የጋዜጠኛ ማስታወሻ የሚለውንና ” የግል የሚለውን ማስታወሻ” ገጣጥሞ ለንባብ ካበቃ በሁዋላ ዲያስፖራው አንግሶት ነበር። በፓልቶክ፣ በሬዲዮ፣ በ”ቲቪ / ዩቲብ” … በተለያዩ ሚዲያዎች አክተር ሆኖ ሙገሳ ጠግቧል። “የቡርቃ ዝምታ” በሚለው የፍጅት አቀጣጣይ መጽሃፉ ጥርስ የነከሱበት ከጅምሩ ቢቃወሙትም የሚሰማቸው አልነበረም። በኢትዮጵያኖች ሚዲያ፣ ኢትዮጵያ ላይ መርዝ እየረጨ ሲጨበጭብለት ያበዱ፣ የተቃጥሉና የተሟገቱ ብዙ ብለው እንደነበርና የሃሳብ መለያየት እስከሚከሰት ድረስ ግጭት ተነስቶም ነበር።
በደጋፊዎቹና ከልብ በሚጠሉት መካከል ያለውን ፍትጊያ ” ኦሮሞን” በመንተራስና ግንቦት ሰባትን በ “መደገፍ” ያለፈው ተስፋዬ ገብረ አብ፣ በስደት ከሚኖርበት ኒዘር ላንድ የወጣበት መረጃ ሊስተባበል በማይችል መልኩ ከሚዲያና እንዳሻው ከሚዘንጥበት ማህበራዊ ገጾች ገፍትሮ እንደወረወረው በጊዜው ብዙ ተብሎበታል። የአሁኑ አመጣጡ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት ሲነሳ መሆኑ አነጋግሪ ሆኗል።

በጋዜጠኛነት ስም መድረክ በማበጀት በኢትዮጵያዊያን ሚዲያ ኢትዮጵያን ለማፈራረስና ህዝቧ እርስ በርስ እንዲባላ ተልዕኮውን ሲያስፈጽም የነበረው ተስፋዬ ገብረ አብ በሰነድ የተረጋገጠ ማንነቱ ገሃድ ሆነ። ዜናውን የሰሙ እንዳሉት ተስፋዬ ካሁን በሁዋላ “በቁሙ ሞተ” ነው የሚባለው ሲሉ ተደምጠዋል።

በተለይም ከኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፉወርቅ ጋር የሚያደርጋቸውን የጽሁፍ ምልልሶች ኮፒ በማደረግ የኒዘርላንዱ ነዋሪ ይፋ ካደረገው በሁዋላ፣ ካለፈው የቡርቃ ዝምታ መጽሃፉ ጋር ተያይዞ ሊከሰስ እንደሚገባው የሚጠይቁ ተነስተውበት ነበር። እነዚህን ሰዎች ጠቅሶ ጎልጉል የድረ ገጽ ጋዜጣ “ተስፋዬ ማለት ካቡጋ ነው፤ የቡርቃ ዝምታ ደግሞ የካቡጋ ሬዲዮ RTLM ነው” ብሏል ። አያይዞም ያነጋገራቸውን ጠቅሶ “ሆላንዳዊው” ተስፋዬ እንደ ካቡጋ “ወደ አባት አገር” በመሄድ ከመሸሸጉ በፊት ውጤታማ ሥራ መሰራት ያለበት አሁን ነው ይላሉ” ሲል ዘግቦ ” አክትቪስት ነን” ለሚሉት ሁሉ ህዝብን ለፍጅት በማነሳሳት ውንጀል እንዲከሰስ አሳስቦ ነበር።
እንደተባለው ይሁን በሌላ ምክንያት ተስፋዬ አገሩ ገብቶ የኢንተርኔት ሱቅ በመክፈት ሲሰራ እንደነበር ከዛው አካባቢ የመጡና የሚያውቁት ይናገራሉ። ተስፋዬ አስመራ እያለም ከሰው ማስኮብለል ጋር በተያያዘ ታስሮ እንደነበርም ስለጉዳዩ የሚያውቁ አመልክተዋል።

Related stories   በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ተያዘ

Image result for tesfaye gebreab

ተስፋዬ በአሁኑ ሰዓት አሜሪካ ሲያትል ይገኛል። እዛም ብዙ እንደሚቆይ ከመናገሩ ውጪ ከሻዕቢያ ጋር ስለመለያየቱ ያለው ነገር የለም። ይልቁኑም አሁን እያሳተመ ያለው ታሪክ የሻቢያን ሚስጢር የሚያጋልጥ እንደሆነ መናገሩን ዜናውን ያቀበሉን ጠቁመዋል።
ጥሩ የመጻፍና የመፈጠር ችሎታ ያለውን ተስፋዬን ኮሎኔል ከማል ገልቾ ” የተወለድኩባትንና ያደኩባትን አርሲን ከኔ በላይ የሚያውቅ ሆኗል” ሲሉ አስተያየት እንደሰጡበት አይዘነጋም። ተስፋዬ አሁን እያሳተመ ያለው መጽሃፍ እንዲተዋወቅለት የኢትዮጵያኖችን ሚዲያና ለመጠቀም ቢፈልግም እንደፈለገው ሊሳካለት እንዳልቻለ በዚሁ ጉዳይ ያወያያቸው ለዛጎል አመልክተዋል።
ኢሳትን ለማስታወቂያነት ቢመርጥም እንዳልተሳካለት የጠቆሙት ምንጮች፣ ኢሳት ተስፋዬን ቃለ ምልልስ አድርጎ የመጽሃፉን ማስታወቂያ ከሰራ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደሚነሳበት ገሃድ በመሆኑ ሊሳካለት እንደማይችል ተናገረዋል። ሌሎች ሚዲአዎችን ለማነጋገር የሚከረ ሲሆን አንዳንዶቹ ጥያቄውን አንቀበልም ባይሉም እንደወትሮው እጃቸውን እንዳልሸረጉለት ነው የተሰማው።

Related stories   አፍሪካ ህብረት ቁርጠኛነቱን አሳይቷል፤ አውሮፓ ህብረት ምርጫ አልታዘብም አለ

በሌላም በኩል ኦነግን ሻቢያ እንዳፈራረሰው ሁሉንም አብጠርጥሮ የተናገረውን ሰናይን ለማስተባበብል ሆን ተብሎ የተዘጋጀና የሻዕቢያን እውቅና ያገኘ መጽሃፍ እንደሆነ ግምት ያላቸውም አሉ። ተስፋዬ ሻዕቢያን ሙሉ በሙሉ የሚያጋልጥ መጽሃፍ ለንባብ ካበቃ፣ የኤርትራን ምድር እንደማይረግጥ ግልጽ በመሆኑ ” እመለሳለሁ” ማለቱ በመጽሃፉ ላይ ከወዲሁ ጥርጣሬን ፈጥሯል። ተስፋዬን በወጉ የሚረዱት እንዳሉት ” አሁን ወቅቱ ኢትዮጵያዊነት የተነቃቃበት በመሆኑ ሃሳብ ለማስቀየርና ሌላ አጀንዳ ለማስቀመጥ ነው” ባይ ናቸው። በዙሁ መነሻ የሚዲያ ረሃቡን ማጠናከረና ፊት መንሳት አስፈላጊ እንደሆነ ያሰምሩበታል። ዛጎል በዚህ ዘግባ ዙሪያ ተጨማሪ ጽሁፍ ያቀርባል።

በቡርቃ ዝምታ ላይ ያሰፈራቸው አንድን ዘር ነጥሎ የሚያስጨፈጭፍ ወፍ ዘራሽና ዓላማ ያለውን ታሪክ ” በሩዋንዳ በተካሄደው የዘር ማጥፋት (ጄኖሳይ) በዋንኛነት ከሚጠቀሱት መካከል የሚዲያውን ኃይል በመጠቀም RTLM (Radio Télévision Libre des Mille Collines) በተሰኘው የሬዲዮ ማሰራጫ አማካኝነት የተነዛው የዘር ጥላቻ ተጠቃሽ ነው፡፡ ሁቱዎች በቱትሲዎች ላይ እንዲነሱ ያደረገውና ቱትሲዎችን “በረሮ” (“cockroaches”) እያለ በመጥራት “እንዲገደሉ” በሬዲዮው አማካኝነት “ትዕዛዝ” ሲሰጥ የነበረው ፌሊሲዬን ካቡጋን (Félicien Kabuga) ዋነኛ ተጠቃሽ ነው፡፡ የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በሩዋንዳ ዘር ማጥፋት ዙሪያ ባደረገው ጥናት ካቡጋን እና የሬዲዮ ጣቢያው ልፈፋ ለ51ሺህ ሰዎች መገደል ቀጥተኛ ተከሳሽ እንዳደረገው ተስፋዬም በተመሳሳይ ሊከሰስ እንደሚገባው ጎልጉል በስፋት አስነብቦ ነበር።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *