ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

የበጋዉ መብረቅ – ጃገማ ኬሎ በ96 ዓመታቸው አረፉ

jagma 2ሌተናንት ጄነራል ጃገማ ኬሎ ከውልደታቸው እስከ እለተ ሞታቸው ለኢትዮጵያ ልዩ ባለውለታ ነበሩ፡፡ ሌተናንት ጄነራል ጃገማ ኬሎ ለሀገራቸው ለኢትዮጵያ ብሎም ለመላው ዓለም ሕዝቦች የተሻለ ሕይወት ክብርና እርካታ እንዲኖራቸው…ሕዝቦችን ለማግባባትና ለማቀራረብ የሚመኙ እና የሚሰሩ ነበሩ…..ጀግኖች እና የሀገ9lር ባለውለታወች በሕይወት ኖረውም ሳይኖሩም በሰሩት ሥራ ሁል ጊዜ ሲታወሱ ይኖራሉ፡፡ነፍስ ይማር
* ሌ/ጀ/ጃገማ ኬሎ የተወለዱት በጥር 20 ቀን 1913 ዓ.ም ነው:: ለቤተሰባቸው የመጨረሻ ልጅ ቢሆኑም ከሁሉም ጎበዝ ብርቱ ነበሩና አባታቸው የቤተሰቡ አለቃ አደረጓቸው::

* አባታቸው ጃገማ ገና ሳይወለዱ ለወላጅ እናታቸው ‹‹ልጃችንን ስሙን ጃጋማ ብየዋለሁ›› በማለት ጠሯቸው::

* “ጃገማ” የአባታቸው የፈረስ ሥም ሲሆን በኦሮምኛ ሀይለኛ ማለት ነው:: ሌ/ጀ/ ጃገማ እስኪወለዱ ድረስ የፈረሳቸውን ሥም የሚሰጡት ሁነኛ ልጅ አላገኙም ነበር::

* የጣልያን ጦር የአድዋ ላይ ሽንፈቱን ሊወጣ ጦሩን እጅግ አግዝፎ ከ40 ዓመት ዝግጅት በኋላ በ1928 በድጋሚ ሀገራችንን ወርሮ ሕዝብ ሲፈጅ ሀገሩን ሊታደግ ሁሉም በየፊናው ሲራወጥ በ15 ዓመት ዕድሜ የአባታቸውን ጀብድ ሊደግሙ በዱር ዘምተው ጠላትን አርበድብደዋል። በዚህም “የበጋ መብረቅ” ተብለው ተሰይመዋል።

Related stories   የቻይናው ሮኬት ስብርባሪ በኢትዮጵያ ቢወድቅ ምን ዓይነት የጥንቃቄ እርምጃዎች ሊወስዱ ይገባል?

* ሌ/ጀ/ ጀገማ ፤ ከጣልያን ጋር 5 ዓመት ሲዋጉ አንድም ቀን ድል ሆነው አያውቁም:: ጥይት ሲያልቅባቸው ብቻ ቦታውን ለቅቀው ይሄዳሉ:: ጥይት መልሶ ለማግኘት እንዴት ያደርጉ እንደነበር እንዲህ ብለዋል፡፡ <<ጥይት ሲያልቅብን ማታ ምሽግ ላይ እንተኩሳለን:: አሥራ አምስት ተኩሰን ከሆነ ሃያ ተኩሻለሁ ይልና አምስቱን ይሸጣል:: ጥይቱን የሚሸጡት ባንዳዎች ናቸው>>

* ሁለተኛ የዓለም ጦርነት ጊዜ እንግሊዝ ጣልያን ከአፍሪካ እንድታስወጣ ተወሰነ:: ስለዚህ ወቅት ጃገማ ኬሎ እንFB_IMG_1491685981732ዲህ ብለዋል፤ <<ይህ ውሳኔ ኢትዮጵያንም ይመለከታልና ከንጉሡ ጋር ሆነው የእንግሊዛውያን ወታደሮች ሲመጡ የከዳውም ባንዳ እየተመለሠ ጣሊያን ተባረረ::

* ከዚያ በኋላ ንጉሡ ተመልሠው ዙፋናቸው ላይ ቢቀመጡም ጎንደርና ጅማ አልተለቀቁም ነበርና የጎንደሩ ይቀመጥ መጀመሪያ የቅርቡን እናስለቅቅ ተብሎ ወደ ጅማ ሲሄዱ ጀኔራል ጋዜራል የግቤን ድልድይ ቆርጦ መከላከል ጀመረ::

Related stories   በምናለሽ ተራ ገበያ – ከሰኞ እስከ እሁድ

* በዚህ ጊዜ ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ያውቁኝ ነበርና ለጃንሆይ “ጃገማን ቢያዙልኝ በአምቦ መንገድ ሄዶ በኋላ ይቆርጥልኛል” በማለታቸው ጃንሆይ ከደጃች ገረሱ ጋር እንድትዘምት ብለው ደብዳቤ ላኩልኝ:: እኔ በወቅቱ 3500 ወታደኖች ነበሩኝ፡ ፡ መሣሪያውን ግማሹን ማርኬ ግማሹን ገዝቼ ያከማቸሁት ነውና መሳሪያ የመንግሥት ነው ስለተባለ ሲፈልጉ መሣሪያውን ይውሰዱ ብዬ እምቢ አልኩ::

* ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድሌ የተባሉ የውስጥ አርበኛ ያውቁኝ ነበርና ለጃንሆይ “ሕፃን የሚያምር ልጅ ነው እንዴት ከሞት ወደ ሞት ይልኩታል፡፡ ያሰናብቱት ጦሩን ቢያዩለትም መልካም ነው” ብለው ተናገሩ::

* ጃንሆይም “እውነት ነው ተሣሥተናል እናያለን” አሉ:: “ጦርህን መጥተን እናያለን ተዘጋጅተህ ጠብቅ ፉከራም ታሰማለህ” ብለው መልዕክት ላኩብኝ፡፡ መጡ:: እኔም ታወር ሰርቼ ጠበኳቸው:: ፎክር ተብያለሁና ፉከራ ባልችልም፤

jagma 3

‹‹አባቱ ኦሮሞ እናቱ ኦሮሞ

ግዳዩን አስቆጠረ ከምሮ ከምሮ›› ብዮ ፎከርኩ፡፡ ከዚያ በኋላ ምሣ አብረን በልተን ከእርሳቸው ጋር አዲስ አበባ ቤታቸው መጣሁ:: 25.000 ብር እና የወርቅ ሰዓት፤ ሙሉ ገበርዲን ሱፍ ሰጡኝ:: ከዚያ ደጃች ገረሱ ጋር ዘምቼ አጋሮ ወርጄ ድልድዩን ዘጋሁት:: መኮንኖቹ ተማረኩ:: ጋዚራም እጁን ሰጠ:: ጠቅላላ 600 እስረኛ ተቀብዬ ጦርነቱ አበቃ>>

Related stories   የበልግ ዝናብ በአንዳንድ አካባቢዎች ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ

* የ ሌተናት ጄኔራል ጃገማ ልጆች እንደ እድሜያቸው ቅደም ተከተል፤ አቶ ሰለሞን ጃገማ ፤ ጸዳለ ጃገማ ፤ የትምወርቅ ጃገማ፤ ሸዋዪ ጃገማ፤ ብሩክታዊት ጃገማ፤ እና ምህረት ጃገማ ናቸው።

* ሌ/ጀኔራል ጃገማ ኬሎ በአጼ ኃይለሥላሴ ዘመን ከነበሩት ሌ/ጀኔራሎች መካከል በሕይወት የሚገኙት ብቸኛው ጀኔራል ነበሩ።

* አንድ ወንድና አምስት ሴት ልጆች፣ አምስት የልጅ ልጆችና አራት የልጅ ልጅ ልጆችን አፍርተዋል፡፡

* በሕይወት ሳሉ የሕይወት ታሪካቸውን ጽፈው አዘጋጅተዋል።

* አስከሬናቸው በጦር ኃይሎች ሆስፒታል ይገኛል። የክብር አሸኛኘትም ይደረግላቸዋል።

Mannie Wollele  – ምሥጋና Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0
Read previous post:
“ኢጂኣኦ” – የቻይናና አህያ ፍቅር – ቻይና በዓመት 4 ሚሊዮን የአህያ ሌጦ ትፈልጋለች

“አህያ ሲጠፋ እህል ማን ሊሸከም ነው? ሴት?!” የአህያ ሥጋና ቆዳ ንግድ እንደ ህገወጡ የአውራሪስ ቀንድ...

Close