“Our true nationality is mankind.”H.G.

የ10ኛ ክፍል ፈተና – የኢንተርኔት መቋረጥ ” አገልግሎቱን ማቋረጥ ፈተናዉ ከመሰረቅ አያግደዉም “

የኢንቴርኔት አገልግሎት መቋረጡ

በኢትዮጵያ የ10ኛ ክፍል የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ዘሬ ተጀምሯል።  1.2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ለፈተናው እንደሚቀመጡና ፈተናዉን የሚያስተናግዱ ከ72,000 በላይ ባለሙያዎች መሰማImage result for preparatory school ethiopiaረታቸዉንም በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አጄንስ የህዝብ ግኑኝነትና የኮሙኒኬሼን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

ባለፈዉ ዓመት ፈተናዉ ሾልኮ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን ላይ በመበተኑ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ተደርጎ ነበር። ይህም የብዙ ተማሪዎችን ስሜት እንደነካና ሌሎችንም እንዳስቆጣ ይታወሳል።

Related stories   የዘረኝነት ጥግ “እናት ነኝ የሌሎች ህፃናት ወላጆችን ግን ገደልኩ”

ዘንድሮም ከፈተናው ዋዜማ ጀምሮ የኢንቴርኔት አጋልግሎት መቋረጡ ኢየተሰማ ይገኛል። ትላንት ከአዳማ ተንስቼ ወደ ወለጋ ተጉዣለዉ ያሉን ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉት ግለሰብ የኢንቴርኔት አገልግሎት እንደልነበረ እና በተጓዙበት ከተሞችና መንገዶች የታዘቡትን ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪ የሆነችዉ ግን ስሟ እንዳይጠቀስ የፈለገች የኢንቴርነት ተጠቃሚ ፣አገልግሎቱ ከትላንት ጀመሮ መቋረጡንም  ትናገራለች።

ኢንቴርኔት መዘጋቱ ምናልባት ፈተናዉ ተሰረቀ ወይም አልተሰረቀም የሚለውን ጭንቀት ሊቀንስ ይሆናል እንጅ አገልግሎቱን ማቋረጥ ፈተናዉ ከመሰረቅ አያግደዉም ስትልም አስተያየት ሰጥታለች።የኢንቴርኔት አጋልጊሎት ተቋርጠዋል መባሉን ከመንግስት ኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ፅፈት-ቤትም ሆነ ከኮሙኒኬሼንና እንፎርሜሼን ቴክኖሎጅ ሚንስቴር የሚመለከታቸዉን ለማነጋገር ብንሞክርም አልተሳካም።

የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈዉ ዓመት የፈተናዉ መሽሎክን ሰበብ በማድረግ ለወራቶች የፌስቡክ፣ የትዊተር፣ የእንስታግራምና የቫይበር  አገልግሎቶችን አቋርጦ እንደነበረ ይታወሳል። በጊዜዉ የከፍተኛ ትምሕርት መግቢያ ማረጋገጪያ ፈተናዉን ለመፈተን ከተመዘገቡት 254,000 ተማሪዎች ዉስጥም 136,000 ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች መግባታቸዉን የሐገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበው ነበር።

መርጋ ዮናስ  ኂሩት መለሰ

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0