ግዜው 1877 ነበር ። ዝነኛው ዶክተር ጆሴፍ ቤል፣ ስኮትላንድ ውስጥ በሚገኘው ትልቅ ሆስፒታል በሕክምና ተማሪዎች ተከቦ ተገኝቷል ። ከተማሪዎቹ መሐል አርተር ኮናን ዶይል የሚባል የሀያ ሁለት አመት ወጣት ይገኝበታል ።

የመጀመሪያ ህመምተኛቸውን ሲጎበኙ ዶክተር ቤል ” ይህ ሕመምተኛ ግራኝ የሆነ የጫማ አዳሽ ነው።” ብለው ለተማሪዎቹ ተናገሩ። አርተር ኮናን ዶይልን ጨምሮ ሁሉም ተማሪዎች ተደነቁ።እንዴት በመጀመሪያ ግንኙነት ፣በቅፅበት እይታ ስለ አንድ ሰው ስራና ግራኝነት መናገር ይቻላል? የሁሉም ጥያቄ ነበር።

“ይታያችኋል ተማሪዎች ፣የህመምተኛው ሱሪ ልክ እንደ ጫማ ሰፊዎች ከጉልበቱ በላይ ተበልቶ አልቋል፤ ይህም የሚሰፋትን ጫማ የሚያሳርፉበት ቦታ ስለሆነ ነው። ግራኝ መሆኑን ያወቅኩት ደግሞ የግራ እግር ሱሪው ብቻ ስለተበላ ነው።”

ታዲያ ይህ የዶክተር ቤል ችሎታ ዘወትር እንደተገለጠ ነው።ዶክተር ቤል አንድ እንግዳ ሰውን አግኝቶ በአፍታ ስለ ሰውዬው ባህሪ ፣ ስራ ወዘተ መናገር ይችላል ።

ይህ ከሆነ 9 አመታት አለፉ። ዶክተር ኮናን ዶይል ግን የዶክተር ቤልን ተሰጥኦ እንዲህ በቀላሉ የሚረሳው አልሆነም ። ዶክተሩ፣ ብዙዎቹ የማያስተውሉትን ትናንሽ ፍንጮች ፈልፍሎ የሚመለከትበት ልዩ መነፅር ነፍሴን ማረካት ብሏል ዶይል ኋላ። ስለዚህ ዝነኛውን የወንጀል ክትትል ታሪክ ለመፃፍ ተነሳ።

ሼርሎክ ሆልምስ እንዲህ ተወለደ።
ከዚህ በኋላ ያለው ታሪክ የስኬት ነው።

ሼርሎክ ሆልምስ ብዙ ሙቪ አዳፕቴሽን ተሰርቶለታል።
ለምሳሌ Sherlock Holmes
Sherlock
Elementary

በተዘዋዋሪ ተፅእኖ ያረፈባቸው
House, M.D.
The Mentalist

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *