“እዚህ ውሳኔ ላይ ስደርስ” አለ ብሩክ እንዳለ “… እዚህ ውሳኔ ውስጥ ስደርስ በጋዜጠኘነት ሙያ ውስጥ ያላችሁን፣ በየዩኒቨርሲቲዎች የጋዜጠኝነትን ትምህርት የምትማሩ ተማሪዎችንና የምታስተምሩ መምህራንን እንዲሁም ፣ መላው የኢትዮጵያን ህዝብን በህሊናዬ እያሰብኩ ነው፤ ለኢቢሲ አጠቃላይ ሰራተኞችና በተለያዩ መንገዶች ከጎኔ ለነበራችሁ ሁሉ አመሰግናለሁ  ዝርዝር ሂደቱን በቅርቡ እንመለከተዋለን፡፡ “

ጉዳዩን ” የሞራል” በማድረግ ለኢቢሲ ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት፣ ለፕሮግራም ቁጥጥር ዘርፍ፣ ለመዝናኛ ዲፓርትመንት ግልባጭ በማድረግ በዋናነት ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኤጀንሲ የስራ መልቀቂያ ማመልክቻ ያስገባው ብሩክ ”በቅርቡ በተፈጠረው ውዝግብ ምክንያት በድርጅቱ ውስጥ ለመቀጠል ሞራላዊ አቅም ስለሌለኝ ስራዬ ለመልቀቅ ተገድጃለሁ” ሲል መግለጹን በፌስ ቡክ አምዱ ይፋ አድርጓል።  ቃል በቃል በፌስ ቡክ ገጹ ከዚህ የሚከተለውን ብሏል

ላለፉት አራት ዓመታት #ከኢቢሲ ጋር ደጉንም መልካሙን ግዜ ተካፍያለሁ  ከሰሞኑ ከተከሰተው(#የቴዲ #አፍሮ) ጉዳይ ጋር ተያይዞ ግን ከህሊናዬ ጋር እየታገልኩ ልቀጥል አልችልም፡፡ ጉዳዩ እንድን የኪነጥበብ ሰው ማቅረብና ያለመቅረብ ጉዳይ ባቻ አይደለም፡፡ ጉዳዩ የጋዜጠኝነት ልዕልናንም የሚጋፋ ሆኖ ስላገኘሁትና ብዙዎች መሰዋት የከፈሉለትን ሙያ ክብር ለመስጠትም ጭምር ነው እዚህ ውሳኔ ለይ የደርስኩት፡፡  ያለፉትን ስድስት ቀናት በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳሳለፍኩ የማውቀው እኔ ነኝ(ግዜው ሲደርስ እናየዋለን)፡፡  እዚህ ውሳኔ ላይ ስደርስ  -በጋዜጠኘነት ሙያ ውስጥ ላላችሁ -የጋዜጠኝነትን ትምህርት በየዩኒቨርሲቲዎች ለምትማሩ ተማሪዎችና ለምታስተምሩ መምህራን  -መላው የኢትዮጵያን ህዝብን በህሊናዬ እያሰብኩ ነው፡፡ለኢቢሲ አጠቃላይ ሰራተኞችና በተለያዩ መንገዶች ከጎኔ ለነበራችሁ ሁሉ አመሰግናለሁ  ዝርዝር ሂደቱን በቅርቡ እንመለከተዋለን፡፡ ስራ ፍለጋው ተጀምሯል

Bruke EBC (2).png

ለኢቲቪ እጅግ ቅርብ የሆኑ እንዳሉት ቅዳሜ እለት ስብሰባ ተካሂዶ ነበር። ከብዙ ንትርክ በሁዋላ ቃለ ምልልሱ እንዲተላለፍ ስምምነት ተደርሶም ነበር። በስተመጨረሻ ግን ዋና እና ምክትል ስራ አስኪያጁ አገር ውስጥ ባለመኖራቸው ሃላፊነት መወሰድ የሚችልና፣ የወረደውን ቀጭን ትዕዛዝ መጋፈጥ የፈለጉ አልተግኙም። በስብሰባው ወቅት ቃለ ምልልሱ መተላለፍ የለበትም ያሉት ክፍሎች ” ብሔር ብሄረሰቦችን አንቋሿል” ሲሉ አቀንቃኙን ግራ በሚያጋባ መልኩ ቃኝተውታል።በሚል ሰፋ ያለ ዘገባ ማውጣታችን ይታወቃል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *