ወንድማችን ሀይለ ገብርኤል “የኢትዮጵያ ሐገራዊ ንቅናቄ ተስፋና ሥጋት” በሚል ርእስ የ“አገር አድን ንቅናቄ”ን ለማሳበጥ የአማራን ትግል አጉብጦ አገኘነው፡፡ በመሰረቱ ስለአገር አድን ንቅናቄው ከተመሰረተበት ሰሞን ወዲህ ተሰምቶም ታይቶም አይታወቅ፡፡ የጤና ነው!!? ለመሆኑ በአገር አለ? ወንድማችን ሀይለገብርኤል የአማራን ድርጅቶች ለማሳነስ የተጠቀምክበት ከአማራ ባህል ውጭ የሆነ ስድብ የሚሳደቡ ሰዎች በአማራው እንቅስቃሴ ውስጥ አሉ የሚለው ነው፡፡ እዚህ ላይ መሰረታዊ ስህተት ሰርተሀል፡፡ ማናችንም ስድብ አንፈልግም፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ተሳደቡ ብሎ ጠቅላላ እንቅስቃሴውን እንዲህ ማሳነስ ግን ተገቢ አይደለም፡፡ ቢሆን እንኳ 50 አመት ሙሉ የስድብ ፕሮፓጋንዳ ተከፍቶበት የኖረ ህዝብ ልጆች ለሰዳቢዎች አጸፋ ቢመልሱ የሚገርም አይሆንም፡፡

Related stories   የአውሮፓ ህብረት የይስሙላ ምርጫዎች ሲታዘብ ቆይቶ አሁን አልታዘብም ያለበትን ምክንያት ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያሳውቅ ተጠየቀ

በዛ ላይ ስንት ስድብ የማያውቅ ህዝብ የሚሳተፍበትን እንቅስቃሴ ተሳዳቢ ብቻ አድርጎ ማሳየት ደግም አይደለ፡፡ እንደገናም የአማራ ድርጅቶች በአገር አድን ንቅናቄው ካልተሳተፉ ድል የለም የሚል ይዘት ያለው ሀሳብ አስፍረሀል፡፡ እግዲህ ትብብርን የሚጠላ የለም፡፡ መተባበር መልካም ነው፡፡ አማራው ብቻውን ማሸነፍ የሚችል መሆኑንም ማስመር መረሳት የለበትም፡፡ የአማራ ትግል የሚተባበረው ከእግዲህ በኋላ ለራሱ ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኘው ብቻ ነው፡፡ የአማራ ህዝብ ህልውና፡ ደህንነት፡ መብትና ጥቅም የሚለውን መርህ አትርሳው፡፡ በዛ ነው የምንመራው፡፡

Related stories   “ጣልያኖችም ሆኑ እንግሊዞች ቅኝ ግዛትን ለማስቀጠል ህዝቡን በዘር መከፋፈልን እንደ አንድ ስልት ይጠቀሙ ነበር” -አቶ ታቦር ገረሱ ዱኪ

ያለፈው የሞኝነት ዘመን አልፏል፡፡ ጽሁፍህ ላይ ኢትዮጵያየ ወይም ሞት የሚል ቃና ይኸለዋል፡፡ ዌል እንግዲህ የአማራው እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ችግር የለበትም፡፡ ለጥያቄ የሚቀርብም አይደለም፡፡ የአማራው እንቅስቃሴ ዋና ችግሩ ከአንድነት ፖለቲካ አራማጁ ጋር ነው፡፡ የአንድነት ጎራው የአማራ ማጥመጃ ባህርና መቃጥን ሆነ ነው ችግራችን፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ አንድነት እና የአንድት ጎራውን ፖለቲካ በማደበላለቃችሁ ነው የእኛውን የአማራ ፖለቲካ መረዳት ያቃታችሁ፡፡ እናም ሁለቱ እንደሚለያዩ ተረዱ፡፡ በመጨረሻም ይሄ አንተ የምትሳተፍበት ንቅናቄ ለአማራ እንቅስቃሴ እውቅና ሰጠም አልሰጠ የእኛ ጉዳይ አይደለም፡፡ የእኛ ጥረት ማንኛውም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄድ እንቅስቃሴ የአማራውን ይሁንታ ካላገኘ ዋጋ እንደማይኖረው በተግባር ማሳየት ነው፡፡ እኛም ማንም እንዲያውቀን ደጅ አንጠናም፡፡ ሌላው እኛ እንድናውቀው ደጅ መጥናቱ ግን አይቀሬ ነው፡፡ ጊዜ ያሳየናል፡፡ የአማራ ሀይል የእሳት አሎሎ ነው፡፡ እሱን የያዘ ህግን ያሰምራል፤ በዛችም ህግ የተቀረው ይመራል፡፡

Related stories   “የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች አለመምጣት የሚያጎለው አንዳችም ነገር የለም፤ እኛም አንጠብቃቸውም” ፕሮፌሰር በየነ

አመሰግናለሁ፡፡

Mesganaw Andualem

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *