..ወይዘሮ ውባንቺ ቢሻው በቤተመንግስት ውስጥ በነበሩበት ወቅት በፖለቲካዊ ውሳኔዎች ላይ የነበራቸው ሚና አነስተኛ ሲሆን ብዙውን ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን እና በኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እንጀራ እናት በወይዘሮ አበራሽ ዘውዴ መኖሪያ ግቢ ውስጥ የመንግሰቱን እንጀራ እናት በሽመና ስራ እያገዙ እንደነበረ ይነገራል፡፡

ኤርሚያስ ቶኩማ    —————————————————————————————————

azeb and wobeanchi

ማስታወሻ:- የመጀመሪያው ፎቶ ላይ የምንመለከታቸው ወይዘሮ ውባንቺ ቢሻው ከልጆቻቸው ጋር ነው።

እነዚህ ሁለት ቀዳማዊ እመቤቶች የብርሃን እና የጨለማ፤ የውኃ እና የእሳት ያህል ልነቶች ያላቸው ወይዘሮዎች ናቸው፡፡ የቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ የነበሩት የኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ባለቤት የሆኑት ወይዘሮ ውባንቺ ቢሻው የተወለዱት በቀድሞው የጎጃም ክፍለሀገር ሲሆን በ1968 ኮሎኔል መንግስቱን በማግባት ትዕግስት፣ ትምህርት እና አንድነት መንግስቱ የተባሉ 3 ልጆችን ያፈሩ ሲሆን በአንፃሩ ወይዘሮ አዜብ መስፍንም ከመለስ ዜናዊ ጋር ተጋብተው ሰምሃል፣ ማርዳና ሰናይ የተባሉ ሶስት ልጆችን መውለዳቸው ይታወቃል፡፡

ወይዘሮ ውባንቺ ቢሻው በቤተመንግስት ውስጥ በነበሩበት ወቅት በፖለቲካዊ ውሳኔዎች ላይ የነበራቸው ሚና አነስተኛ ሲሆን ብዙውን ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን እና በኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እንጀራ እናት በወይዘሮ አበራሽ ዘውዴ መኖሪያ ግቢ ውስጥ የመንግሰቱን እንጀራ እናት በሽመና ስራ እያገዙ እንደነበረ ይነገራል፡፡ ወይዘሮ ውባንቺ የባለቤታቸውን ስልጣን መከታ አድርገው የህዝብ ሀብት ለመዝረፍ የሚሯሯጡ አይነት ግለሰብ እንዳልነበሩ ከሰሞኑ ተወዳጁ ጋዜጠኛ ደረጄ ኃይሌ የኮሎኔል መንግስቱ እህትና ወንድም የሆኑትን የሺንና ደረጄን ቃለመጠይቅ ሲያደርግ መታዘብ ችለናል፡፡ የሺ ኃይለማርያም እና ደረጄ ኃይለማርያም ለጋዜጠኛ ደረጄ ኃይሌ እንደነገሩት ከሆነ ከውባንቺ ቢሻው ቤተሰብ የመንግስቱ እህትና ወንድም በመሆናቸው ያገኙት የተለየ ጥቅም አልነበረም፤ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ የመንገስቱ እህት የሆነችው አመለወርቅ ኃይለማርያም አቃቂ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ውስጥ ተቀጥራ ስትሰራ የነበረች ሲሆን ወንድሞቹ ጥላሁን እና ደረጄ ሐይለማርያም ሀገራቸውን በወታደርነት እንዳገለገሉ ይታወቃል አባቱ ኃይለማርያም ወልዴ ደግሞ በስተርጅና ፋብሪካ ውስጥ ተቀጥረው በመስራት ቤተሰቡን ያስተዳድሩ ነበር፡፡ የመንግስቱና የውባንቺ ቤተሰቦች ከተቀረው ኢትዮጵያዊ ጋር ተመሳሳይ ኑሮ የኖሩ ሲሆን ከቀበሌ የሚሠጠውን ዱቄትና ዘይት እንኳን እንደሌላው ዜጋ ተሰልፈው ይገዙ እንደነበረ ይገለፃል የተማሩትም ቢሆን የመንግስት ትምህርት ቤት የሆኑት ጠመንዣ ያዥ፣ ሽመልስ ኃብቴ፣ ዘርፈሽዋል፣ ምስራቅ አጠቃላይና ወንድራድ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ነው፡፡

በአንፃሩ የአዜብ መስፍንን ጉዳይ ስንመለከት ህወሃት ኢትዮጵያን ከወረረበት ከ1983 ዓመተ ምህረት ጀምሮ የመለስ ዜናዊን ስልጣን በመጠቀም የኢትዮጵያን ህዝብ ሃብት የዘረፈች እና በጣሊያኑ ጋዜጣ ኮቲዲያኖ ጭምር ቀዳሚዋ ሙሰኛ ተብለው መሰየማቸው የሚታወቅ ሲሆን የአለም ሃብታሞችን የሀብት ደረጃ በማስቀመጥ የሚታወቀው ዘ ሪቸስት የተሰኘው ድህረገፅ ከዛሬ አራት አመት ይፋ ባደረገው መረጃ ደግሞ አዜብ መስፍን ከሁሤን አላሙዲን ቀጥሎ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለተኛዋ ቢሊየነር ስትሆን ፎረብስ መፅሄት ከ4 ቀናት በፊት በለቀቀው መረጃ የኢትዮጵያ 2ኛው ቢሊየነር ከበደ ከሳ የተባለ ግለሰብ እንደሆነ ቢገልፅም ከበደ ከሳ አሻንጉሊት የሆነ ግለሰብ ሲሆን በከበደ ስም የሚንቀሳቀሰው ሃብት በሙሉ የአዜብ መስፍን ሀብት እንደሆነ እሙን ነው፡፡ በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተባረሩት ምሁራን መካከል አንዱ የሆኑት ዶክተር ወንድሙ መኮንን ከጥቂት ዓመታት በፊት ለእንግሊዝ ፓርላማ የአዜብ ልጅ የሆነችው ሰምሃል መለስ ወደሶስት ቢሊየን የሚጠጋ ገንዘብ እንዳላት የሚያሳይ መረጃ ማቅረባቸውም ይታወሳል፡፡

ወይዘሮ ውባንቺ ቢሻው ልጆቻቸውን መክረውና አስተምረው እስከ ዶክተርነት ያደረሱ እንስት ሲሆኑ ኮሎኔል መንግሥቱ ይህንኑ አስመልክተው መዳብ እያሉ ስለሚጠሯቸው ባለቤታቸው ወይዘሮ ውባንቺ ቢሻው የሌተናል ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ትዝታዎች በተባለው መፅሃፍ ሲናገሩ

“አሥራ ሰባት ዓመት ሙሉ በሥልጣን ላይ ስቀይ ከውባንቺና ከልጆቼ ጋር የማሳልፈው ጊዜ በጣም ውሱን በመሆኑ አንድም ቀን ሰለቸን ደከመኝ ሳትል፡ ሳትማረር የልጆቿን ትምህርትና የቤተሰቡን ጣጣ ሁሉ ብቻዋን የተወጣች ነች” ብለዋል፡፡ በአንፃሩ አዜብ መስፍን ልጆቿን  ልጆቿ የፈፀሟቸው አስነዋሪ ተግባራትን የሚያሳዩ ፎቶዎችን ተመልክተን መታዘባችንም ይታወሳል፡፡

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *