ethiopian in saudi

ሰው ወደ አገሩ መመለስ እንዴት ያስፈራዋል? ሰው እንዴት የመንን እያየ እንዴት ወደ የመን ሊጓዝ ይነሳል። ሰው ሊቢያ ላይ የሆነውን እያየ እንዴት በሊቢያ በኩል ህይወትን ለማሻሻል ይወስናል? … ኢትዮጵያውያን ሲሰደዱ ያልሞቱት ሞት የለም። በየብስ፣ በባህር አልቀዋል። የሰውነት ክፍላቸው እየተሰረቀ በበረሃ አልቀዋል። ግን አሁንም ስደቱ አልቆመም።

ይህ ታላቅ ብሄራዊ አጀንዳ አይደልም? ሰው ወደ ሞት እየተንደረደረ ሲጎርፍ እንዴት   ብሄራዊ አጀንዳ አይሆንም? ከዚህ በላይ የሚብስ ምን ጉዳይ አለ? ወገን ከሰላማዊ አገሩ ተነስቶ ወደ ሞት ሲሮጥ እንዴት አንደነግጥም? እንዴት አንታመምም? እንዴት መሽቶ ይነጋል? መላ ለመፈለግ ለምን ማንኛውም ዓይነት ስራ፣ ውሳኔ፣ አይወሰነም? አንድ አገር ዜጎቿ ወደ ሞት ሲያመሩ እንዴ መሪዎች ያርፋሉ? ነቢዩ ሲራክ ያነሳቸው ጥያቄዎች እንዲህ ይነበባሉ።

የጀርመን ራዲዮ ወይም የዶቸ ቬሌ የትናንት እሁድ ” ኢትዮጵያ 26 ዓመታት በኢህአዴግ አመራር ” የሚለውን ውይይትት አደመጥኩት ። እጅግ በጣም በሳል ፖለቲከኞች ያደረጉትን ውይይት እያዳመጥኩ ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ስደት የማውቀው የኢትዮጵያን ስደተኛ በውል የማውቀው የ 20ዓመት ጉዞ ከፊቴ ድቅን አለ ። ውይይቱን እያደመጥኩ ከፊት ለፊቴ የተቀመጠውን ድጉስ በሁነኛ አሳታሚና ተከታታይ ሰው እጦት ተዘጋጅቶ ግን ያልታተመውን መጽሐፊን በትዝብት እየተመለ ከትኩ እንደ ስደተኛ የሆነብንን በቁዘማና ትካዜ መካከል አሰንኩት ። ሀገር አድጋ ተመንድጋ ወጣቱ ሀገር ገንቢ ሀገሩን ጠልቶ ስደተኛ የሆነበትን ምክንያት ከተወያዮቹ ብሰማም አሳማኙን ምክንያት ከተገፊ ስደተኞች በበርሃው ላይ ሰምቸዋለሁና አልደነቀኝም ፍትህ ርትዕ በጎደለባት ፣ የሀብት ክፍፍል እኩል በማይደረግባት ፣ አንዱ ባቋራጭ ሲከብር ለፍቶ አዳሪው ለማደግ አሳር ፍዳውን የሚበላባት ሀገረ ኢትዮጵያ ያደገች ግን ሀሀር ግንቢ ወጣት ዜጎቿን ከስደት ያልታደገች ድሃ ሀገር መሆኗ ደረቁ እውነት ነው ! በውይይቱ በፖለቲለኞች የሰማሁት እውነት ፣ ባልታተመው መድብሌም ከአረቡ ሀገር ስደተኛ ባለታሪክ ወገኖቸ የማውቀው ሌላ ያፈጠጠ ያገጠጠ እውነት ነው  የሚያም እውነት  ብቻ ግሩም ድንቅ ውይይቱን ሰምቸ ጨርሰኩትና ወደ ራሴ ተመለስኩ ፣ ወደ ሳውዲው ስደት የሁለት አስርት አመታት ትዝታዬ ተጓዝኩ …

የጀርመን ራዲዮን ውይይት ከዚህ በታች አያይዥዋለሁ ፣ አድምጡት ! እኔም በሳውዲ ስደት ዙሪያ እዚህ ያደረሰንን መንገድ ዳሰሳ ወግ ጀመርኩት እንጅ አልጨረስኩትም ። ወጋችን ፈታ ፈታ አድርገን እናወራለን … በሳውዲው ስደት ዙሪያ የምታውቁትን ዛሬ ሀሳባችሁን ስጡበት ፣ እኔም ከእናነተ ጥቆማና አስተታየት ለጥቆ በቀጣይ የምዳስሰው ወግ ይሆናል !

ልጠይቅዎ !
========
* የምህረት አዋጁ ሊገባደድ ነው ፣ ምን ተሰርቷል ምንስ ተሳክቷል?
* የኮንትራት ስምምነቱ ተፈርሟል ዝርዝር መረጃ ለምን አልወጣም ?
* በስምምነቱን ወደ ተግባር ለመግናት እውን 6 ወር ይፈጃል ?
* የተባለው ዝግጅትስ ተደርጓል ?
* ካለፈው የከሸፈ ዲፕሎማሲና መብት ጥበቃ ምን እንማራለን ?
* ከስደተኛውና ከመንግስት ምን ይጠበቃል ?
* ስደቱ እንዴት ነበር ? እንዴትስ ኖርነው ?
* ኩሩው ዜጋ ” ውጣ” ተብሎ ለምን አልወጣም ?
* ሀገር እያለው ወደ ሀገሩን መመለስ ለምንስ እልፈለገም ?
* አስዎጭቹንስ ለምን ሳይፈራ ለምን ” ና ” ባይ መንግስትና ሀገሩን ፈራ ?
* ያልተሳካው የመብት ጥበቃና ያልተሳካው ዲፕሎማሲ እስከ ምን ?

…ብዬ እጠይቃለሁ መልስ ያላችሁ ወዲህ በሉ ፣ እንወያይበት !

ቸር ይግጠመን !

ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 5 ቀን 2009 ዓም

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *