​ በቅርቡ በሜዳ ላይ ህይወቱን ያጣው አይቮሪኮስታዊ እግርኳስ ተጫዋች፣ ቺክ ቲዮቴ በእግርኳሱ ዓለም ዘንድ ከፍተኛ ኃዛን ፈጥሯል። ይህም እውነት አፍሪካውያን ተጫዋቾች ከሌሎች ተጫዋቾች በላቀ ህይወታቸው በሜዳ ላይ እያጡ እንደሚገኙ ማሳያ ይሆን ወይ? የሚል ጥያቄን እንድንጭር ምክኒያት ሆነናል ይላል የሚከተለው ፅሁፍ።

via የእግርኳስ የልብ ችግር: ስለምን የልብ ችግር በአፍሪካውያን ተጫዋቾች ላይ በረከተ? — ኢትዮአዲስ ስፖርት

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በርካታ ቁጥር ያላቸው ተጫዋቾች እግርኳስ በመጫወት ላይ ሳሉ ህይወታቸውን አጥተዋል።

ይህ አጋጣሚ ከገጠማቸው ተጫዋቾች መካከልም ሁለቱ አፍሪካውያያን ማለትም ካሜሮናዊው ማርክ ቪቪያን ፎኤ እና ኮንጓዊው ፋብሪስ ሙኣምባ (በሜዳ ላይ የልብ ምቱ ከቆመ በኋላ ከሞት የተረፈ) ይገኙበታል።

የቀድሞው የኒውካሰል ተጫዋችና ከሳምንታት በፊት ህይወቱን ያጣው ቺክ ቲኦቴ

በጨዋታ ላይ እያሉ ህይወታቸው ስላለፉ ሰዎች በይፋ የቀረበ መረጃ የለም። ነገር ግን ይህ አጋጣሚ ደርሶባቸዋል ተብለው በዊኪፒዲያ ደረገፅ ላይ የተዘረዘሩ ተጫዋቾችን ለዚህ ፅሁፍ እንጠቀማለን። የምንማለከታቸውም በጨዋታ ላይም ሆነ በልምምድ ወቅት ህልፈት የገጠማቸውን ተጫዋቾች ይሆናል።

እንደማጠናከሪያ አድርገንም የግሎባል ስፖርት ተንታትኝ ሮበርት ማስትሮ ዶሚኒኮን የቁጥራዊ የስሌት ትንታኔን እንውሰድ።

ተንታኙ ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ 64 እግርኳስ ተጫዋቾች ለህልፈት እንደተዳረጉ ነገር ግን የሁሉንም ማች ተጫዋቾች ዜግነት ማወቅ እንደሚቸግር ገልፅዋል።

በመሆኑም ዝርዝሩ ውስንነቶች እንዳሉበት መገንዘብ ያሻል። ሆኖም ግን እሱ ከዘረዘራቸው ሟቾች አንፃር ቁጥሩ አንዳች አስገራሚ ነገር መኖሩን ያመላክተናል።

ባለፉት አስርት ዓመታት ህይወታቸውን ካጡ 64 ተጫዋቾች ውስጥ 26 ተጫዋቾች አፍሪካውያን ናቸው። ይህ በመቶኛ ሲሰላ 40 ከመቶ ማለት ነው።

የዓለም አቀፉ የእግርኳስ አመራር ፊፋ በዓለም አቀፍ ደረጃ 265 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በይፋ በሚታወቁ ቡድኖች ውስጥ እግርኳስን እየተጫወቱ ይገኛሉ። ከእነዚህ መካከል ደግሞ 17 በመቶ የሚሆኑት የሚጫወቱት በአፍሪካ ውስጥ ነው።

ይህ ቁጥር ግን በሌሎች አህጉራት ሊጎች ውስጥ በመጫወት ላይ የሚገኙ አፍሪካውያን ተጫዋቾችን አላካተተም። ይሁን እንጂ ቁጥሩ ላነሳነው ሃሳብ እንደማሳያነት ለማገልገል ግን አያንስም።

በመሆኑም ከዓለም የእግርኳስ ተጫዋቾች መካከል 17 እጅ የሚሆኑት አፍሪካውያን ውስጥ እነዚያ 40 በመቶው ሟቾች ይካተታሉ ማለት ነው።

በአጠቃላይ ለእግርኳስ ተጫዋቾች የሜዳ ላይ ህልፈት ዋነኛ መንስኤው ድንገተኛ የሆነ በልብ ምክኒያት የሚፈጠር ህልፈት ነው። በዚህ ምክኒያት ህይወታቸውን የሚያጡት አፍሪካውያን ተጫዋቾች ደግሞ ዕድሜያቸው 25 እና 26 ሳለ መሆኑ ይታወቃል።

እውነትም አፍሪካውያን ተጫዋቾች በልብ እክል ምክኒያት ለሚፈጠር ህልፈት ተጠቂ ናቸው?

ፕሮፌሰር ሳንጄ ሻርማ

የልብ ጥናት ፕሮፌሰር የሆኑት ሳንጃይ ሸርማ በአሜሪካ የሰበሰቧቸው ማስረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ከቅርጫት ኳስ ተጫዋቾች መካከል ጥቁር ተጫዋቾች ከነጭ ተጫዋቾች በሶስት እጥፍ ከልብ ጋር በተያያዘ ችግር ምክኒያት ህይወታቸውን ያጣሉ።

ነገር ግን ፕሮፌሰሩ በጥናታቸው ይህ ዓይነቱ የችግር ተጠቂ ቁጥር ያለበት ብቸኛ ስፍራ አሜሪካ ብቻ አይደለም ይላሉ።

“በአሜሪካ ብሄራዊ የኮሌጆች አትሌቲክ ማህበር የቁጥር መረጃ በአሜሪካ ከአጠቃላዩ በድንገት ከሚከሰት የልብ ችግር ህልፍት በስፖርት ላይ የሚከሰተው 48,000 አደጋ በአንዱ ላይ ነው።

“ይሁን እንጂ ቁጥሩን በጥልቀት ስንመረምረው ግን አደጋው በጥቁር አትሌቶች ላይ ከፍ ያለ ነው። ከ18,000 ድንገተኛ የልብ ተጠቂ አንዱ ጥቁር ወንድ አትሌት ነው።” በማለት ፕሮፌሰሩ ይናገራሉ።

በሌላ አገላለፅ የጥቁር ተጫዋቾች ህልፈት ከነጮቹ ጋር ሲነፃፀር በስድስት እጥፍ ይበልጣል። የመትረፍ ዕድላቸውም ቢሆን በእጅጉ አነስተኛ ነው።


በሜዳ ላይ ህይወታቸው ያለፈ አፍሪካውያን ተጫዋቾች

  • የቀድሞው የጋቦን ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቹ ሞኢሴ ብሩ አጋንጋ በ35 ዓመት ዕድሜው በሊቨርቢል በልምምድ ላይ ሳለ ህይወቱ ያለፈ
  • የካሜሮን ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቹ ፓትሪስ ኢኬንጌ በሮማኒያ ለዳይናሞ ቡካሬስት በመጫወት ላይ ሳለ እ.ኤ.አ. ግንቦት 2016 በ26 ዓመት ዕድሜው ህይወቱ ያለፍ
  • ዛምቢያዊው ቻስዌ ንሶፍዌ እ.ኤ.አ. በ2007 በ28 ዓመት ዕድሜው በእስራኤል በመጫወት ላይ ሳለ ህይወቱ ያለፈ
  • ናይጄሪያዊው ሳሙኤል አክዋራጂ ለሃገሩ ከአንጎላ ጋር ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በመጫወት ላይ ሳለ እ.ኤ.አ. በ1989 በ25 ዓመት ዕድሜው ህይወቱ ያለፈ

“[በልብ ምክኒያት የሚከሰተው ህልፈት] መሰረታዊ ምክኒያቱ ግልፅ አይደለም።” ይላሉ ፕሮፌሰር ሸርማ። ነገር ግን የፕሮፌሰሩ ጥናት የዳሰሰቸው መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ጥቁር ስፖርተኞች ላልተረጋጋ የልብ እክል በይበልጥ ተጠቂ ናቸው። ምክኒያቱ ደግሞ የልባቸው የግራ ክፍል ግድግዳ ሌላ ዝርያ ካለቸው ተጫዋቾች በተለየ የሳሳ ነው።

“ይህም ኤሌክትሪካዊ የሆነ የልብ አለመረጋጋት በመፍጠር ድንገተኛ ህልፈት ሊፈጥር ይችላል።” ሲሉ ፕሮፌሰር ሸርማ በጥናታቸው የደረሱበትን ውጤት ገልፀዋል።

የፕሮፌሰሩ ጥናት የዳሰሰው በሰሜን አሜሪካና ዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ ጥቅር ተጫዋቾች ላይ ነው። ነገር ግን ይህም ቢሆን ጉዳይ ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ በሚገባ የሚያመላክት ነው።

“በጥቁር ህዝቦች ማካከል የተወሰኑ የዘረመል ልዩናቶች ይኖራሉ። የእኛ መረጃም ምንጫቸው ከምዕራብ አፍሪካ በሆኑና በእንግሊዝና አሜሪካ በሚገኙ ጥቁር አትሌቶች ላይ ማሰረት ያደረገ ነው።” ይላሉ ፕሮፌሰር ሸርማ።

ፕሮፌሰሩ አክለውም በምስራቅ አፍሪካ ላይ መረጃ ባይኖርም በዚያ የሚገኙት እንደምዕራብ አፍሪካውያኑ አቻዎቻቸው ከፍ ባለ ሁኔታ የአደጋው ተጠቂ እንደማይመስሉ ገልፀዋል።

በድሆቹ የአፍሪካ ሃገራት የልብ ህመም መመርመሪያ እጥረት አለ። በመሆኑም በተጫዋቾቹ ላይ ያለው ችግር ሁልጊዜም ተለይቶ አይታወቅም።

“የአፍሪካውያኑ ህልፈት ከአጠቃላዩ ድንገተኛ ህልፈቶች ከ48,000 አንዱም እስከ 50,000 አንድ ድረስ ይደርሳል።” ይላሉ ፕሮፌሰሩ።

“የአፍሪካውያኑ የእግርኳስ ተጫዋች ቁጥር ከፍ ያለ ነው?” ለሚለው ጥያቄ መልሱ “ምናልባት።” የሚል ነው።

ጥሩ የሆኑ መረጃዎች እጥረት፣ የሃገር እና የዘር ልዩነት እንዲሁም በቂ የሆነ ክትትል አለመኖር ተደማምረው ትክክለኛውን መልስ ለመስጠት ይቸግራል።

ሆኖም እንደህክምና ጥናቶች መረጃ ጉዳዩ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ እንድናስብ የሚያደረጉ በርካታ የሆኑ ተጨባጭ ምክኒያቶች መኖራቸው ግን እርግጥ ነው።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *