ስንዴ ወይም ሩዝ በአንድ ቦታ ላይ ዘርቶ በተለይ በማሽን ብዙ ለመስብሰብ ቀላል የሆኑ እህሎች ናቸው። የተራበ ሰውንም ሆድ በቀላሉ ለመሙላት ይቻላል። ነገር ግን ሆድ ከመሙላት አልፎ የሰው ልጅ የሚያስፈለውን ንጥረ ነገር ሁሉ አልያዙም። እንዲያውም አንዱን በብዛት ሌላውን ደግም ምንም ባለመያዛቸው የሰው ልጅ ስንዴን ወይም ሩዝን አመጣጥኖ ከሌላ እህል ጋር ካልበላው የሆነ ነገር መብዛት ወይም የሆነ ነገር ማነስ ይይዘዋል።

Related stories   እኛ የምንመርጠው አባትና አያቶቻችን የመረጡትን ነው።

ጤፍ ግን የምትገርም ነች። በተለይ ቀይ (በተለምዶ ጥቁር የምናላት) የሰው ልጅ ለዚህም ለዚያም ያስፈገዋል የሚባለውን ቪታምን ሁሉንም ከዚህም ትንሽ ከዚያም ትንሽ በዛች ሰውነቷ ላይ አጭቃ ይዛለች። የአካሏን ማነስ ገምታ ሳይሆን አትቀርም ምንም የሚጣል ነገር የላትም።

ጤፍ በጣም የሚገርሙ ብዙ ባህሪዎች አሏት።
1- በሰውነት ውስጥ ሃይልን / ኢነርጂ እንደ ሌሎቹ እህሎች ዘርግፋ አታወጣም፤ ቀስ በቀስ ነው የምትለቀው።
2- ሲያበስሏት እሳት አትፈጅም። በልጅነቱ የጤፍ ዱቄት መቼም ያልቃመ የለም። በልጅነትህ ያልቃማችሁ  ከሆነ አሁን ጓዳ ሂድና ቃሙ ማብሰል እንኳን አያስፈልገውም፣ እንደኔ ስንዴውንም ሞክራችሁ ሆዳችሁን ካልታመመችሁ (ሙከራ ማድረግ ስለምወድ ነው)
3- ለሆድ ቀላልና ቶሎ የሚፈጭ ነው። (ፓስታ ቀላል ምግብ ነው እያለን ሲወጠረን  ይኖራል)።

Related stories   የመረጃ መንታፊዎች ዋትሳፕን እንደ ጥቃት ማድረሻ መሳሪያ እየተጠቀሙ መሆኑ ተገለጸ

ይህንን የጤፍ ባህሪ አይተው ፈረንጆቹ በሚስጢር አዲስ ስም አውጥተውላታል። እኛ ሳንሰማው ‘ሱፐር ግሬይን’ ይሏታል።ጤፍ ከዕህል ዘሮች ውስጥ ጥንታዊ እህል (ancient grain) ከሚባሉት ትመደባለች። ስለዚህ የሚቀጥለው ጊዜ የጥቁር ጤፍ እንጀራ ሲቀርብልህን ብድግ ብለህ እጅ እንንሳት። የእህል ንግስት ነትና።

Geleta Gammo

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *