ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

በጋምቤላ ክልል ፈተና ለማጭበርበርና ለመኮረጅ የሞከሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ

በጋምቤላ ክልል እየተሰጠ ባለው ሀገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ለማጭበርበርና ለመኮረጅ  ሲሞክሩ የተደረሰባቸው 24 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ የፈተና ኮማንድ ፖስት አስታወቀ።

የፈተና ኮማንድ ፖስቱ ሰብሳቢና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ማህበር ኮር ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል 20 ግለሰቦች በተለያዩ የፈተና ጣቢያዎች ለጓደኛና ለዘመድ ለመፈተን ተመሳስለው ለመግባት የሞከሩ ናቸው፡፡

Related stories   “በተለምዶ ‘ሸኔ’ የሚባለው ራሱን ‘የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት’ ብሎ የሚጠራው ቡድን ነው”

ቀሪዎቹ አራት ተማሪዎች ደግሞ  ሞባይል ይዘው በመግባት ፈተና ለመኮረጅ ሲሞክሩ የተደረሳባቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ከእነዚህ መጠነኛ ችግሮች በስተቀር በክልሉ በሚገኙ 13 ጣቢያዎች ፈተናው በተረጋጋ ሁኔታ ያለ ምንም ችግር እየተሰጠ መሆኑን ነው የተናገሩት ሰብሳቢው ።

በቀጣይም ከክልል እስከ ወረዳ የተቋቋመው የፈተና ኮማንድ ፖስት ቀሪ የ12ኛና የ8ኛ ክፍል ፈተናዎች ያለምንም ችግር ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል አቶ ማህበር።

Related stories   “በተለምዶ ‘ሸኔ’ የሚባለው ራሱን ‘የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት’ ብሎ የሚጠራው ቡድን ነው”

የጋምቤላ ከፍተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤት ፈተና ጣቢያ አስተባበሪ አቶ ደረጃ ኃይለማሪያም በሰጡት አስተያየት  ለተማሪዎች አስፈላጊውን ማብራሪያ በመስጠት ፈተናውን በተረጋጋ ሁኔታ እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑን  ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ በትናንትናው ዕለት የተሰጣቸውን ማብራሪያና ገለፃ  በመጣስ  ወደ ፈተና ክፍል ሞባይል ደብቀው በማስገባት ለመኮረጅ ሲሞክሩ የተገኙ አራት ተማሪዎች ከፈተና ተሰርዘው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።

በጋምቤላ ክልል በሚገኙ 13 የፈተና ጣቢያዎች ከሶስት ሺህ 200 በላይ ተማሪዎች ሀገር አቀፉን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና በመውሰድ ላይ ናቸው።

Related stories   “በተለምዶ ‘ሸኔ’ የሚባለው ራሱን ‘የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት’ ብሎ የሚጠራው ቡድን ነው”