“ከዚህ በሁዋላ አሁን ያለውን የፌደራል አወቃቀር ለመቀየር መሞከር አደጋው የከፋ ነው” በማለት የመንግስት ባለስልጣናት መናገራቸውን ባለፈው ሳምን ሸገር በዜና እወጃው አሰምቶ ነበር። ኢትዮጳያ ውስጥ ያለው የፌደራል ስርዓት አወቃቀር ከመቼውም  ጊዜ በላይ አደጋው እየአፈጠጠ መሄዱን በተደጋጋሚ አስተያየት ሲሰጥ መቆየቱ የሚታወሰ ነው። ለዚህም ይመስላል ሸገር ባሰማው ዜና ላይ ይህንኑ የተመልከተ ጥናት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶ ነበር።

በዚሁ ውይይት ወቅት የፌደራል ስርዓቶ በመልክአምድራዊ አከላለል ቢተካ የሚል ሃሳብ ሲቀርብ መድረኩን የሚመሩት አካላት ሃሳቡ ተጋብር ላይ የሚውል እንዳልሆነ አስረግጠው ሲናገሩ ተደምጧል። አሁን ያለውና ቋንቋን ማእከል ያደረገው ፌደራሊዝም ወደ ጎጥና ጎስ ወርዶ አገሮቱን ወደ አላስፈላጊ ችግር እየገፋት መሆኑ ቢታመነም፣ ቋንቋን መሰረት ያደረገው አወቃቀር እንደማይቀየር ነው አባይ ጸሃዬ ሲናገሩ የተሰሙት። የመፍትሄ ሃሳቦችን ማድመጥና አቁምን መቀየር የማይቻል ከሆነ ለምን ውይይት ይደረጋል? ሲሉ የሚጠየቁ አሉ።  ይህንኑ የተስታከከ ዜና አዲስ አድማስ እንደሚከተለው አቅርቧል።

Related stories   The Legend of the “Greater Republic of Tigray” and the Delirious TPLF Media

ምሁራን በፌደራል ሥርአቱ ስጋቶች ላይ ጥናቶች አቀረቡ

• ፓርቲ በመንግስት ተቋማት ውስጥ ጣልቃ መግቱ መገታት አለበት

• ተቃዋሚዎች በፓርላማ አለመኖራቸው ለስርአቱ ስጋት ነው ተባለ

የፌደራል ስርአቱ በህገ መንግስቱ መሰረት በአግባቡ እየተተገበረ አለመሆኑ፣ የሀገሪቱን አንድነት ስጋት ላይ እንደጣለ ሰሞኑን የቀረቡት ጥናቶች ያመለከቱ ሲሆን በፓርላማው የተቃዋሚ ድምፅ አለመኖሩም ለፌደራል ስርአቱ ስጋት ነው ተብሏል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ከትናንት በስቲያ በተከናወነ የአንድ ቀን አውደ ጥናት ላይ በዩኒቨርሲቲው ምሁራን “በፌደራል ስርአቱ ላይ” የቀረቡ ጥናቶችን መነሻ በማድረግ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተሳተፉበት ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡ በመድረኩ ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ ካቀረቡት ምሁራን መካከል ፕ/ር አሰፋ ፍሰሀ፤ባለፉት 26 ዓመታት የተገነባው የፌደራል ስርአት የተለያየ ማንነት ያላቸውን ህዝቦች በራስ የመተዳደር መብት በማጎናፀፍና እርስ በእርስ በማቀራረብ በኩል ውጤታማ መሆኑን ጠቁመው፤በዚህ መሃል ግን የዜጎች መብት በተለያዩ ግለሰቦች መጣሱ ለፌደራል ስርአቱ አደገኛ ነው ብለዋል፡፡
ዜጎች ከሀገራዊ እሳቤ ይልቅ ክልላዊና መንደራዊ እሳቤ ላይ ማተኮራቸው አሳሳቢ መሆኑን የጠቆሙት ምሁሩ፤ ይህን አመለካከት ለመቀየር በርካታ የፖለቲካ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ የፌደራሊዝም ስርአቱ ዋነኛ አላማ፤ ጎሰኝነትንና ክልላዊነትን ማስፈን እንዳልሆነ ባልተገነዘቡ ሰዎች፣ ባልተገባ መንገድ እየተተረጎመ መሆኑንም አስረድተዋል -ምሁሩ፡፡
በፌደራሊዝም ስርአት ግንባታ ውስጥ ዋነኛ ምሰሶ የሆነው ህገ መንግስቱ በሚገባ በተግባር ላይ ካልዋለ ቅሬታና ግጭት እንደሚያስነሳ በጥናታቸው ያመለከቱት ሌላው የፅሁፍ አቅራቢ ፕ/ር ካሣሁን በሪሁን፤ ህገ መንግስቱ መሬት ላይ ሲተረጎም በአግባቡ አለመሆኑ የፌደራሊዝም ስርአቱ ተግዳሮት ነው ብለዋል፡፡ የመንግስትና የፓርቲ ጉዳይ መደበላለቅም የወቅቱ የፌደራሊዝም ስርአቱ እንቅፋቶች መሆናቸውን የጠቆሙት ጥናት አቅራቢዎቹ፤ ፓርቲ በመንግስት ተቋማት ውስጥ ጣልቃ መግባቱ መገታት አለበት ብለዋል፡፡
“በቤኒሻንጉል፣ ኦሮሚያና ሌሎች ክልሎች፣የሌላ ብሄር ተወላጆች በየጊዜው መፈናቀላቸው ብሄርና ቋንቋን መሠረት ያደረገው ፌደራሊዝም ውጤት ነው” የሚል አስተያየት ከመድረኩ የተሰነዘረ ሲሆን ጥናት አቅራቢዎች፤ ”የመንግስት አስፈፃሚ አካላት ችግር የፈጠረው ነው” ብለዋል፡፡ ፌደራሊዝሙ ለምን በመልከዓ ምድራዊ አቀማመጥና በህዝብ ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ አይሆንም የሚል ጥያቄም ከተሣታፊዎች የተሰነዘረ ሲሆን ከመድረኩ በተሠጠው ምላሽ፤ ከዚህ በኋላ አሁን ያለውን የፌደራል ስርአት ቅርፅና ይዘት አጠናክሮ ከማስቀጠል ውጪ ወደ ኋላ መመለስ አደጋ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡ “ችግሮቹን ነቅሶ አውጥቶ፣ እያረሙና እያስተካከሉ መጓዝ እንጂ ከዚህ በኋላ እንደገና መመለስ የሚፈጥረው ቀውስ ከባድ ይሆናል”
“የማንነት፣ የወረዳና ዞን እንሁን” ጥያቄዎች በሰፊው እየቀረቡና ለግጭትም መንስኤ እየሆኑ መምጣታቸው ፌዴራሊዝሙን አደጋ ላይ እንደጣለው የተጠቆመ ሲሆን መፍትሄው ፖለቲካዊ መግባባት መፍጠርና የዜጎች ድምፅ የሚሰማበትን አማራጭ ማስፋፋት ነው ተብሏል፡፡

Related stories   እውነትን ለሥልጣን መናገር !! ሳማንታ ፖወር - ለኢትዮጵያ ዘር ፖለቲከኞች መከላከል አቁሚ!

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *