ዛጎል ዜና – ሰሞኑን የኦሮሚያ ክልል በህገ መንግስቱ መሰረት ከአዲስ አበባ ማግኘት የሚገባውን ልዩ ጥቅም አስመልክቶ በመንግስት ተዘጋጅቶ ቀረበ በሚል የተሰራጨው ረቂቅ አዋጅ ሃሰተኛ መሆኑንን መንግስት አስታወቀ። በተመሳሳይ ግን ክልሉ ማግኘት የሚገባውን ልዩ ጥቅም አስመልክቶ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተመልቷል።

[youtube https://www.youtube.com/watch?v=DMoY06bp_q0&w=640&h=360]

ኢኤንኤን ዛሬ ባሰራጨዋ ዘገባ እንዳመለከተው ተሰራጨ ሰለሚባለው ሰነድ የተወካዮች ምክር ቤት የህግ ቋሚ ኮሚቴ የሚያውቀው ነገር የለም። ሰነዱ ከተሰራጨ በሁዋላ ዛጎልን ጨምሮ በርካታ የደረ ገጽ ጋዜጦች አስተጋብተውታል። ጉዳዩ በከፍተኛ ደረጃ በማህበራዊ ገጾች መነጋገሪያ ከመሆኑም በላይ ቅሬታም ያስከተለ ጉዳይ ሆኖ ነው የሰነበተው።
አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ ተጠሪነቷን ለኦሮሚያ ክልል የሚያደርገውን ” ፊንፌኔ /አዲስ አበባ” በሚል ስያሜ እንድተጠራና በክልሉ የኦሮሞ ተወላጆች ብቻ ያለመፈናቀል ብቸኛ መብት የሚያጎናጽፈው ሰነድ ከኦሮሚያ ክልል የወጣ እንደሆነ ነበር ሲገለጽ የነበረው።
ለመንግስት ቅርብ የሆኑ ወሬዎችን ቀድሞ በማግኘት የሚታወቀው የሆርን አፌርስ “According to sources in the government, the draft legislation was prepared and tabled by Oromia’s ruling party OPDO/EPRDF to the federal leadership about two months ago.” በማለት ሰነዱ በኦህዴድ አማካይነት ተዘጋጅቶ ከሁለት ወር በፊት ለፌደራሉ አመራር መቅረቡን የመንግስት ምንጮቹ እንደነገሩት ጠቅሶ Monday, May 1, 2017 @ 6:31 am ዘግቦ ነበር።
ኢኤንኤን ዛሬ እንዳለው አቃቤ ህግ፣ ኦሮሚያ ክልል፣ የተወካዮች ምክር ቤት የህግ ኮሚቴ ሁሉም አያውቁትም። ሰንዱን አስመልክቶ የኦሮሞ ሚዲያ ኔት ዎርክ ሃላፊ ጁሃር መሐመድና አቶ እስቅኤል ” ሰንዱ ለኦሮሞ ጥያቄ ምላሽ የሰጠ አይደለም” በማለት ሲያጣጥሉት ነበር። አያይዘውም ትግሉ እንደሚቀጥል ሲያስረዱ ነበር። ህገ መንግስቱን የጣሰ እንደሆነም ሲያመላክቱ ነበር።
ረቂቅ አዋጅ ተብሎ የቀረበው ሰነድ ህወሃት የአማራና የጉራጌ ብሄር አባላትን ከአዲስ አበባ ለማፈናቀል ያዘጋጀውና ይህም ድርጅቱ ሲጀምር ጀምሮ የተያዘው ኢትዮጵያን የመበታተን አጀንዳው አካል እነድሆነ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ተወስቷል። ጉዳዩ የብሄር ፖለቲካ ጣጣው ውጤት በመሆኑ ሃዘናቸውን የገለጹም ነበሩ።
ሰፊ የመከራከሪያ ጉዳይ በሆነው ረቂቅ ላይ መንግስት ማብራሪያ መስጠቱ አግባብ ቢሆንም መዘግየቱ አሁንም ጥርጣሬን ፈጥሯል። አንዳንዶች እንደሚሉት ሆን ተብሎ የሰውን ስሜት ለመለካት የተዘጋጀ መሆኑንን ነው። ” ህወሃት አንድ ነገር ሲያስብ አስቀድሞ ማስወራትና የህዝቡን ስሜት አይቶና አዋዝቶ የሚፈልገውን የማድረግ ልምድ አለው” ሲሉ አስተያየት የሰጡ አሉ።

 የኢኤንኤን ዜና ማስፈንጠሪያ እነሆ።
https://www.youtube.com/watch?v=CUt4bV9FjYs&feature=push-u-sub&attr_tag=aPPgVCoMbMN4_jWj-6

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *