promised to stand up for the rights of the poor.

ሶስት ጊዜ በሚደረግ ምርጫ እልባት የሚያገኘውን የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል ምርጫ ዶክተር ቴዎድሮስ እየመሩ እንደነበር መረጃዎች ያሳዩ ነበር። በዚሁ መሰረት በመጀመሪያው ዙር ቴዎድሮስ አድሃኖም 95  የድጋፍ ድምጽ አገኝተዋል። ተፎካካሪያቸው ዴቪድ ናባሮ 52 ፣ ሳኒያ ኒሺታር 38 ድምጽ አግኝተው ነበር።  በሁለተኛው ዙር 121 ድምጽ በማግኘት ቴዎድሮስ ቀዳሚ ሲሆኑ ዴቪድ ናባሮ የ62 ድምጽ ባለቤት በመሆን ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ተዛውረው በድል አጠናቀዋል። ሳንያ ግን በዛው ተሰናብተዋል።

በድርጀቱ ህገ ደንብ መሰረት ቴዎድሮስ አደሃኖም በሁለተኛው ዙር ሁለት ሦስተኛ ድምጽ ባለማግኘታቸው ሳቢያ  የመጨረሻው ዙር ውድድር  ተካሂዷል። በዚሁ መሰረት በተካሄደው ሶስተኛ ውድድር ፣ ዶ/ር ቴድሮስ 133 ድምጽ ተችረዋል።  በሁለት ብቻ ድምጽ ያልሰጡ ተመዝገበዋል። እንግሊዛዊው ናቫሮ ሃምሳ ድምጽ አግኝተው ለመሸነፍ ተገደዋል።

በዚሁ ውጤት መሰረት ዶከተር ቴዎድሮስ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ተመራጭ ለመሆን በቅተዋል። ስራቸውን ም ከአንድ ወር ተኩል በሁዋላ በይፋ ይጀምራሉ። ከፍተኛ ዘመቻና ወጪ የተደረገበት፣ የአፍሪካን ህበረት ሙሉ ድምጽ ከጅማሬው ያገኘበትና በዓለም የዓለም የጤና ድርጅት ታይቶ የማያውቅ ተቃውሞ የተስተዋለበት ምርጫ በዚህ መልኩ ተፈጽሟል።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

የተቃውሞውን ዘመቻና የጥላቻውን ጥንካሬ የሚከታተሉም ሆነ በተቃውሞ ውስጥ የሚተሳተፉ እንደሚሉት ይህ ቅራኔ በኢትዮጵያ ያለው ፖለቲካ ነጸብራቅ ነው። የጎሳ ፖለቲካና ውጤቱ የሆነው ጥላቻ የደረሰበት የግለት ደረጃ  አመላካች ነው። ብዙዎች እንደሚሉት የሚያሳስበው እንዲህ የጋመውን ጥላቻ አርግቦ እንደ አገር መቀጠል የሚቻለው እንዴት ነው የሚለው ነው።

በነጻ አስተያየት ለመስጠት የማይደፍሩ ገለልተኛ ወገኖች ” ይህ ምርጫ ክብራችን ሊሆንና በህብረት ልንደግፈው የሚገባ ሆኖ ሳለ ዓለም ላይ መሳቂያ እንድንሆን ያደረገን የውስጡ ፖለቲካ ነው” ይላሉ። እኒሁ ክፍሎች እንዳሉት ” ኢትዮጵያን እየመሩ ያሉት ሃይሎች ከዚህ ሊማሩና ቀውሱን ለማስወገድ ሊሰሩ እንጂ ሊሳለቁና ሊፎክሩ አይገባም” ሲሉ ይመክራሉ።

“አገራዊ ስሜትና አንድነት መክሸፉ እንደ ድል የሚያስደስተው አካል ካለ ያሳዘናል። ማንም ጤነኛ ህሊና ያለው አሁን በታየው የጥላቻ ነጸብራቅ ስለወደፊቱ ከማስብ ይልቅ በድል አደራጊነት የሚያቅራራ ከሆነ ያማል። ራሳቸው ዶክተር ቴዎድሮስም ቢሆኑ የሚቃውሟቸንም ሰዎች ጨምሮ የተወዳደሩት በኢትዮጵያ ስም ስለሆነ በአንድነት ሊያመሰገኑ ይገባል” የሚሉ አስተያየት ሰጪ፣ በተሸናፊና አሸናፊ ስሜት ቀጣይ የጥላቻና የመረጋገም ውዝግብ ውስጥ እንዳይገባ አሳስበዋል።

Related stories   Egypt-Sudan alliance shifting in row with Ethiopia over Nile dam

አንድ የወንጌል አገልጋይ ” ቢልልን አብረን ደስታውን ብናበስር ደግ ነበር። አልሆነም። ብዙ የተበላሹ ጉዳዮች አሉ። አሁን መንግስትም፣ ሚዲያውም፣ ራሳቸው ዶክተር አድሃኖምም ነገሮችን ወደ ማስከን ሊያተኩሩ ይገባል” ሲሉ ተናገረዋል። ዶከተር ቴዎድሮስ በድርጀቱ 70 ዓመት ታሪክ የዓለምን የጤና ድርጀት እንዲመሩ የተሰየሙ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ተደረገው ዛሬ ተመዝግበዋል። የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር የነበሩት አቶ ሱፊያን መሐመድም የአፍሪካን ልማት ባንክ ለመምራት ብቃት ያላቸው ስለመሆናቸው ጥርጥር ባይኖርም በቅስቀሳና በዘመቻ እንዲሁም በበጅት ችግር እስከመጨረሻ አለመጓዛቸው እዚህ ላይ ሳይጠቀስ አይታለፍም።

ቢቢሲ በአጭሩ ይህንን ብሏል

Tedros Adhanom Ghebreyesus from Ethiopia will be the next director general of the World Health Organization (WHO).

He will be the first African to head up the UN agency, after winning the most votes from 186 member states.

Related stories   የትህነግ "ውሮ ወሸባዬ" - የመንግስት ሩጫ - የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!

He replaces Margaret Chan, who will step down from her 10-year post at the end of June.

During her tenure, the WHO’s response to the Ebola epidemic in West Africa was criticised for being too slow.

The agency was accused of missing key warning signs about the severity of the outbreak that began in December 2013 and ultimately killed more than 11,000 people.

Addressing the World Health Assembly shortly before the vote, Dr Tedros promised to respond to future emergencies “rapidly and effectively”.

He also promised to stand up for the rights of the poor.

“All roads should lead to universal health coverage. I will not rest until we have met this.”

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *