ባህርዳር ዩኒቨርስቲ በአራቱም ካምፓሶች በዚህ አመት ብቻ 250 ተማሪወችን አባሯል። ከነዚህ ውስጥ ከ80% በላይ የሚሆኑት አዲስ ተማሪወች ናቸው። እውነት ለመናገር ሆን ተብሎ አይደለም። አሁን ላይ ትውልዱ ዋዥቋል። ተማሪውም መምህሩም በዝሙት እና በሱስ ጦንዝዟል። በተለይ ፖሊ እና ፔዳ ካምፓሶች። ምሽት በየዛፉ ሥር ጎራ ብትሉ ገና ያልበሰሉ እምቦቃቅላ ጥንዶች እንደ እንሥሣ ሢላላሡ ታያላችሁ።

ትናንት መጋቢት 24.2009 ዓ.ም በባህርዳር ፋሲሎ ከፍተኛ ሁለተኛ እና መሰናዶ ት.ቤት የአመቱ የወላጅ መምህር ስብሰባ ተካሂዶ ውሏል። እኔም ተሳታፊ ነበርኩ። ምናባትህ ልትሠራ እንዳትሉኝ። እኔም አንዲት ልጅ አለችኝ። ባይኖረኝስ! ለጉረቤቶቼ ልጆች መሄድ አልችልም? ስለ አማራ ልጆች እንደ አማራነቴ ይመለከተኛል እኮ።
ስብ,ሰባው የምር አሳዛኝ አሥገራሚም ነበር። መምህራን ኡኡ ብለዋል። ምን አይነት ትውልድ መጣብን ብለዋል። በዚህ አመት ምንም ተማሪ እንደሌለ፤ በየክፍሉ ለሽልማት ከቀረቡት ሁለት ሁለት ልጆች በቀር ምንም የሚያልፍ ተማሪ እንደማይኖር አስጠንቅቀዋል።
ስለ ችግሩ ሲጠየቅ ሁሉም ተሠብሣቢ ማለት ይቻላል ሥለ ቃና ፕሮግራም ነበር የተነሣው። በተለይ የገረሙኝን ልንገራችሁ። አንድ አባት “አሁን እዚህ 12ኛ ክፍል ተማሪ አለችኝ። ርሥዋ አምልጣለች። እውቀቱ ቢቀር ባይሆን ስብእናዋ ደና ነው። የካቲት 23 የምትማረው ልጅ ግን የለችም። ሁለመናዋ በቃና ተበክሏል እንዲያው ዝም ብየ ሳያት ሁሉ ነገሯ እዛ ቃና ሚባለው ውሥጥ እንዳለው ዝሙት ነው። በእውነት ምን እናድርግ? የቤታችንን ብንቆልፍ ወይ ብናጠፋ ከጎረቤት ሂደው ያያሉ። በእውነት እናንተ መምራን ትውልድ ቀራጮችም አደላችሁ ምነው ይህንን ቃና ቢስ ፕሮግራም የሚጠፈበትን መንገድ ከሚመለከተው ክፍል ጋር ብትነጋገሩ?”
ሌላ እናት ቀጠለች” ቃና እኮ ባህላችንን ብቻ አይደለም ያጠፋው ዝሙትን እያሥፋፋ ነው። ሰውነትን እያረከሠ ነው። ዛሬ እኮ ህጻናት አፋቸውን ሚፈቱት በዝሙት ሆኗል። በየሽንጉሩ ብትገቡ የአራተኛ ክፍል ህጻናት ኪሲንግ ሲያረጉ ነው ምታገኟቸው። እኔ ቃናም ኢቢሲም ዘግቻለሁ። ልጄም አንድ ነው ለቁጥጥር አያሥቸግረኝም። ቤተክርሥትያን ሥላሥለመድኩት የምለውን ሁሉ ይሠማኛል ይመሥገነው። ሁለት ሦሥት ልጅ ላላችሁ ለእናንተ ይብላኝላችሁ።”
ሌላም ብዙ ተባለ
እኔ ደጉ ግን ደግ ይበላችሁ ብያለሁ። ቃና ሃጣያቱን ማቀንቀን እንደጀመረ ስለ ግምነቱ ብናገር ሠሚ አልነበረኝም። ሆን ተብሎ ባህሉን ሃይማኖቱን ለማጥፋት በአማራኛ የመጣ የፈረንጅ ቀንዳም ጋኔል ነው። የወያኔ እጅ አለበት። ባለአክሲወኖቹም …..
በእውነት ቃና ትውልድ እያመከነ ነው። ቃና ባህል እያጠፋ ነው። ሆን ተብሎ ለመበረዝ ለመከለስ የተፈበረከ ሚዲያ፣ ካልጠፋት መቶ ኢትዮጵያዊ ቋንቋወች ሆን ተብሎ በአማራኛ የመጣ ከያዘ ማይለቅ ነጭ ሰይጣን…
የምር ልንገራችሁ ቀጣይ የሚለቀቁት ፊልሞች ሰይጣንን ሥለማምለክ፣ ገሃዳዊ ወሢብ፣ ግብረ ሠዶም ሌዚቢያ ወይም ሴት ከሤት ወንድ ከወንድ ተመሣሣይ ጾታ ወሢብ፤ ሥለማሥተርቤሽን ወይም ራሥን በራሥ በወሢብ ማርካት፣ ሠይጣንን ሥለማምለክ እግዚአብሔርን ሥለመክዳት የሚሠብኩ ፊልሞች ናቸው።

Related stories   በምናለሽ ተራ ገበያ – ከሰኞ እስከ እሁድ

የፋሲሎ መምህራን ስለ ቃና “ምንም ልንል አንችልም። እንዳላችሁት ትልቁ ችግር ቃና ነው። በየክፍሉ ሥለ ቃና ፊልሞች ነው ሚወራው። ላይብራሪ ውሥጥ በሹክሹክታ ሥለቃና ነው ሚወራው። መምህሩ እያሥተማረ የጎንዮሽ ወሬ ሥለ ቃና ነው ሚወራው። በእውነቱ ይህ ከላይ የመጣ ችግር ነው። ምንም ልናደርግ አንችልም። ቤቻላችሁት መጠን ቤተሰባችሁን ጠብቁ…” ነበር ያሉት …እና እባካችሁ እህቶች ወንድሞች እናቶች አባቶች ሁላችሁ ቃናን ከቸናል ገበያ ልናጠፋው አንችል ይሆናል። ግን ከልባችን እናጥፋው። በቤት በጎረቤት በሰፈር ቃናን እናጥፋ ባለማየት በመቆለፍ ዲአክቲቭ በማድረግ ቃናን እናጥፋ።

Related stories   የዓለም ጤና ድርጅት ለቻይናው ክትባት ይሁንታውን ሰጠ
Degu Bekele Alemu  

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *