ይልማ ሃብተሚካኤል ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ችግር በግርድፉ እየቃኘ ዶክተር አርከበ እቁባይን መልስ በጠየቀበት ሪፖርቱ ማጠቃለያ “እኔ ብቻ አውቅልሃለሁ የሚለው የሶቪየት ዓይነቱ አመለካከት እንደ በርሊን ግንብ ፈራርሷል” ይላል። ስለ መናገርና አንስቶ ስለ ፕሬስ ነጻነት አንስቶ ፣ ስለ ኢኮኖሚ እድገትን ሲዳስሱ የዴሞክራሲ ግንባታን በተለከተ ” ወዳልታወቀ ቦታ አሽቀንጥረውታል ” ብሏል።

ፕሬስን አስመልክቶ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሳፈውና አውሮፓ የሚጻፈው አንድ መሆኑን ድ/ር አርከበ አመልክተዋል። ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ የተጀመረው በ1995 ዓ.ም መሆኑን ያስታወቁት አርከበ  በአገሪቱ ሃሳብን በነጻነት ከመግለጽና የተቃውሞ ስልፍ ከማክሄድ ጋር በተያያዘ የደረሰው ሰብአዊ ውድመት፣ እንዲሁም የጅምላ እስር ያሳቸው ፓርቲ ጀመረው ስላሉት ዴሞክራሲ መግለጫ እንደሆነ አልተጠያቁም። አልተሞገቱም።

Related stories   Let’s See the Proof of “Ethnic Cleansing” in Ethiopia, New York Times!

ፓርቲያቸው ማንም የሚያውቀውን የካፒታሊዝም አስተሳሰብንና ርዕዮተ ዓለም ኢኮኖሚ ስርዓት እንደሚከተል ያስታወቁት አርከበ፣  አቶ መለስ ፈጠሩት ስለሚባለው የአብዮታዊ ዴሞክራሲ እሳቤና ትግበራ ያሉት ነገር የለም። የኒዮ ሊብራል አስተሳሰብን ባለመከተላቸው የነቀፌታ ሃሳብ እንደሚሰነዘርባቸው የፓርቲያቸው ከፍተኛ አመራሮችና ካድሬዎች በተለያዩ ጊዜያት ሲ መናገራቸው ያታወሳል። የካፒታሊዝምን የኢኮኖሚ መርህ እንደሚከተሉ ” ሁሉም ያውቀዋል” ሲሉ የገለጹት የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ   የመሬት ባለቤትነትን አስመለክቶ አርሶ አደሩ መሬቱ ሸጦ ባዶ እጁን እንዳይቀር ድርጅታቸው ስልሚጨነቅ መሬት መሸጥ መለወጥ እንደማይቻል ተናገረዋል። ይህ የተለመደው አባባል በኢንቨስትመንት ስም ግዳጅ ያለበቂካሳ ክፍያ ከመሬታቸው የሚባረሩትን የሚመለከት ይሁን አይሁን እንዲያብራሩ ጋዜጠኛው አልጋበዛቸውም።

Related stories   የኢዜማ 23 የፓርላማ እጩዎች እነማን ናቸው?

ጋዜጠኛው ቃለ በቃል ባይሞግትም ” ምላሹን አውቀዋለሁ” በሚል ስሜት ይመስላል መሬት ላይ ያለውን እውነታ አጠንክሮና ዋቢዎቹን በደፈናው ጠቅሶ አድማጭን ለፍርድ የጋበዘ ይመስላል። ሪፖርቱን ያድመጡ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *