደ ባይተዋር፣ እንደ እንግዳ፣ እንደ መጤ የሚቆጠር ከሆነ፣ ፊቱን ማዞሩ የማይቀር ነው። ዘረኝነት የሚያሰባስብ ሳይሆን የሚያራርቅ ነው።

ይሄ የዘር ፖለቲካ ከማንም በላይ የኦሮሞዉን ማህበረሰብ ክፉኛ የጎዳው። የኦሮሞ ወጣቶች ላለፉት 25 የተሞሉትን የጥላቻ መርዝ ከአይምሯቸው ካላወጡ፣ ይመኑኝ ወድቀው ነው የሚቀሩት። እንኳን ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለን ቀርቶ፣ በአለም አቀፍ ደረጃ ሕዝብ ከሕዝብ እየተሳሰረ በመጣበት ወቅት፣ ተመልሰው ወደ middle age የኋላ ቀር አስተሳሰብ መሄዳቸው ትልቅ ጉዳት ነው።

#ግርማ_ካሳ የተወሰደ 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *