የአቋም መግለጫ – ይህ በአይነቱ የመጀመሪያ በሆነውና አሜሪካ ውስጥ በዋሽንግተን ስቴት ሲያትል ከተማ ግንቦት 19 እና 20 2009 ዓ.ም. በተካሄደው የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ጉባኤ ላይ ከመላው ዓለም የመጡ ከ20 በላይ ታዋቂ ምሁራን፣የፖለቲካ፣ የሃይማኖት ተቋማት እና ሲቪክ ማህበራት መሪዎች፣እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች ተሳትፈዋል። በሲያትል እና ዙሪያዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአካል ተገኝተው በጉባኤው የተሳተፉ ሲሆን በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ በመላው ዓለም የሚገኙ ወገኖቻችን ደግሞ በኢሳትና በሌሎች የመገናኛ አውታሮች ውይይቱን ተከታትለዋል። በሲያትል የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ጉባኤ ተሳታፊውች የሀገራችንን ወቅታዊ ሁኔታዎች ገምግመንና በሀገራችን ብሄራዊ አንድነት፣ የጋራ ራዕይና ሀገራዊ አጀንዳችን ላይ ሰፊ ውይይት አካሄደን የሚከተለዉን ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ ዛሬ ግንቦት 20 2009 ዓ.ም. አውጥተናል፡፡

Related stories   ኦፌኮ ራሱን ከምርጫው ማግለሉን አረጋግጧል

8 – ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መሠረት ከሆኑት ዓበይት ጉዳዮች ውስጥ አንዱ የፕሬስ ነፃነት ቢሆንም በሀገራችን ኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን በነፃነት ሊሰሩ የሚችሉበት ሁኔታ ፈፅሞ የለም። በተለይ የወያኔ/ኢህአዴግ የፀረ ሽብር አዋጅ ፀድቆ ተግባራዊ ከተደረገ ጀምሮ የግል ፕሬሶች ሚና እጅግ ከመገደቡም ባለፈ ሚዲያዎቹ በግዳጅ ከኢንዱስትሪው እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡የመንግስት ሚዲያዎችም በሳንሱር ሰንሰለት ተሸምቅቀው ከአንድ ፓርቲ ፕሮፓጋንዳና አስተምህሮ በስተቀር ነፃ አስተሳሰቦች አይስተናገዱባቸውም። በዚህም የተነሳ ህዝቡ አማራጭ መረጃዎችን የሚያገኝባቸው ዕድሎች ሙሉ በሙሉ ተዳፍነዋል ማለት ይቻላል። የሚዲያ ነፃነት የሚረጋገጠው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ሲረጋገጥ ብቻ መሆኑን አምነን በቅድሚያ የህዝቡንና የሚዲያውን ነፃነት አፋኝ የሆነውን አምባገነን ሥርዓት አጥብቀን ለመታገል ቃል እንገባለን፡፡

Related stories   ኦፌኮ ራሱን ከምርጫው ማግለሉን አረጋግጧል

የኢትዮጵያ-ብሔራዊ-አንድነት-ጉባኤ-የአቋም-መግለጫ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *