አርበኛ ዘመነ ካሴ ከእይታ ከጠፉና ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በፈቃዱ ድርጅቱን ለቆ በክብር መሸኘቱን ካስታወቁ በሁዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ራሱን ገለጸ። በዚሁ አጭር መልዕክት ሲያስተላልፍ በታየበት ቪዴዮ፣ ከአስመራ እንዲወጣ ማን በትክክል ሚናውን እንደተወጣ ወደፊት እንደሚገልጽ አመልክቷል። አያይዞም በሽርፍራፊ እውነቶችና በመላመት የሚጻፉና የሚሰራጩ ጽሁፎች ትግሉን እንደሚጎዱ በማሳሰብ ሁሉም ወገኖሽ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥይቋል።

በኤርትራ ያሉትን ታግዮች ለምን እንደተለያቸውና፣ ሳይፈልግ ከትግሉ እነደራቀ በማስታወሰ ” እወዳችኋለሁ” ብሏል። አይይዞም ” የእናትና የአብቶቻቹሁ አምላክ ይጠብቃችሁ” ሲል ስሜቱ ግራ በሚያጋባ ሁኔታ የነብስ ምኞት ተመኝቶላቸዋል። ከአስመራ ስለመውጣቱ ሲናገር የኤርትራን መንግስት እንደ መንግስት የሚችሉትን ሁሉ በማድረጋቸው አመስግኗቸዋል። ይሁን እንጂ ስለ አርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች ያለው ነገር የለም።

Related stories   በትግራይ 3.5 ሚሊዮን ተረጂዎች የዕለት ቀለብና ተመሳሳይ እርዳታ እየተደረገላቸው ነው

ከአስመራ ለመውጣት እንዲችል የገንዘብ እገዛ ያደረጉለትንና አሁን ድረስ እርዳታቸው ላለተለየው ሁሉ ያመቸውን በስም፣ ያላመቸውን በደፈና ሲያመሰግን ድርጅቱ ስላደረገለት የገንዘብ ድጋፍ አልገለጸም። መጥፋቱና ከትግሉ ቦታ መሰወሩ ላሳሰባቸው ፣ ላስጨነቃቸው በሙሉ ክፍተኛ ምስጋና ያቀረበው ዘመነ ካሴ ለእርዳታ የተከፈተለት የሂሳብ አካውንት ለጊዜው ባልታወቁ ሰዎች አማካይነት መዘጋቱን አስመልክቶ ይሁን አይሁን ሳያስረዳ ” ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋውን ከጅምሩ አንስቶ እውቅና ሰጥቼዋለሁ” ሲል ተናግሯል። ሙሉ መልክቱን ከዚህ በታቸ ያለውን ሊንክ በመጫን ያድምጡ።

Related stories   The Forces of Evil Arrayed Against Ethiopia ( (Part I of II)-By almariam

ዘመነ ስለ ሁሉም ነገር ለመናገር የጊዜ ቀጠሮ ይዟል። በተመሣይ በስማ በለው ስለሚነገሩ ጉዳዮች ማሳሰቢያ አዘል መልዕት አስተላልፏል። አሁን በመላካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝም አመልክቷል።

 

https://www.facebook.com/plugins/video.php?href=https%3A%2F%2Fwww.facebook.com%2FAbaytube.net%2Fvideos%2F1169172093189412%2F&show_text=0&width=220

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *