የአዲስ አበባን ስም፣ የመሬት ስሪት፣ የስራ ቋንቋ፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሃላፊዎች መደባና ቅጥር ሙሉ በሙሉ የኦሮሞ የሚያደርግ አጀንዳ ለውሳኔ  እንደሚቀርብ አዋዜ ዘገበ። አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን እንደነገሩት በመግለጽ ዜናውን ይፋ እንዳደረገው የውሳኔ ሃሳቡ የሚቀርበው 20 ወንበር ላለው የኢህአዴግ ዋና ስራ አስፈጻሚ ነው። አጀንዳውንም የሚያቀርቡት ጓድ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ናቸው።

https://www.youtube.com/watch?v=Ja7Z1DoOXY8

የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ የሚያገኘውን ልዩ ጥቅም የሚወስን ህግ በቅርቡ ለፓርላማ ይቀርባል – ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም

አዋዜ አሁን የደረሰን ዜና  በሚል በ16.06.17 እንዳቀረበው  ከሆነ ስብሰባው የተካሄደው አርብ በ17.06.2017 ነው። ይፋ የሆኑት አጀንዳዎች ቀደም ሲል መንግስት እንደማያውቀው በይፋ ያስታወቀው በአዲስአበባ የኦሮሚያን ልዩ መብት የሚደነግግ ተብሎ ከተሰራጨው ረቂቅ  ሰነድ ጋር አንድ ነው።

የኦሮሞ ህዝብ በአዲስ አበባ ላይ ያለው ጥቅሙ አልተከበረም

በዚሁ አዲስ አበባን ፊንፊኔ በሚል ስም የሚተካውና፣ የከተማዋን የስራ ቋንቋ ለጊዜው ኦሮሚኛና አማርኛ የሚያደርገ ነው። በሂደት አማርኛ እንዲከስም ይደረግና ሙሉ በሙሉ ኦሮምኛ የስራ የአገሪቱ ብሄራዊ የስራ ቋንቋ ይሆናል። አዋዜ በክልሉ የኦሮሞ ተወላጆችን የሊዝ ህግ እንደማይመለከታቸው ሲገልጽ በሌላ በኩል የሌሎች ብሄረሰቦች ላይ የሊዝ ህጉ እጥፋ እንደሚሆን ነው ያስረዳው። የአዋዜ ባለቤት ዓለምነህ ዜናውን ሲያውጅ  ደጋግሞ እነዳስታወቀው ይህንን ታላቅ የተባለ ሚስጢር የጠቆመው ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ክፍተኛ ምንጭ ሲሆን፣ መረጃውንም ሲሰማ መድንገጡም በዜናው ተመልክቷል።

አራቱ የኢህአዴግ ድርጅቶች አምስት አምስት ወንበር እንዳላቸው በማስላት በአጀንዳው ላይ ስለሚኖረው የስምምነት አንደማታ በዜናው ግምት ተሰቷል። አጀንዳውን ህወሃትና ብአዴን ሊቃውሙት እንደሚችሉ፤ የደቡብ ህዝቦች ደርጅት አቋም ለጊዜው እንደማይታወቅ፣ ሆኖም እኩል የተቃውሞና የድጋፍ ድምጽ ካለ አቶ ሃይለማርያም የደገፉት ሃሳብ እንደሚያሸንፍ ተመልክቷል።

በዚሁ እሳቤ መሰረት ዜናውን የተከታተሉ ክርክር ገጥመዋል። ” እብደት ነው”  በሚል  ዜናውን ሳይሆን መላምቱን ያልተቀበሉ እንዳሉት የአዋዜ ምንጭ ጉዳዩን ህወሃት እንደማያውቀው አድርጎ ማቅረቡ ሚዛን አይደፋም። አጀንዳውንም ህወሃት ሊቃወም ይችላል መባሉን ያጣጥሉታል።  ጉዳዩን በአጀንዳነት አቶ ሃይለማሪያም ሲያቀርቡት በራሳቸው ውስኔ እንዳደረጉት ማስመሰሉ ምን አልባትም ከታሪካዊ ጥፋትና፣ ሊደርስ ከሚችለው ውስብስብ ችግር አንጻር ጉዳዩን ወደ አቶ ሃይለማሪያም የመለጠፍ ዝንባሌ እንደሆነ ያስረዳሉ።

Related stories   ፍርድ ቤቱ በሙስና ወንጀሎች የተጠረጠሩ የሃያ አራት ግለሰቦችን ጉዳይ ተመለከተ

ከዜናው ጋር በተያያዘ በስፋት የሚጠቆመው የኦሮሞ ጥያቄ ላይ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቅይጥ ኦሮሞዎች ጉዳይና ፍላጎት፣ እንዲሁም ህዝብ ሃሳቡ ሳይጠየቅ በፖለቲከኞች ሃሳብ ላይ ብቻ መንጠላጠል ችግሩን የሚያባብስ እንዳይሆነ ስጋታቸውን የሚገልጹ አሉ። ቅይጥ ደም ያላቸው ኦሮሞዎች በራሳቸው ግማሽ አካል ላይ ጥቃትም ሆነ በደል እንዲደረስ ስለመፍቀዳቸው ማረጋገጫ የለምና ሁሉም ወገኖች ይህ ሃይል ሃሳቡ ምን እንደሆነ ሊረዱ እንደሚገባ በተደጋጋሚ የሚመከሩ ግን ሰሚ ያጡ ወገኖች ጥቂት አይደሉም።

አዋዜ ይፋ ያደረገው እጅግ ውድ መረጃ አስመልክቶ ይህ እስከተጻፈና እስከታተመ ድረስ በድርጅት ልሳኖችም ይሁን በመንግስት ሚዲያዎች የተባለ ነገር የለም። አዋዜም ቢሆን ባለፈው አርብ ይደረጋል ስላለው ውይይት ተጨማሪ መረጃ አላስተላለፈም።

ንጅኅ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *