Image result for achamyeleh«ዳግማዊ ምኒልክ ካምፓስ» በሚል ስም የመሰረት ድንጋይ በወደቀለት ትውልድ ማምከኛ ካምፕ ውስጥ ንጉሱ ሰብአዊ መብት ስለፈጸሙ ተማሪ መማር ላይፈልግ ይችላል ካላችሁ ለምን ይህ ጉዳይ ከናንተ አይጀምርና ምኒልክ «የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጽመው» በገነቡት አገር፤ በቆረቆሩት ከተማ መኖር አንፈልግም ብላችሁ ወደ ትግራይ አትገቡም? እናንተ የሰብአዊ መብት መምህሮች ሰብአዊ መብት ተረግጦ በተገነባ አገር ውስጥ ለምን ትኖራላችሁ?

አቻምየለህ ታምሩ

 

ወያኔ ደብረ ብርሀን ላይ በከፈተው የአእምሮ ማጫጫ የፖለቲካ ማዕከል [ዩኒቨርሲቲ ላለማለት ነው] «ዳግማዊ ምኒልክ ካምፓስ» በሚል ስም የመሰረት ድንጋይ ለወደቀለት ትውልድ ማምከኛ ካምፕ የትግራይ ካድሬዎች እነ ዳንኤል ብርሀነ «ንጉሱ የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጽመዋልና በሳቸው ስም በየተሰየመ ካምፓስ ውስጥ አዲስ ገቢ ተማሪ መማር አልፈልግም ቢል እንዴት ይታያል?» ሲሉ ዘመቻ ከፍተዋል።

ምን ይሄ ብቻ! እነዚህ ካድሬዎች ምኒልክን «በየሰብዓዊ መብት ረገጣ» እየከሰሱ እነሱ ተጨማሪ ሀውልት እንዲቆምላቸው፤ ግዛት እንዲሰየምላቸው ዘመቻና ቅስቀሳ የሚያካሄዱላቸውና «የኛ ናቸው» የሚሏቸው እነ ዓፄ ዮሐንስኮ «ጎጃም ተቃጠለ ከአባይ እስከ አባይ፣ ትግሬ ቅጠል ይዞ ሊያጠፋው ነው ወይ?» የተባለላቸው፤ በነ ዳንኤል ብርሀነ አገላለጽ «ከሰብዓዊ መብት ረገጣ» አልፎ ጎጃምን በሙሉ ያጠፉ፤ ወሎን የጨፈጨፉና የዋጉን ተክለ ጊዮርጊስን አይን በእጃቸው አፍርጠው በዱልዱም በማረድ ዘግናኝ ጭካኔ የፈጸሙ ናቸው።የወያኔ ካድሬዎች ሰው ሁሉ እንደነሱ ደንቆሮና ማገናዘብ የተሳነው ይመስላቸዋል። ይሄ እነሱ «ንጉሱ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ፈጽመዋል» የሚሉት ነገር ሁሉኮ የተፈጸመው ወያኔ ሀውልትና ትምህት ቤት ያቆመላቸው ዓፄ ዮሐንስ አራተኛ ንጉሰ ነገሥት በነበሩበት [ያኔ ምኒልክ ንጉስ ነበሩ] ዘመንኮ ነው። ፖለቲካቸው ጸረ እውቀት፣ የዘርና የዐማራ ጥላቻ ስለሆነ ዓፄ ዮሐንስ አራተኛ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት ሆነው በኢትዮጵያ ውስጥ ተፈጸመ ለሚሉን «የሰብዓዊ መብት ረገጣ» የአንዱን ጠቅላይ ግዛት[ የሸዋን] ገዢ ንጉስ ምኒልክን ተጠያቂ ያደርጋሉ። ይገርማልኮ! ወያኔ ሐውልት ያቆመላቸው የጨለንቆም ሆነ የአኖሌ እየተባሉ የሚነገሩት ጦርነቶችኮ የተካሄዱት በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን ሳይሆን ዓፄ ዮሐንስ አራተኛ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት በነበሩበት ዘመንኮ ነው። እና በምን መስፈርት ነው በዓፄ ዮሐንስ አራተኛ ንጉሰ ነገሥት ዘመን በሆነው ንጉስ ምኒልክ ተወቃሽ ተደርገው «ንጉሱ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ፈጽመዋል» ሊባሉ የሚችሉት?

Related stories   የምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ አቅል ያጣ ፍላጎት ግን ምንድን ነው!?

ምን ይሄ ብቻ! የተከዘ ማዶ ካድሬዎች በየቦታው ሀውልት እንዲቆምላቸውና ትምህርት ቤት እንዲሰየምላቸው የሚቀሰቅሱላቸውና «የኛ ናቸው» የሚሏቸው እነ ራስ አሉላ አባነጋኮ «ሰብዓዊ መብት ረገጣ» ብቻ ሳይሆን ጦርነት በሌለበት ሁናቴ ሰላማዊ ሕዝብ በመውረር ፌቫሊና ሮይ ፓተማን «Blood, Land, and Sex፡ Legal and Political Pluralism in Eritrea» በሚል ርዕስ ባሳተሙት መጽሀፍ ገጽ 36 ላይ እንደገለጽው እ.ኤ.አ. በ1886 ዓ.ም. በባህረ ነጋሽ ባርካን ክልል ባካሄዱት ወረራ ሁለት ሶስተኛውን የኩናማና የናራ ህዝብ እንደጨፈጨፉ አስከፊውን ጭፍጨፋ ተከትሎ የተካሄደውን ጥናት ጠቅሰው አቅርበዋል።

Related stories   ኢትዮጵያን የምታለቅሰው በ"መሪዎቿና በውድ ልጆቿ" ነውና !! ጆሮ ያለው ይስማ!!

እና እንግዲህ «የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጽመዋልና በሳቸው ስም በየተሰየመ ካምፓስ ውስጥ አዲስ ገቢ ተማሪ መማር አልፈልግም ቢል እንዴት ይታያል?» ከተባለ መታየት ያለበት የምኒልክ ብቻ ሳይሆን በዓፄ ዮሐንስ አራተኛና ራስ አሉላ አባ ነጋ ስም የተሰየመውና የሚሰየመው ሁሉ ነው መሆን ያለበት። በዚህ በማይዋሽበት ዘመን ሲያቃጥል በማንኪያ፤ ሲቀዘቅዝ በእጄ አይሰራም! ኢትዮጵያስ ዳግማዊ ምኒልክ በግፍ የመሰረቷት አገር ከሆነች ለምን ሁላችን ወደነበርንበት ከግራኝ በፊት ወደነበረው ይዞታችን አንመለስም?

በምኒልክ ከተማ በአዲስ አበባና በመላው በአገሪቱ ተንፈላሰው ደልቷቸው ተዘባነው እየኖሩ «ንጉሱ የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጽመዋልና በሳቸው ስም በየተሰየመ ካምፓስ ውስጥ አዲስ ገቢ ተማሪ መማር አልፈልግም ቢል እንዴት ይታያል?» የሚሉትን የትግራይ ካድሬዎች እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቁልኝ፤

1. «ዳግማዊ ምኒልክ » በሚል በተሰየመ ካምፓስ ውስጥ «ንጉሱ ሰብአዊ መብት ረገጣ ስለፈጸሙ» ተማሪ መማር ላይፈልግ ይችላል ካላችሁ የናንተው ድርጅት ወያኔ ምኒልክ ቤተ መንግሥት ውስጥ ምን ይሰራል? ሁሉ ነገር ከራስ ይጀምራል እንደሚባለው «ሰብአዊ መብት በፈጸሙት» በምኒልክ ቤተ መንግሥት ውስጥ ፋሽስት ወያኔ ለምን ይኖራል? እስቲ መጀመሪያ እናንተ «ሰብአዊ መብት ረገጡ» ካላችኋቸው ከምኒልክ ቤተ መንግሥት ውጡና ለመርሃችሁ መገዛታችሁን አሳዩን?

Related stories   ኢትዮጵያን የምታለቅሰው በ"መሪዎቿና በውድ ልጆቿ" ነውና !! ጆሮ ያለው ይስማ!!

2. እናንተ የትግራይ ካድሬዎች «ምኒልክ የሰብአዊ መብት ረገጣ ስለፈጸሙ በሳቸው ስም በየተሰየመ ካምፓስ ውስጥ አዲስ ገቢ ተማሪ መማር የለበትም» ስትሉ ያነሳችሁት «ተጠይቅ» የመርህ ጉዳይ ከሆነ፤ ምኒልክ «የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጽመው» በገነቡት አገር ውስጥ፤ «የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጽመው» በቆረቆሩት ከተማ ውስጥ እናንተ ምን ትሰራላችሁ? ለምንስ እናንተ የትግራይ ሰዎች ተከዘን ተሻግራችሁ፤ ወሎና ሸዋን አልፋችሁ ምኒልክ የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጽመው በገነቡት አገር፤ በቆረቆሩት ከተማ በአዲስ አበባ ውስጥ ትኖራላችሁ?

3. «ዳግማዊ ምኒልክ ካምፓስ» በሚል ስም የመሰረት ድንጋይ በወደቀለት ትውልድ ማምከኛ ካምፕ ውስጥ ንጉሱ ሰብአዊ መብት ስለፈጸሙ ተማሪ መማር ላይፈልግ ይችላል ካላችሁ ለምን ይህ ጉዳይ ከናንተ አይጀምርና ምኒልክ «የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጽመው» በገነቡት አገር፤ በቆረቆሩት ከተማ መኖር አንፈልግም ብላችሁ ወደ ትግራይ አትገቡም? እናንተ የሰብአዊ መብት መምህሮች ሰብአዊ መብት ተረግጦ በተገነባ አገር ውስጥ ለምን ትኖራላችሁ?

4. የናንተ ድርጅት ፋሽስት ወያኔስ ለምን ምኒልክ «የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጽመው» አንድ ያደረጉትን አገር ይገዛል? እንዴትስ ብሎ ምኒልክ «የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጽመው» አንድ ካደረጓቸው «ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች» ግብር ይሰበስባል? እስቲ ጠይቁልኝ!

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *