Riyad Mahrezአርሰናል የኤፍ ኤ ካፕ ባለቤት መሆኑ ብቻ አይበቃም የሚለው ውዝግብ በረድ ብሏል። አርሰን ዌንገርም ቀጣዩ አሰልጣኝ መሆናቸው እውን ሆኖ አሁን ገበያ ላይ ተጠምደዋል። ሁሌም በየዓመቱ በርካታ ታዋቂ ተጨዋቾች ስማቸው ከአርሰናል ጋር እየተነሳ ግዢ ሳይፈጸም ወሬ ሆኖ ስለሚቀር አሁንም እመነት የለም። ይሁን እንጂ ቀደም ሲል ዌንገር ሲሉት አልቀበለውም ሲሉት የነበረውን ሪፎርም መቀበላቸው፣ የዘንድሮው ዓመት ለየት ያለ ውጥረት፣ የደጋፊው ማምረርና እውቅ ነን የሚሉት የክለቡ ተጨዋቾችም ጥያቄ በማየሉ አዳዲስ ተጨዋቾች መምጣታቸው የማይቀር እንደሆነ ተገምቷል።

በሌላ በኩል ያለተቋጨው የሳንቼዝና የኦዚል ጉዳይ ላይ ዌንገር የሰጡት ምላሽም እንደ ወትሮው ልምምጥ የተሞላበት አይመስልም። ” እነሱን የሚተካከሉ ተጨዋቾች ካገኘን ሊለቁ ይችላሉ” ነው ያሉት። በተለይም ሁለቱ ጠጫዋቾች የጠየቁት የተጋነነ ሳምንታዊ ክፍያ በተለይም ለኦዚል አይገባውም የሚል አስተያየትም አለ። ገንዘብ ላይ ጥብቅ የሆኑት ዌንገር ስለዚሁ ጉዳይ በተጠየቁበት መግለጫ ላይ ” ገንዘብ የፈሰሰበት ተጨዋችና ብዙ የሚከፈላቸው በሙሉ ውጤታማ ናቸው ማለት አይቻልም” ሲሉ በሁለት ሚሊዮን የዝውውር ሂሳብ ስላመጡት ታዳጊው ተከላካያቸው ብቃትና ተስፋ አስረግጠው ተናግረዋል።

ምንም አሉ ምን ዌንገር ለሚቀጥለው ዓመት ውድድር የኦዚልና የሳንቼዝን ጉዳይ አጠናቀው የሚጨመሩ ተጫዋቾችን አካተው የተሻለ ቡድን ለመገንባት ደፋ ቀና እያሉ ነው። 100 ሚሊዮን ያቀረቡለት የሞናኮው ታዳጊ አጥቂ ጭምሮ በሚከተሉት ተጫዋቾች ዙሪያ የአርሰናል ስም በክፍተኛ ደረጃ እየተነሳ ነው። አሌክሳንደር ላዛትን ለማስፈረም ማንችስተር ዩናይትድና ሊቨርፑል ዘመቻ ላይ መሆናቸው፣ በተለይም ክሎፕ አዲስ አጥቂ ለማስፈረም ካላቸው እቅድ አንጻር 50 ሚሊዮን ፓውንድ ለመከፈል የተጨዋቹን ወኪል ለማግኘት ለማነጋገር ማቀዳቸው አርሰናል ከውድድሩ መወጣቱን አመላካች ሆኗል። ተጨዋቹ ማድሪድ መግባት ቢፈልግም ከጃንዋሪ በፊት የዝውውር እግዱ ስለማይነሳላቸው መቸረሻውን መጠበቅ ግድ ይሆናል። ሊዮን ግን በእርግጠኛነት ተጨዋቹ ብበዚህ በጋ ጥሏቸው እንደማይሄድ እየገለጹ ነው። ብር ሊያማልልላቸው እንደሚችልም ጎን ለጎን ይወራል። ተጨዋቹ በውድድሩ ዓመት 34 ጎሎችን አስቆጥሯል።

ማህሬዝ ከሌስተር ወደ አርሰናል መግባቱ ያለቀለት የሚመስል ፍንጭ ራሱ ተጨዋቹ ተናግሯል። ባለፈው የውድድር ዓመት ለመቀጠል ሲሳማማ ለቀጣዩ ዓመት እንደሚለቁት ቃል እንደገቡለትና አዲስ ሃላፊነት ውስጥ የመግባት ውሳኔ ላይ መድረሱን ነው ያስታወቀው። ይህ ደግሞ አርሰናል ቤት ኦዚል ሊያበቃለት እንደሚችል አመላካች ሆኖ ተወስዷል።  ሳንቼዝን የሚፈልገውን ከፍሎ ለማስቀረት ሃሳብ እንዳለ ከወራት በፊት ሲሰማ የነበረውን ፍንጭም ይህ የዘውውር ቀመር የሚያጎላው ይመስላል። ኦዚል ካለው ግዴለሽነት፣ ፍጥነት፣ ፍላጎት፣ ጥንካሬና የወቅቱ ብቃት አንጻር አርሰናል እሱ በሚፈልገው ሂሳብ ሊያስማማው ብዙ መንገድ ርቆ ሊሄድ እንደማይችል ተባራሪ ሃሳቦች ከደጋፊዎች አካባቢ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲሰራጭ የቆየ ጉዳይ ነው። በማንኛውም መለኪያ ግን ማሂሬዝ ከኦዚል በበለጠ አርሰናልን ሊያገለግል እንደሚችል የሚታመን ነው። የብዙዎች እምነት የሆነው ሳንቼዝ ብቻ ነው አርሰናልን ቢለይ ደጋፊውም ሆነ ቡድኑ ሃዘን ሊቀመጥ የሚገባው።

ሳንቼዝ ግምቱ፣ ብልተቱ፣ ፍላጎቱ፣ ችሎታው፣ ወኔው፣ እልሁ…. የተሟላ ተጨዋች ነው። ለዚህም ይመስላል ታላላቅ የሚባሉት ክለቦች በሙሉ አሰፍስፈው እየጠበቁት ነው። ባየር ሙኒክ፣ ሲቲ፣ ሴንት ዠርመን፣ ዩናይትድ፣ ቼልሲ… እነዚህ ሁሉ ሳንቼዝን እያሉ ነው። ዌንገር እንዴት አድርገው ያስቀሩት ይሆን?

Alexander la

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *