ትራምፕ ወደ ፕሬዚዳንትነት የመጡበት መንገድ ከምርጫው ዘመቻ ባልተናነሰ ቀልብ የሰባ ክስተት ሆኗል። በተለይም ሩሲያ ዋኝታበታለች የሚባለው የምርጫ ጠለፋ ጉዳይ ከረር መለስ እያለ ቢሆንም በዋንኞቹ ተቀናቃኞችም ሆነ በራሳቸው በታራምፕ ደጋፊዎችም ዘንድ መዥጎርጎር ፈጥሯል።
ከሁሉም በላይ የኤፍቢአይ ዳይሬክተር በድንገት ከሃላፊንታቸው መነሳት ጉልህ ከሚባሉት የዚሁ የምርጫ ጣጣ አንዱና ዋናው ሆኖ ከርሟል። ብዙ አስተያየትም ሲሰጥ ቆይቶ ነበር። ዛሬ ቢቢሲ እንደዘገብው ጀምስ ኮሜይ ከኤፍቢአይ ሃላፊነታቸው የተነሱትለምን እንደሆነ ይፋ አድርገዋል።
ኮሜይ እንዳሉት ከሃላፊነታቸው የተነሱት በምርጫው ጣጣ ነው። በምርጫው ሂደት ሩሲያ ጣልቃ ስለመግባቷ የሚደረገውን ምርመራ አቅጣጫ ለማስቀየር ሲባል ከሃላፊነታቸው መነሳታቸውን አፍርጠዋል። በሌላ ቋንቋ የትራምፕ በትር ያረፈባቸው የምርመራውን ሂደት ለማኮላሸት ሲባል ነው። ኮሜይ አንድ ቀን ትራምፕ እንደሚዋሹዋቸው ያውቁ ስለነበር  በንግግራቸው መካከል ማስታወሻ እንደሚይዙና የተቀዱ ማስርጃዎች ስለመኖራቸውም አለሸሸጉም። ፋና የሚከተለውን ተርጉሟል
“በአሜሪካ የ2016 ምርጫ ላይ ሩሲያ ጣልቃ ስለመግባቷ የሚመረምረው ኮሚቴ ስራ ጫና እየፈጠረባቸው መሆኑን የተረዱት ፕሬዚዳንት ትራምፕ፥ የምርመራውን አቅጣጫ ለማስቀየር ስለፈለጉ ከስልጣኔ አንስተውኛል” ነው ያሉት በማለት ነው አለሳልሰው ጉዳዩን ያቀረቡት።
ኮሜይ ሩሲያ በአሜሪካ ምርጫ ጣልቃ ስለመግባቷ ጥርጣሬ እንደሌላቸውም ለአሜሪካ የህግ አውጭ ምክር ቤት የመረጃ እና ደህንነት ቋሚ ኮሚቴ አባላት በሰጡት የእማኝነት ቃል የጠቀሱት፡፡
በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፥ የሃገሪቱ የምርመራ ቢሮ (ኤፍ ቢ አይ) የቀድሞ ዳይሬክተር ጄምስ ኮሜይ ለምክር ቤቱ የመረጃና ደህንነት ጉዳዮች ኮሚቴ የትራምፕ አስተዳደር ከሩሲያ ጋር ስላለው ግንኙነትና የእርሳቸውን ከሃላፊነት መነሳት በተመለከተ ለኮሚቴው አባላት የእማኝነት ቃላቸውን ሰጥተዋል።
ኮሜይ በቅርቡ ከኤፍ ቢ አይ ሃላፊነታቸው በተነሱበት ወቅት በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሀሰት መረጃ የተቋሙ እና የእርሳቸው ስም መጥፋቱን በአስተያየታቸው ገልፀዋል። ከፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ጋር ተያይዞ፥ የሩሲያን ጣልቃ ገብነት ምርመራ እንዲያቋርጡ በትራምፕ ስለመጠየቃቸው የቀረበላቸውን አስተያየት በዝምታ አልፈውታል፡፡
ኮሜይ ከትራምፕ ጋር ሰላደረጓቸው ንግግሮች ሲናገሩ፥ ሁሉንም ውይይቶች ወይም በአብዛኛው ከውይይቶቻቸው በኋላ በፅሁፍ ያሰፍሩ ወይም ማስታወሻ ይወስዱ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
“ምክንያቱም አንድ ቀን ትራምፕ እንደሚዋሸኝ እና መረጃዎች እንደሚስፈልጉኝ አምን ስለ ነበር” ነው ብለዋል፡፡ በህጉ መሰረት የኤፍ ቢ አይ ዳይሬክተርን ለማንሳት ምንም ምክንያት ባያስፈልግም ትራምፕ ግን እኔን ከስልጣን ለማንሳት ኤፍ ቢ አይ ደካማ ተቋም እየሆነ አድርጎ በማሳየት ነው። እንዲሁም ኮሜይ ተቋሙን የመምራት አቅም የለውም የሚል ምክንያት ማቅረባቸው ተገቢነት እንደሌለው መናገራቸውን በወል ስትሪት ጆርናል የወጣው ዘገባ ያሳያል።፡
ኮሜይ በንግግራቸው የብሄራዊ የደህነት አማካሪ የነበሩት ማይክል ፍሊን ጉዳይን የማጣራት ሂደት እንዲቋረጥ፥ ከትራምፕ ጋር ስለመነጋገራቸው ለቀረበላቸው ጥያቄ ጉዳዩን ምክር ቤቱ አጣርቶ ውሳኔ ላይ መድረስ እንደሚችል አስረድተዋል። ከዚህ ባለፈም ከትራምፕ ጋር ስለነበራቸው ግንኙነቶች እና ንግግሮች የተቀዳ ድምፅ ሊኖር እንደሚችልም ጠቁመው ፕሬዚዳንቱ እንደዋሿቸው ተናግረዋል፡፡
የቀድሞው ዳይሬክተር በሰጡት እማኝነት በስልጣን ዘመናቸው የሂላሪ ክሊንተንን ኢሜል ልውውጥ፥ ከምርጫው በፊት ይፋ ያደረጉት ጫና ለመፍጠር ሳይሆን ፍትሕን ለመጠበቅ ነው ብለዋል፡፡ ሮበርት ሚዩለር የሚመሩት ኮሚቴ፥ ዶናልድ ትራምፕ እንዲያሸንፉ ሩሲያ ያደረገችውን ጣልቃ ገብነት እና የትራምፕን የፍትህ ጥሰት በአግባቡ እንደሚያጣራው አስባለሁም ብለዋል በሰጡት የእማኝነት ቃል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

That wraps up our live coverage of one of the most gripping set-pieces of political theatre on Capitol Hill in many years.

  • In today’s highlights:
  • Referring to the president’s claim that he was fired because he was incapable of leading the FBI, Comey accused Trump of telling “lies, plain and simple”
  • Comey said he took meticulous notes of his meetings with Trump because he was concerned the president would lie about them. “I was honestly concerned that he might lie,” he said
  • Comey said he had “no doubt” that he was fired by Trump to “change” the Russia investigation, and called his sacking a “very big deal”
  • Comey said he had no doubt that Russia meddled in the US election, but said there was no evidence that it had successfully altered any votes
  • Regarding Trump’s tweeted threat that he had taped Comey in the Oval Office, Comey was unconcerned. “Release all the tapes, I’m good with it,” he said
  • Comey said he told Trump he was not the subject of an open foreign counter-intelligence investigation
  • ቢቢሲ ላይቭ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *