ኢህአዴግ ” ሉዓላዊ አገርን መዳፈር ነው” ሲል የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በአገሪቱ የደረሰውን ሰብአዊ ጥፋት ለማጣራ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ካደረገ በሁዋላ ገብዣ አደረገ። በዚሁ መሰረት ከፍተኛ ኮሚሺነር ዘይድ ራአድ አል ሁሴን አዲስ አበባ ገቡ።
ኮሚሽነር ዛይድ የተጠሩት የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ” ገለልተኛ ሆኜ አጣራሁት” ያለውን ሪፖርት ይፋ ካደርገ በሁዋላ ነበር። የኮሚሽኑ ሪፖረት ሲቀርብ ” ኢህአዴግ ገደለ፣ ኢህአዴግ አሰረ፣ ኢህአዴግ አጣራ፣ ኢህአዴግ ፓርላማ ሆኖ ሰማ፣ ራሱ በራሱ ለራሱ ወሰነ፤ ይህንን ድራማ አንቀበለውም” በሚል ተቃዋሚ ሃይሎች እና የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ተቃውሞ አሰሙ።
በተለይም ሂውማን ራይትስ ዎች ኢህአዴግ ነጻ አጣሪን የሚፈራበትን ምክንያት ዘርዝሮ ይፋ አደረገ። የዛጎል ምንጮች እንዳሉት ሁማን ራይትስ ዎች መግለጫውን በማውጣት ብቻ አልተቆጠበም። ከፍተኛ ኮሚሺነር ዘይድ ራአድ አል ሁሴን በጉብኝታቸው ወቅት ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ በግላቸው በርካታ፣ በዲፓርትመንት ደረጃና በከፍተኛ ሃላፊዎች በኩል ውትወታ አድርገዋል።
የአገሪቱ ችግር በፖለቲካ ብቻ ሳይሆን በምንዛሬ እጥረትና በእዳ ክምር የታጀበ፣ አሰቃቂ አደጋ ያንዣበበት ድርቅ ያላተመው፣ ማህበራዊ ውጥንቅጡ የተባባሰበት፣ የኑሮ ውድነትና የመቻቻል ባህል የሰለለበት፣ የተፈራው የዘረኝነት ዘር ፍሬው ያሸተበት፣ እንዲሁም የግጭትና የጦርነት ዜና የበዛበት መሆኑ አሳሳቢ የሆነባቸው ይመስል ” የአገሪቱ መጻኢ እድል በመንግስት እጅ ነው” ሲሉ ከፍተኛ ኮሚሺነር ዘይድ ራአድ አል ሁሴን ማሳሰቢያ አዘል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የቪኦኤ አዲስ አበባ ዘጋቢ መለስካቸው አመሃ ከአዲስ አበባ እንደዘገበው ኮሚሽነሩ ጉብኝታቸውን አስመለከተው መንግስትን አለሳልሰው ተችተዋል። የፖለቲካና የዜግነት መብት አደገኛ እንደሆነ ጠቁመዋል። ማህበራዊ፣ ምጣናዊ ጉዳዮች የተያያዙ መሆናቸውን ጠቁመው አደገኛ ያሉት ጉዳይ እንዳይከሰት ” የማታ ማታ የዚህችን አገር መጺአ እድል ለማበጅት ርምጃ መውሰድ ያለባት መንግስት ብቻ ነው” ሲሉ መደነቃቀፍ እንዳይከሰት ስጋታቸውን ገልጸዋል።
መደራጀት፣ መናገር፣ በነጻነት መስብሰብ፣ የጸረ ሽብርተኞች አዋጅና የማህበራት አዋጅ፣ የመገናኛ አዋጅ ዳግም እንዲታዩና እንዲቀየሩ ያሳሰቡት ኮሚሽነሩ፣ እስረኞች እንዲፈቱ ጠይቀዋል። የድርቅ ሰለባዎችን እንደሚረዱ ተናገረዋል። አያይዘውም የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ምርመራ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

Related stories   አፍሪካ ህብረት ቁርጠኛነቱን አሳይቷል፤ አውሮፓ ህብረት ምርጫ አልታዘብም አለ

ታም ማሊኖውስኪ ” አገሪቱ አሁን ያለችበት ሂደት በእሳት ላይ ተጥዶ እንደሚንተከተክ ማሰሮ ይመስላል። እናም እንዲህ የሚንተከተክ ማሰሮ ለማስተንፈስ ያለው ምርጫ ክዳኑን ማንሳት ብቻ ነው፤ ያ ካልተደረገ መንተከተኩ አያቆምም። በዛ ከቀጠለ ደግሞ መገንፈሉ አይቀርም። ከዚያ በሁዋላ የሆነው ሁላችንም እናውቀዋለን ማለታቸው አይዘነጋም።

ዝርዘሩን ያድምጡ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *