በኦሮሚያ፣ በአማራና በደቡብ ክልል ተቀስቅሶ በነበረው ተቃውሞ ምክኒያት በኢትዮጵያ የተከሰተውን የሰው ሞት፣ አካል መጉደልና ንብረት መጥፋት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዛሬ ያወጣው የምርመራ ሪፖርት “ተቋሙ ገለልተኛ ባለመሆኑ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም” ሲሉ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና የብዙሃን መገናኛ ኃላፊዎች ገለፁ።

በሪፖርቱ በአባባሽነትና በ”ዐመፅ” ጠሪነት ከተጠቀሱት የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ አንዱ ሲሆን ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ሙላቱ ገመቹ ” ራሱ መስካሪና ራሱ ፈራጅ ነው። ቀጪውም፣ መርማሪውም ሁሉንም ያደረገው እርሱ ነው። ይሄ ትክክለኛ ሪፖርት ነው ብለን አንቀበለውም” ብለዋል።

የሰማያዊው ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሸዋስ አሰፋ፤ “ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም የገለልተኝነት ጥያቄ የቀረበበት ነው። ለአንድ አካል ያደላ እና ለፓርቲ የቀረበ አቋም ያለው ነው” ካሉ በኋላ በእንዲህ ያለ አካል የቀረበ ሪፖርት ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም ብለዋል። የኦሮሞሚያ ሚዲያ ኔትወርክ እና የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴቭዥን ኃላፊዎችም ምላሽ ሰጥተዋል።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *