ዶር ፍቅሬ ቶሎሳ

የዛሬን አያድርገውና የአባታችንን የኢትዮጵን ስም የተሸከመችው ኢትዮጵያ በመላው ዐለም ገናና ነበረች። ከጥንት ጀምሮ እስከዛሬ 200 ዐመት (እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ማለት ነው) ዛሬ አትላንቲክ ኦሽን ተብሎ የተሰየመው ውቅያኖስ የኢትዮጵያ ውቅያኖስ በላቲን Mar di Aethiopia

በእንግሊዝኛ ደግሞ Ethiopian Ocean ተብሎ ይጠራ ነበር። አውሮፓውያን በሳሉት በዚህ ካርታ አናት በስተግራ በሁለት ሰዎች ያለው ስሌዳ ላይ እና በደቡብ አሜሪካና በ ምእራብ አፍሪካ መሀል ያለው ውቅያኖስ ላይ በላቲን Oceanus Aethiopicus የኢትዮጵያ ውቅያኖስ ይላል። ካርታውን አጉልታችሁ እዩት። ዛሬ Indian Ocean የህንድ ውቅያኖስ የተባለውም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ Ethiopian Ocean የኢትዮጵያ ውቅያኖስ ይባል ነበር። መላውም አፍሪካ ኢትዮጵያ ይባል ነበር። ሲል ሲል አንሶ ከሳሀራ በታች ያለው ክፍል እስከዛሬ 400 ዐመት ድረስ ኢትዮጵያ ይባል ነበር። እሱን በሌላ ወቅት እሳያችኋለሁ። አሁንም ቢሆን አፍሪካ የምትጠራው ድሮ በንግድና የመርከብ ግንባታ በታወቁት በኢትዮጵያውያን አፋሮች ወገኖቻችን ስለሆነ እና ስሙ ከኛው ስላልወጣ ቅር አይለንም። እስያም ቢሆን የኢትዮጵያን ስልጣኔ ወደ እስያ ባደረሰው በአጼ እስያኤል ነው የምትጠራው። በእዚህም እንኮራለን። ዝርዝሩን “የኦሮሞ እና የአማራ የዘር ምንጭ” በተሰኘው መጽሀፌ ማየት ይቻላል።

ጥንት የኢትዮጵያ ውቅያኖስ የሚለውን ስም ፍቀው አትላንቲክ ውቅያኖስ ያሉት የክብራችን ተሻሚዎች ነጮች ቅኝ ገዥዎች ናቸው።

የኢትዮጵያን ታሪክ ተረት ነው ብላችሁ እያናናቃችሁ የእሷን ገናናነት የምትክዱት እና የምታዋርዷት
ሰዎች የታላላቅ አባቶቻችሁን እና እናቶቻችሁን ክብር ገደል ውስጥ እየከተታችሁ መሆኑን እወቁት። እናንተ ማንነታችሁን የማታውቁ እንደ መጻጉእ ድንክዬዎች ብትሆኑም እነሱ እንደ ነፊለም ግዙፋን ነበሩ።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *