Bilderesultat for merera” …ለሁላችንም የምትሆንና በእኩልነት የምታስተናግደን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትፈጠርና ነፃ የፍትህ ሥርዓት በሀገራችን እንዲሰፍን ላለፉት ሃያ አምስት አመታት በመታገሌ መከሰሴ አንሶ የአገሪቱ ፓርላማ አባል የነበርኩ ሰው ለተራ ወንጀለኛ የሚፈቀድ የዋስ መብት በመከልከሌ የተሰማኝ ጥልቅ ሀዘን ፣ ለራሴ ብቻ ሳይሆን እኛም ሆን ልጆቻችን በሰላም ይኖሩበታል ለምንለው መከረኛ ሀገራችንና አላልፍለት ብሎ ሲታመስ ለሚኖር መከረኛ ሕዝባችን ጭምር መሆኑን እንዲታወቅልኝ ነው ” ዶክተር መረራ 

ዛጎል ዜና – የዶከተር መረራ ክስ አብረዋቸው ከተከሰሱት ከእነ ዶከተር ብርሃኑ ነጋና ጁሃር መሃመድ ተነጥሎ ሊታይ እንደማይችል ጠቅሶ ዓቃቤ ህግ ምላሽ መሰጠቱን የመንግስት መገናኛዎች ዘገቡ። ፍርድ ቤቱ ለብይን ለግንቦት 25 ቀን 2009 ቀጠሮ ሰጠ።
ዶክተር መረራ ላቀረቡት የመቃመሚያ መልስ ከሳሽ አቃቤ ህግ የበኩሉን እንዲል የተቀጠረው ለሚያዚያ 26 ቀን 2009 ነበር። የፈደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በሰጠው ቀጠሮ መሰረት ዓቃቤ ህግ ባለ አምስት ገጽ መቃወሚያ አቅርቦ ነው የተመሰረተው ክስ ከእነ ዶከተር ብርሃኑ ነጋና ጁሃር መሃመድ ጋር ተነጥሎ ሊታይ እንደማይችል የሞገተው።

Related stories   ምርጫውን ለማደናቀፍ ያሴሩ አካላት ህልማቸው አይሳካም – አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

https://zaggolenews.com/2016/12/06/shifting-the-peaceful-struggle-in-to-extremists/
ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ባቀረበው መልስ በዋናነት ያሰፈረው ” የጋራ ግብ፣ አላማና ግንኙነት ያላቸው በመሆኑ ክሱ ሊነጠል አይገባም” ብሏል። አክሎም ተከሳሽ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መተላለፋቸውን አመልክቷል። የዶክተር መረራ መቃወሚያ የወንጀል ሰነ ስርዓት ህጉን ያልተከተለ እንደሆነም ጠቁሟል። ምላሹን የሰማው ችሎቱ የዶክተር መረራን መቃወሚያና የዓቃቤ ህግን ምላሽ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለግንቦት 25 ቀጠሮ ሰጥቷል።
ዶ/ር መረራ በቅድመ ክስ መቃወሚያቸው ላይ በኦሮሞ የጥናት ማኅበር (OSA) ያቀረቡት የእንግሊዝኛ ጽሑፍ እጅግ ሰላማዊና ችግር ፈቺ ጽሑፍ መሆኑንን፣ የአገሪቱን ዘርፈ ብዙና ውስብስብ ችግሮች የፖለቲካ መፍትሔ አመላካችና በሰላማዊ ውይይት፣ በድርድር፣ በበጎና በቅን መንፈስ እንዲፈታ የሚጠቁመው ጥናታዊ ጽሑፍ መደምደሚያ ሆን ተብሎ ተቆርጦ መውጣቱ እጅግ በጣም እንዳሳዘናቸው ለፍርድ ቤቱ አስረድተው ነበር።
ዶ/ር መረራ አገራቸውን በተሰማሩበት የሥራ መስክ ከ40 ዓመታት በላይ ከመርዳት ባለፈ፣ ሊያስከስሳቸው የሚችል ተግባር የፈጸሙ ወይም የሚፈጽሙ ባለመሆናቸው ክሳቸው ተነጥሎ መታየት ብቻ ሳይሆን፣ ውድቅ ተደርጎ በነፃ እንዲሰናበቱም ጠይቀው ነበር ፡፡ ክሱን በዋናነት የተቃወሙት በወንጀል መከላከል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 130(1፣ 2፣ መ እና ሰ) መሠረት ፣ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 111(1ሐ) እና 112ን አለማሟላቱን በመግለጽ የተመሰረተባቸውን ክስ እንደሚቃወሙ በመከራከሪያ ደብዳቤያቸው ገልጸዋል።
ከዶ/ር ብርሃኑና ከአቶ ጀዋር ጋር በጋራ ወንጀል እንደሠሩ ተደርጎ በክሱ የተጠቆመ ቢሆንም፣ መቼ አብረው የወንጀሉ ተካፋይ እንደሆኑ፣ ቀን፣ ወርና ዓ.ም. ተለይቶ አለመገለጹን፣ በአጠቃላይ ክሱ የተሟላ ባለመሆኑ ውድቅ እንዲደረግላቸው ፍርድ ቤቱን መጠየቃቸው ይታወሳ፡፡
በተጠርጠሩበት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 01/2009ን የመተላለፍ ወንጀል በፌዴራል ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) በቆዩበት ወቅት የሰጡት ቃል፣ ፍርድ ቤት በቀረበው ክስ ላይ ተጣሞ ከመቅረቡም በላይ ተቆራርጦ መቅረቡንና ሙሉ ቃላቸውን ያላካተተ መሆኑን ለችሎቱ ማስረዳታቸው አይዘነጋም። ዶክተር መረራ ጽንፈኛ አስተሳሰብ የማያራምዱ፣ በሁሉም ዓይነት የህብረተሰብ ክፍል በግልጽ ተናጋሪነታቸው የሚታወቁና የኦሮሚያ ጉዳይ በኢትዮጵያ መዕቀፍ ውስጥ ምላሽ ሊያገኝ እንደሚገባው፣ ኦሮሞ ግንድ በመሆኑ የመገንጠል አጀንዳ የሌሎች እንጂ የኦሮሞ ህዝብ እንዳልሆነ አበክረው የሚናገሩ ፖለቲከኛ ናቸው።

Related stories   በቡድን ተደራጅተው የውንብድና ወንጀል የፈጸሙት ተከሳሾች ከ18 እስከ 20 ዓመት በሚደርስ እስራት ተቀጡ፡፡

ፎቶ ከሰማያዊ ፓርቲ ፌስ ቡክ ገጽ የተወሰደ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *