“Our true nationality is mankind.”H.G.

በሳዑዲ አረብያ አዋጅና በመንግስት እቅድ ዙሪያ መተማመን ያለ አይመስልም፤ ሁኔታው እጅግ አሳሳቢና አሳዛኝ እንዳይሆን ስጋቱ ጭምሯል

በሳዑዲ አረቢያ የምትኖር እህት እያነባቸ የምትናገረውን ማዳመጥ ያማል። በተለይ ምንም ማደረግ የማይችል ዜጋ ሆኖ ስቃይን ማዳመጥ ሌላ በሽታ ነው። እሷ እንደምትለው በመንግስት ሚዲያ የሚወራው ሁሉ እንደሚባለው አይደለም። ከአየር ዋጋ ጀምሮ ውሸት አለበት። በግል ከዝግጅታችን ክፍል ጋር የተነጋገረ እንደሚለው ” ቤቴን አውቀዋለሁ። መግቢያ የለኝም። መኝታ እንኳን የለንም። ቤተሰቦቼን ምን ብዬ አያቸዋለሁ” ሲል እያለቀሰ ይናገራል።

መንግስት በበኩሉ ሁሉንም እንደ አቅማቸው ለመርዳት ዝግጁ መሆኑንን፣ ቁሳቁስ ይዘው ሲገቡ እንኳ ቀረጥ እንዳይከፉ ህግ ማውጣቱን፣ ሲመለሱም እንደ መንግስት መልሶ የማቋቋም ስራ እንደሚሰራ ተናግሯል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ቃል አቀባይም በተደጋጋሚ ስጋታቸውን በመግለጸ ዜጎች በተሰጣቸው ቀነ ገደብ ውስጥ ወደ አገራቸው እንዲገቡ ሲማጸን ቆይቷል። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝም ስጋታቸውን ገልጸዋል። አቶ ወርቅነህ ነገዎም ሳዑዲ ቆንስላ ጽፈት ቤት ሆነው ዜጎችን ሲያነጋገሩ ታይቷል።

ይህ ሁሉ ሆኖ የሚሰማው ቅሬታ አስደንጋጭ ነው። እያለቀሰች የሚወራው ሁሉ የተጋገነነ ነው የምትለውን እህት ጨምሮ በርካቶች መንግስት ከሚያወራው ጋር አይሰማሙም። ከዚህም በላይ የሳዑዲ መንግስት ሰራተኞችን ለመቀጠር ያደረገው ስምምነት የፈጠረው ጥርጣሬም ቀላል ሆኖ የሚይታይ አልሆነም። አንዳንዶች እንደሚሉት የህጋዊ ቀጥሩን እዛው ማስጀመረና የተወሰኑ ዜጎችንም ቢሆን እንኳ ችግር መቅረፍ የሚቻልበት ድርድር ሊኖር በተገባ ነበር። ሁሉንም የሚከታተሉ ወገኖች እንደሚሉት ግን ነገሮች ወደ አሳዛኝ ደረጃ ሳይቀየሩ በብልሃት ሁሉንም ዓይነት ውሳኔ መወሰንና የአንደን አገር ውሳኔም ማክበር ግድ እንደሆነ ይመክራሉ። የሰው አገር ተሰው ነውና!!

የኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ ዶክተር ነገሪ ሌንጮን ጠቅሶ ፋና የሚከተለውን ዘግቧል

በሳዑዲ ዓረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲወጡ ለማድረግ መንግስትና ዜጎች የሚያካሂዱትን ጥረት አጠናክረው ቀጥለዋል ብለዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በየዕለቱ ከ1 ሺህ በላይ ዜጎች የጉዞ ሰነድ በመውሰድ ላይ ይገኛሉ ያሉት ዶክተር ነገሪ፥ ከ50 ሺህ በላይ ዜጎች የጉዞ ሰነድ መውሰዳቸውን ገልፀዋል።

እስካሁንም በአጠቃላይ 20 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ሚንስትሩ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ተናግረዋል።

እነዚህ ዜጎች አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ ወደ ክልል የሚጓዙት እና አዲስ አበባ የሚቆዩ ተመላሾች ላይ እንግልት እንዳይደርስ በመንግስት ደጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ዶክተር ነገሪ አንስተዋል።

ተመላሾቹ እንደ ሌሎች ዜጎች ሁሉ በራሳቸው ስራ ፈጠራ፣ በንግድ፣ በግብርና ወይም በሌሎች ዘርፎች ላይ ሰርተው መኖር እንዲችሉ በፈቃዳቸው ላይ የተመሰረተ አደረጃጀትና ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም ገልጸዋል።

በአቅም ምክንያት ወደ አገራቸው መመለስ ለማይችሉ ዜጎችም መንግስት ድጋፍ ከሚያደርጉ አካላት ጋር በመሆን አስፈላጊው እገዛ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል።

ብሄራዊ የዜጎች አስመላሽ ግብረ ሃይል እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቀናጅተው በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኙ ያነሱት ኃላፊ ሚኒስትሩ፥ በቀን ውስጥ የሚደረገውን የበረራ ቁጥር ለማሳደግ ከሳዑዲ መንግስት የበረራ ፈቃድ ተጠይቆ ምላሽ እየተጠበቀ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ የክልል መንግስታት ለተመላሽ ዜጎች አስፈላጊውን እገዛ እያመቻቹ መሆኑን ነው ዶክተር ነገሪ የጠቀሱት።

በተለይም ከኦሮሚያ፣ አማራ እና ደቡብ ክልሎች የተውጣጡ ቁጥራቸው 20 የሚሆን የስራ ሃላፊዎች ለቅስቀሳ ስራ ወደ ሳዑዲ መሄዳቸውንም እብራርተዋል።

በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የተመራ የዜጎች አስመላሽ ግብረ ሃይል ወደ ሳዑዲ በመሄድ ከሀገሪቱ ንጉስ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ዜጎች እንዲወጡ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መነጋገራቸው ይታወሳል።

በዚሁ ወቅትም ከሁለት ዓመታት ምክክርና ድርድር በኋላ በኢትዮጵያና በሳዑዲ ዓረቢያ መካከል የውጭ አገር የሥራ ስምሪት ስምምነት መፈራሙን አስታውሰዋል።

በሳዑዲ በህገ ወጥ መንገድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የምህረት አዋጁ ቀነ ገደብ ከመጠናቀቁ በፊት መብቶቻቸው እንደተከበሩላቸው ከአገሪቱ እንዲወጡ መንግስት ጥሪውን እንደሚያቀርብም ዶክተር ነገሪ መልእክት አስተላልፈዋል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ በሳዑዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን እና በራሳቸው ተነሳሽነት በማስታወቂያ በመቀስቀስ ላይ ላሉት የመገናኛ ብዙሃኖችም መንግስት ምስጋናውን ያቀርባል ብለዋል።

በሌላ በኩል የጀርመን ሬዲዮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማነጋገር የሚከተለውን የድምጽ ዘገባ አቅርቧል።

Related stories   “…ለዛሬ ብለን ነገን ከምናበላሽ፣ ለነገ ስንል ዛሬን እንሠዋ” አብይ አህመድ

ሳዑዲ አረቢያ የሥራ እና የመኖሪያ ሰንድ የሌላቸውን የውጭ ዜጎች ለማስወጣት ያስቀመጠችው ቀነ ገደብ ሊያበቃ አንድ ወር ያህል ሲቀረው የኢትዮጵያ መንግሥት ከሳዑዲ መንግሥት ጋር የተፈራረመው አዲስ የሠራተኛ ሥምሪት ስምምነት ፤ተመላሾች በህጋዊነት ወደ ሳውዲ አረብያ ዳግም እንዲሄዱ ያስችላል ቢባልም ብዙዎች እምነት አልጣሉበትም።

የጅርምን ሬዲዮ የተለያዩ ክፍሎችን በማነጋገር ያዘጋጀው ዘገባ እዚህ ላይ ያድምጡ አውዲዮውን ያዳምጡ።30:51

የሳዑዲ አረብያ መንግሥት ህገ ወጥ የሚላቸው የውጭ ዜጎች ከሀገሪቱ እንዲወጡ ያስቀመጠው የ3 ወራት የምሕረት ጊዜ ሊያበቃ 23 ቀናት ብቻ ናቸው የቀሩት። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት 12 ሚሊዮን የሚደርስ የውጭ ዜጋ በህጋዊ መንገድ እንደሚኖር በሚነገርባት በሳውዲ አረብያ 3 ሚሊዮን ያህል ህገ ወጥ የሚባሉ የውጭ ዜጎች ይገኛሉ። ከመካከላቸው በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩት ኢትዮጵያውያን ናቸው። ይሁን እና ህገወጦች ሊከተልባቸው የሚችለውን ቅጣት ያስቀራል የተባለውን የምሕረት አዋጁን ተጠቅመው ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የተዘጋጁት ኢትዮጵያውን ቁጥር ከብዛታቸው ጋር ሲነፃጸር ዝቅተኛ ነው።

መጀመሪያ ላይ አነስተኛ የነበረው የተመላሾች ቁጥር ወደ ኋላ ላይ እየጨመረ ቢሄድም፣ በርካቶች ወደ ሀገር ከመመለስ ይልቅ እዚያው መቅረትን የመረጡ ይመስላል። ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ከሚፈልጉት መካከልም የጉዞ ወጪያቸውን ለመሸፈን ባለመቻል፣  የጉዞ ሰነድ ለማውጣት በመቸገራቸው እና በሌሎችም ምክንያቶች ከሳዑዲ አረብያ መውጣት እንዳልቻሉ በምሬት የሚናገሩም ጥቂት አይደሉም።  ሳዑዲ አረቢያ የሥራ እና የመኖሪያ ሰንድ የሌላቸውን የውጭ ዜጎች ለማስወጣት ያስቀመጠችው ቀነ ገደብ ሊያበቃ አንድ ወር ያህል ሲቀረው የኢትዮጵያ መንግሥት ከሳዑዲ መንግሥት ጋር የተፈራረመው አዲስ የሠራተኛ ሥምሪት ስምምነት ፤ተመላሾች በህጋዊነት ወደ ሳውዲ አረብያ ዳግም እንዲሄዱ ያስችላል ቢባልም ብዙዎች እምነት አልጣሉበትም። የዛሬው እንወያይ በሳዑዲ የምሕረት አዋጅ እና በኢትዮጵያውን ምሬት ላይ ያተኩራል ።

በዚህ ጉዳይ ላይ የሚወያዩ አራት እንግዶችን ጋብዘናል። እነርሱም አቶ ፈይሰል አልይ በሳውዲ አረብያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዳያስፖራ እና የቆንስላ ጉዳዮች ዘርፍ ሃላፊ፣ አቶ ሻውል ጌታሁን በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ሊቀ መንበር፣ አቶ ኤልያስ ባሃሮን ሳውዲ አረብያ ውስጥ በግል ስራ የሚተዳደሩ እና ከ35 ዓመት በላይ የኖሩ ኢትዮጵያዊ እንዲሁም ወይዘሮ ቅድስት ኒና በመመለሻ ውጣ ውረድ ሳውዲ አረብያ ውስጥ በመንገላታት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ውይይቱን የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ማዳመጥ ይችላሉ።

ኂሩት መለሰ ፣ ልደት አበበ

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0