ከ50 ዓመት በላይ እድሜ ያለው የአቃቂ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል

ከግማሽ ምእተ ዓመት በላይ እድሜ ያለው የአቃቂ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው ፋብሪካው ሰራተኞች የብረታ ብረት ማምረቻው በአሀኑ ወቀት ሙሉ በሙሉ ምርት ማቆሙን ይናገራሉ። የአቃቂ ብረታ ብረት ኢንደስትሪ መሰረታዊ የሰራተኞች ማህበር አባላት ኢንዱስትሪው ባለፉት 50 ዓመታት የቤት ክዳን ቆርቆሮ እና የውሃ ትቦ በማምረት በዓመት እስከ 100 ሚሊየን ብር ትርፍ ያገኝ እንደነበር ያስታውሳሉ።

ኢንዱስትሪው በ2002 ከመንግሰት ወደ ግል በተዛወረ የመጀመሪያዎቹ ዓመታትም ከፍተኛ ትርፍ በማግኘት ችሎ እንደነበረ ነው ሰራተኞቹ የሚናገሩት። ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን ፋብሪካው ቀደም ሲል ከነበረዉ ይዞታ በማሽቆልቆል ሙሉ በሙሉ ምርት ወደ ማቆም ደረጃ ደርሷል ሲሉም ይናገራሉ። ይህም ሰራተኛው ማግኘት ያለበት ተገቢውን ጥቅማ ጥቅም እንዳያገኝ ምክንያት መሆኑን ነው ሰራተኞቹ የሚናገሩት።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በስፍራው ባደረገው ምልከታም፥ ከ50 ዓመት በላይ የማምረቻ ማሽኖች ድምፅ ይሰማበት የነበረው ስፍራ በፀጥታ ተሞልቷል። ጣራ የሚያለብስ ቆርቀሮ ሲያመርቱ የነበሩ ማሽኖችም ስራ ፈተው ሸራ ለብሰው መቀመጣቸውን ታዝቧል።

የኢንደስትሪው ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ አበበ ፍብሪካው ምርት ማቆሙንም የተናገሩ ሲሆን፥ ለዚህም የውጭ ምንዛሬ እጥረትን በምክንያትነት አስቀምጠዋል። እንደ ስራ አስኪያጁ ገለፃ፥ ለኢንደስትሪው ስራ ማቆም የግብኣት እጥረት አንዱ ምክንያት ነው፤ ግብኣቶቹን ለመግዛት የሚያስፈልገውን የውጪ ምንዛሬ ማቅረብ ያለቻለውን መንግስትንም የችግሩ አካል አድርገዋል።

የብረታብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስትቲዩት በበኩሉ ፋብሪካው ካለፈው ዓመት ጀምሮ የውጪ ምንዛሬ ጠይቆ አያውቅም፤ ችግሩ የራሱ ነው የሚል ምላሽ ሰጥቷል። በኢኒስቲቲዩቱ የብረታ ብረት እና ቴክኖለጅ ልማት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ አስፋው፥ የኢንደስትሪው ችግር ስራ አስኪያጁ እንዳሉት የውጭ ምዝሬ እጦት አይደለም ይላሉ።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባደረገው የማጣራት ሂደት ያገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ኢንደስትሪው የውጪ ምንዛሬ ገጠመኝ የሚለው ከሰኔ ወር 2008 ጀምሮ ነው። ኢንስቲቲዩቱ ደግሞ በፋብሪካው እና በኔ መካካል የነበረው ግንኙነት ከጥር 2008 ጀምሮ ተቋርጧል ይላል።

እኛም ከዚህ ምላሽ በመነሳት ለቃሊቱ ብረታ ብረት ኢንደስትሪ ስራ አስኪያጅ የውጪ ምንዛሬ ሳትጠይቁ እንዴት የውጪ ምንዛሬ እጦት ለምርት ማቆም ዳረገን ትላላቸሁ የሚል ጥያቄ አቅርበናል። እንደ ስራ አስኪጁ ምላሽ ከሆነ፥ ፋብሪካው ምረት ማምረት ያቆመው በራሱ ውስጣዊ ችግር ምክንያት ነው። ፋብሪካው በአጭር ጊዜ ወስጥ ወደ ቀድሞ የማምረት አቅሙ ይመለሰል ሲሉም የኢንደስትሪው ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ አበበ ተናግረዋል።

የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲቱት ግን የአቃቂ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ከገባበት ችግር ለመውጣት ከኢንስትዩቱ ጋር ያቋረጠውን ግንኙነት በማስቀጠል ለችግሮች መፍትሄ ማስቀመጥ የሚል መክረ ሃሳብን አስቀመጧል። ኢንዱስትሪው በትክክል ችግሮቹን ካስቀመጠም ኢንስቲትዩቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቋል።

ዜናው የፋና ነው – ሚያዚያ 9፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  በተመስገን እንዳለ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *