ነገሩ ለአንዳንዶቻችሁ እውነት ላይመስል ይችላል። ኧረ እንደውም ቀልድ ሊመስላችሁ ይችላል! እኔ ግን በጦላይ የተሃድሶ ስልጠና ላይ አጋጥሞኝ የነበረ፣ ዛሬ የኦሮሚያ ቴሌቪዢን ስመለከት ጉዳዩን በድጋሜ እንዳነሳው አድርጎኛል። በጦላይ የተሃድሶ ስልጠና ላይ “የክልል መንግስታት በክልሉ የመሬት ይዞታ ላይ በራሳቸው የመወሰን ስልጣን አላቸው ወይስ የላቸውም?” የሚል የመወያያ ሃሳብ ተነስቶ ነበር። ያው እንደተለመደው 25 ሰልጣኞች እና አንድ ከፌዴራል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የመጣ አሰልጣኝ (የፌዴራል ፖሊስ አባል ነው) ከዛፍ ጥላ ስር ተቀምጠን እየተወያየን ነው።

በዙሪያዬ ያሉት በሙሉ ከላይ በተነሳው ጥያቄ ላይ ሲጨቃጨቁ እኔ ከዛፉ ቅርንጫፍ ላይ በሚያስቀና ቅንጅት ጎጆ የሚሰሩ ወፎችን በተመስጦ እየተመለከትኩ ነበር። የውይይት ሰዓቱ ሊገባደድ አከባቢ አሰልጣኙ “ስዩም በዚህ ላይ ምን ትላለህ?” አለኝ። ልክ ከእንቅልፉ አንደ ነቃ ሰው አይኔን እያሻሸሁ “ጥያቄው ምን ነበር? እስኪ ድገምልኝ” አልኩት። “የክልል መንግስታት በክልሉ የመሬት ይዞታ ላይ በራሳቸው የመወሰን ስልጣን አላቸው ወይስ የላቸውም?” ብሎ ጥያቄውን በድጋሜ አነበበልኝ።

እኔም ታዲያ “እንዴ…ይሄ’ማ ምን ጥያቄ አለው። በሕገ-መንግስቱ መሰረት እያንዳንዱ ክልል ራሱን በራሱ የማስተዳደር ስልጣን አለው። ይህ ማለት የክልል መስተዳደሮች በራሳቸው ጉዳይ ላይ የመወሰን

Related stories   ኢትዮጵያን የምታለቅሰው በ"መሪዎቿና በውድ ልጆቿ" ነውና !! ጆሮ ያለው ይስማ!!

“ሉዓላዊ” መብት አላቸው። ስለዚህ፣ ለምሳሌ የኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደር በክልሉ የመሬት ይዞታ ላይ በራሱ የመወሰን ስልጣንና መብት አለው” ብዬ በእርግጠኝነት መለስኩለት። የእኔ ምላሽ አሰልጣኙ ለሁለት ሰዓት ያህል ከሌሎቹ ሰልጣኞች ጋር ያደረገውን ክርክር ከንቱ አደረገው።

ለካስ ለአሰልጣኞች በተሰጠው የስልጠና መመሪያ መሰረት “የክልል መንግስታት በክልሉ የመሬት ይዞታ ላይ በራሳቸው የመወሰን መብት ወይም ቀጥተኛ ስልጣን የላቸውም” የሚል ኖሯል። “እና ታዲያ ራስን በራስ የማስተዳደር ትርጉምና ፋይዳ ምንድነው?” ስላቸው፣ “አይ…የክልል መንግስታት በመሬት ይዞታ ላይ ያላቸው ስልጣን ከፌዴራሉ መንግስት “በውክልና” የተሰጠ ነው” አሉኝ። የተሃድሶ ዋና አስተባባሪ የነበሩት ጄኔራል (የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ ናቸው) ይሄንኑ ደግመው…ደጋግመው ሊያስረዱኝ ሞከሩ። እኔ ግን ፍፅሞ ሊገባኝ አልቻለም።

Related stories   የምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ አቅል ያጣ ፍላጎት ግን ምንድን ነው!?

ዛሬ ጠዋት በኦሮሚያ ቴሌቪዥን ላይ በእንግድነት ቀርበው የነበሩት የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ “የአህያ ቄራ በቢሾፍቱ ከተማ ላይ እንዲገነባ ፍቃድ የተሰጠው መቼና በማን ነው?” በሚል ከጋዜጠኛው ለቀረባላቸው “የኢንቨስትመንት ፍቃድ የተሰጠው በ2005 ዓ.ም እንደሆነና ፍቃድ ሰጪው የፌዴራሉ መንግስት መሆኑን ገለፁ። የእኛ ድርሻ የመሬት ካርታና ፕላን መስጠት ብቻ ነው” ብሏል።

በመቀጠል ጋዜጠኛው “ቢሾፍቱ እኮ የኢሬቻ በዓል የሚከበርባት የአምልኮ ቦታ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ የእምነትና ባህል ማዕከል በሆነች ከተማ ላይ እንዴት ነው የአህያ ቄራ እንዲገነባ የተፈቀደው?” የሚለውን ጥያቄ አስከተለ። የከተማው ከንቲባ ልክ “እሱ የእኛም ጥያቄ ነው!…” እንዳለ መብራት ጠፋ።

Related stories   የምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ አቅል ያጣ ፍላጎት ግን ምንድን ነው!?

እና እላችኋለሁ፣ በጦላይ የተሃድሶ ስልጠና ላይ ያልገባኝ ነገር በዛሬው ቃለ-ምልልስ በደንብ ገባኝ። የኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደር በክልሉ የመሬት ይዞታ ላይ በራሱ የመወሰን መብት ወይም ቀጥተኛ ስልጣን የለውም። የአህያ ቄራ እገነባለሁ ብሎ ለመጣ የውጪ ባለሃብት የኢንቨስትመንት ቦታ ቢሾፍቱ እና አሰላ መርጦ ይሰጣል።

እኔ የምለው…ደቡብ ውስጥ አህያ በብዛት የሚገኝበት ቦታ የት ነበር? ሀድያ? ወላይታ? አላባ? … ”ብቻ ደቡብ ውስጥ የሆነ አከባቢ ነፍፍፍ አህያ አለ” አሉ…. የአህያውን ስጋና ቆዳ ወደ ውጪ ለመላክ ደግሞ ከቢሾፍቱና አሰላ ይልቅ ጅግጅጋ እና መቐለ ተመራጭ ናቸው።

ስዩም ተሾመ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *