ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

”ዋ” አለ ገበሬ፤ የደም አዙሪት የያዘው ታሪካችን – ከ12 ዓምት በሁዋላም ሌላ ሞት፤ ሌላ የሰማዕታት ቀን!!

ግን ግን በቃ እንደዚህ ነው ይምንቀጥለው? ግደል ሲባል የሚቆላ ወታደር፣ ፖሊስ፣ ድህንነት፣ ደጋፊ….. ከዛ ሌሎች ቀባሪና ለቅሶ ተቀማጭ፣ ሃዘን ልብስ ደርተው የሚኖሩ፣ የሙታን ፎቶ ግድግዳ ላይ ሰቅለው ታሪክ እያሰቡ የሚኖሩ…. እንዴት ነው ነገሩ? ገዳዮች ሲገሉ፣ ተገዳዮች እየሞቱ ስንት ዓመት? እስከ መቼ? ገዳይ ቤትሰብ የለውም? እናት አባት… ልጆች… ዘመድ….. መሪዎችስ ከዚህ ሁሉ ውጪ ናቸው? የስሜት ህዋሳቸው የተለየ ነው? ዛሬ እኮ እናት የልጇ አስከሬን ላይ ተቀምጣ ተገርፋለች። ይህ የአካባቢው አመራሮች በሚዲያ ያመኑት እውነት ነው። እንዲህ ያለው ነገር እንዴት ደስታን ይሰጣል? ወዴትስ ነው የሚወስደን? ሰዎች ሁል ጊዜ የሙት ጸበል ጻዲቅ እያዘጋጁ ሃዘን ለብሰው፣ ማቅ ተሸፋፍነው? ”ዋ” አለ ገበሬ!!.

Image result for the goverment force killed after ellection in ethiopiaethiopia
የዚህ ዜና አቀናባሪ የ1997 ዓም ምርጫ ተከትሎ በተወሰደው የሃይል ርምጃ የደረሰውን ጉዳት በተለያዩ ስፍራዎች ዞሮ ተመልክቷል። በሆስፒታሎች በተለይም በሚኒሊክና በራስ ደሰታ ዳምጠው ሆስፒታል ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ወገኖች ደማቸው እየፈሰሰ ሲጮሁ አይቷል። የህክምና ባለሙያዎች እገሌ ከእገሌ ሳይባል ሲረባረቡና ጉዳቱን ሪፖርት ለማድረግ በቅንነት ሲተባበሩ ያስታውሳል። ብቻውን ሳይሆን ከስራ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን አደጋውን ከየትኛውም ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ሚዲያዎች በላይ በምስል በማስደገፍ ድርጊቱ ይፋ አድርገናል።
እኔ፣ አሁን ቪኦኤ በመስራት ላይ ያለችው ጽዮን ግርማ፣ እንዲሁም ፎቶ ግራፈር ቢኒያም መንገሻ፣ ዮሐንስ አምበርበር፣ ዳዊት ቀለመወረቅ ፣ አሽከረካሪያችን በግናባር ቀደም የማነሳቸው ጥይት ውስጥ ሆነው የዘገቡ ናቸው። በሁሉም ዘርፍ የሪፖርተር ሙሉ ስታፍ በ1997 ምርጫ ከጅምሩ እስከ መጨረሻው የሰሩት ስራ አንድ ቀን ከሙያ አንጻር ለዛን ወቅት ስራቸው በአደባባይ ዋጋ ያገኛሉ ብዬ አምናለሁ። ምንም እንኳን ዛሬ ወያኔ በሚል በጅምላ ቢንሰደበም!! ዳሩ ችግሩ የነብረው ከሪፖርተርም ነበር። በሪፖርተር ሰው ለሰራው ስራ ስሙን መጻፍ አይችልም ነበር። ሪፖርት አዘግጅቶ፣ ቃለ መጠይቅ አቅርቦ፣ ዜና ጽፎ የስራው ባለቤት ለመሆኑ ስሙ እንዲጻፍ የሚጠይቅ ሰው ውግዝ ነበር። ይህ እውነት ነው። ይህንን ታሪክ ለማሰቀየርና ስማችንን በጋዜጣው ላይ ለመጽፋ የሚከለክለን ግን ዋናው ባለቤት አልነበረም። ይህንን በቅርቡ በማስተዋውቀው ታሪክ በጥልቀት እገባበታለሁ።
ቢኒያም መንገሻ ህሊናን በሚፈታተነው ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል አስከሬን ክፍል ለራሱና ለጤናው ሳያስብ ውስጥ በመግባት ያነሳቸው ምስሎች፣ በየጥጉ የወደቁትን ወገኖች ያለፍርሃት እየተከታተለ በመቅረጽ ለታሪክ ይሆን ዘንድ ለሰራው ስራ አደባባይ ክብር እንዲሰጠው ሁሌም ምኞቴ ነው።
በዛ ትራንስፖርት ባልነበረበት፣ ሁሉም ነገር ጸጥ እረጭ ብሎ ጥይት በሚያፏጭበት፣ ሰዎች በተቃውሞ “በቃ” ሲሉ፣ ኢህአዴግ ሲገል፣ ልዩ መታወቂያና ከለላ ያልነበራቸው፣ ኢንሹራንስ ያልተገዛላቸው የሪፖርተር ጋዜጠኞች መስክ ለመስክ እየዞሩ የሰሩት ስራ በአገሪቱ የሚዲያ ታሪክ ዋጋ ያለው ስለመሆኑ ሌላ ጊዜ በሰፊው ሃቀኞች ነን የሚሉ ሁሉ ሊመሰከሩለት የሚገባ ይመስለኛል።

Related stories   አቡነ ማቲያስ መነጋገሪያ ሆነዋል - ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻው እንዲከር ጥሪ አቅርበዋል

Image result for the goverment force killed after ellection in ethiopiaethiopia
ሰኔ 1 ቀን የዛሬ 12 ዓመት በጥይት ለተገደሉ ሁሉ ነብስ ይማር። ያን የመሰለ ምርጫ፣ ያን የመሰለ የሕዝብ ተሳትፎ፣ ያንን ታላቅ ምዕራፍ፣ ያንን ታላቅ ገድል፣ ያንን ታላቅ ፋናና እንቁ እንዲሁም አገሪቱን ወደ ዴሞክራሲያዊ ጎዳና የሚያራምድ ሽግግር ላኮላሻሽሁ ማናችሁም ወገኖች የንጹሃን ደም ይፍረድ። የሚጦሩዋቸውን ልጆቻቸውን ያጡ ደካማ እናቶች እምባና ሃዘን ይፍረድ። ከሁሉም በላይ በዚህ የማጨናገፍ፣ የመግደለና ያማስገደል ሂደት ውስጥ ያለፋችሁ ሁሉ ሰማያዊው አምላክ ፍርዱን ይስጣችሁ። ከቅንጅትም ከኢህአዴግም ወገን !!
ሰሜን አዲሱ ገበያ ስጋ ቤቶቹ አካባቢ ቆሜ ሁኔታውን እከታተል ነበር። ከወደ ስጋ ቤቶች አካባቢ አንድ በግምት 19 ዓመት የሚሆነው ጎረምሳ ወደ ዋናው መንገድ መጣ ። ቀይ ባርኔጣ ከለበሰው ወታደር ጋር በመንፈስ ያውሩ በሌላ አልውቀም፣ አናቱን በስናይፐር መታው። እፊት ለፌቴ ተደፋ። በቃ እጥፍ ብሎ ተከነበለ። እዛው አረፈ። ገዳዩ መሳሪያውን ደግኖ ሌላ ለመግደል አይኑን ያጉረጠርጣል። በደቂቃዎች ልዩነት እናት እያነቡ ቁልቁል መጡ። ልጃቸው ላይ ተጠቀለሉ። ለካስ እሳቸውም ተመተዋል። ይህ ነው የግደሉ ትዕዛዝ። ይህ ነው የአቶ መለስ ሌጋሲ። ይህ ነው ባለ ራእዩ መሪ እርምጃ እንዲወሰድ ያዘዙት ትዕዛዝ ውጤት። ለዚህ መሪ መንፈስ ነው የሚገበረው። ለሱ ነው ሃውልት የቁም እየተባለ በቁም ያሉ የሚባረሩት!! አቤት!!
አዎ በ1997 ምርጫ 12ኛ ዓመት ሰማዕታቱ ብቻ ሳይሆኑ እጅግ ብዙ የሚታወሱ ፖለቲካዊ ውርጃዎች አሉ። የዛ ጠባሳ በአገር ደረጃ መተማመን እንዲጠፋ አድርጎ የመባላት፣ እርስ በርስ የመከዳዳት፣ እርስ በርስ የመወነጃጀል፣ የመጠላለፍ፣ ለንዋይ የማበድ፣ ነዋይ ከተገኘ ምንም የመሆን፣ ከሰው ተራ የመሸሽ፣ ነገን አላማሰብ፣ ነገን አለመቁጠር፣ የመጪውን ትውልድ ድርሻ እና ማንነት ጨመሮ የማመንዠግ፣ የማነከት….. ደረጃ ተደርሰ!!
የሚገረመው ከዛ ቀውስ 11 ዓመት በሁዋላም ይኽው በሺህ የሚቆጠሩ ተገለዋል። በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ታስረዋል። ከተለያዩ ወገኖች የሚወጡ መረጃዎች ሁሉ ራስን የሚያስደፉ እንጂ ቀና ብለን እንድንሄድ የሚያደርጉ ሊሆኑ አልቻሉም።  ጉዞ ወደ ሁዋላ ሆኖ በልዩ ኮማንድ ፖስት መተዳደር፣ በወታደራዊ አመራር መኖር ግድ ሆኗል። ይህ ሁሉ እየሆነ ስለ ይቅርታና ስለ ሰላም ማውረድ ማሰብ ቀርቶ ዛሬ በየጥጉ ቂም እየተወቀጠ ነው። ቂም የጥንሡ ጊዜ የደረሰ ሁሉ የሚመስልበት ምልክት አለ።
ዛሬ፣ የዛሬ 12 ዓመት የተፈጸመውን ግድያ ስናስብ፣ አሁን የሞቱት ትኩስ ሃዘን ይዘን ነው።” ለመሆኑ” አለ አንድ ግራ የተጋባ ” እኛ መቼ ነው ከግድያና ከደም አዙሪት የምነወጣው? መቼ ነው የምንሰለጥነው? ወታደሩስ ዝም ብሎ እንዴት ወገኑንን ይገላል” ሲል የጠየቀው እዚህ ላይ የሚታወሰ ነው።

Related stories   በአቡነ ማቲያስ መልዕክት ሳቢያ - ሲኖዶስ በመቆጣቱ አስቸኳይ ስብሰባ ተደርጎ የተግሳጽና የማስተካከያ መግለጫ ሊሰጥ ነው

Image result for the goverment force killed after ellection in ethiopiaethiopia
ግን ግን በቃ እንደዚህ ነው ይምንቀጥለው? ግደል ሲባል የሚቆላ ወታደር፣ ፖሊስ፣ ድህንነት፣ ደጋፊ….. ከዛ ሌሎች ቀባሪና ለቅሶ ተቀማጭ፣ ሃዘን ልብስ ደርተው የሚኖሩ፣ የሙታን ፎቶ ግድግዳ ላይ ሰቅለው ታሪክ እያሰቡ የሚኖሩ…. እንዴት ነው ነገሩ? ገዳዮች ሲገሉ፣ ተገዳዮች እየሞቱ ስንት ዓመት? እስከ መቼ? ገዳይ ቤትሰብ የለውም? እናት አባት… ልጆች… ዘመድ….. መሪዎችስ ከዚህ ሁሉ ውጪ ናቸው? የስሜት ህዋሳቸው የተለየ ነው? ዛሬ እኮ እናት የልጇ አስከሬን ላይ ተቀምጣ ተገርፋለች። ይህ የአካባቢው አመራሮች በሚዲያ ያመኑት እውነት ነው። እንዲህ ያለው ነገር እንዴት ደስታን ይሰጣል? ወዴትስ ነው የሚወስደን? ሰዎች ሁል ጊዜ የሙት ጸበል ጻዲቅ እያዘጋጁ ሃዘን ለብሰው፣ ማቅ ተሸፋፍነው? ስንት ዓመት ይቀጥላሉ።  ”ዋ” አለ ገበሬ!!…. ለምን የደም ታሪካችንን አንዘጋውም? ምንድን ነው ችግሩ? ለምን አገሪቱ እርቅ እንዲወርድባት አይደረገም? አሁን በተያዘው መንገድ ገና ሌላ አደጋ የሚመጣ ነው የሚመስለው። ለሁሉም የሰማይ አምላክ ይርዳን። በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚደማመጡና ካለፈው የሚማሩ ማግኘት ….
ቪኦኤ ቀኑን አስመልክቶ