መስቀሉ አየለ

Image result for sky saver

ሰሞኑ የአለምን የመገናኛ ብዙሃን ጉድ ያሰኛው በምእራባዊ ሎንዶን የሚገኘው የእሳት ቃጠሎ ነው። በተለይ እኛ ኢትዮጵያውያን ብዙ ወገኖቻችን በዚህ ህንጻ ውስጥ እንደነበሩና የጉዳቱ ሰለባ ከሆኑት ውስጥ፤ በመቶኛ ሲሰላ ከሌላው አገር ይልቅ በቁጥር የሚልቁት የኛ ዜጎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገመታል። ሌላው መጥፎ አጋጣሚ እሳቱ የተነሳው ከአንድ ኢትዮጵያዊ መኖሪያ ቤት ውስጥ መሆኑ ሲሆን እሳቱ በተነሳ በአምስት ደቂቃ ውስጥ ለእሳት አደጋ መደወሉ፤ አስራ አንደኛው ደቂቃ ላይ እሳት አደጋው መኪና መድረሱንና በአስራ አምስተኛው ደቂቃ ላይ እሳቱ ከቁጥጥር ውጭ መውጣቱን ከዜና ማሰራጫዎች ሰምተናል። ልጁ የተቻለውን ያህል ጎረቤቶቹን ለመቀስቀስ ጥረት ማደርጉን ይነገር እንጅ የመጀመሪያዎቹን ወርቃማ አምስት ደቂቃዎች ያጠፋው ሻንጣውን(ባንክ የማያውቀውንና የደበቀውን ገንዘብ) ሲሸክፍ እንደሆነ ለማዎቅ ተችሎዋል። እነዚያ ወርቃማ ደቂቃዎች ብዙዎች ህይወታቸውን ሊታደጉባቸው ይችሉ እንደነበር መገመት ይቻላል። ይኽ ሲባል ግን አንድ በጣም የሰለጠነ ማህበረሰብ ውስጥ እንዲህ አይነት የተዝረከረከና ፈቃጅ የሌለው ህንጻ መኖሩ የብሪታኒያ ኔሽን ፌይለሪት ነው የተባለለት አሳፋሪ አሰራር መኖሩን አለም እንደታዘባቸው እና እገረ ደረቂቱንና ቀልበቢሷን ጸሃፌ ትእዛዝ ቴሬዛ ሜይን ጭምር አንገት ያስደፋ ኩነት እንደነበርና ዋናውን ተጠያቂነት መውስድ ያለበት የብሪታኒያ መንግስት መሆኑን ሳልዘነጋ ነው።አንድ የትዊተር መረጃ ላይ እንዳየሁት ሰውየው አደጋው ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ ለህይወቱ በመፍራት ፖሊስ ባልታወቀ ቦታ ደብቆታል ይላል።

ስካይ ሴቨር ምንድን ነው፤

በሬ ሆይ ሳሩን ስታይ ገደሉን እንዲባል ጋሻ ሻውን የአባቶቹን እርስት መሬት ለደደቢት መሳፍንቶች እያስረከበ የተወላሸሹ ኮንዶሚኒዩሞችን እንደ ቶምቦላ ለሚናፈቀው የአገሬ ሰው የሚኖረው እሳት አደጋ በሌለበት፣ ቢኖርም ውሃ በሚጠፋበት፣ ውሃ ቢኖርም እሳት አደጋው በማይመጣበት፤ በሚዘገይበት፣ ሲያስፈልግም ወያኔ እራሱ ሆነ ብሎ በውስጥ መመሪያ (በሳቦታጅ) መንደር ሙሉ ቤት በሚያቃጥልበት አገር ውስጥ እንደመኖራችን በእንዲህ አይነት ኮንዶሚኒየም ላይ የእሳት አደጋ ቢፈጠር አስቀድሞ መውጫውን መንገድ ማስላቱ አይከፋም።ይህ ማስታወሻ በተለይ በቨርጂኒያና ቺካጎ ሰማይ ጠቀስ የህንጻ ጫካዎች ውስጥ ባሉ ስካይ ስክራፐሮች ላይ ተንጠልጥላችሁ የምትኖሩ ይዲቪ ጀነሬሽን ወገኖቻችንን በእጅጉ ይመለከታል።

ስካይ ሴቨር ;- በእስራኤል የጦር ሃል ላቦራቶሪ የተፈጠረና ግራቬቲክ & ስታንዳርድ ኢንስቲቱት ኦፍ እስራኤል በተሰኘ ገለልተኛ ተቋም አዋጭነቱ የተመሰከረለት ለአጠቃቀም በጣም ቀላል የሆነ አይነተኛ ህይወት አድን መሳሪያ ነው። ስካይ ሴቨር በሶስት አይነት ሞዴል የሚመጣ ሲሆን ባለ ሃያ አምስት፣ አምሳና ሰማንያ ሜትር ያህል መዘርጋት የሚችሉ ገመዶች ያሉትና በጣም አስተማማኝ ብሬከር የተገጠመለት ሲሆን እስከ መቶ ሰላሳ ሶስት ኪሎ ግፍራም ክብደት ያለውን ሰው የመሸከም አቅም, በሴኮንድ ሁለት ሜትር ፍጥነትና የራሱ የእጅ መቆጣጠሪያ (ፌርን ) ያለው ነው።

ማንም በፎቅ ላይ ተንጠልጥሎ የሚኖር ሰው ሁሉ ገዝቶ ከትራሱ ስር ቢያስቀምጠው እንዲህ ለማየት ቀርቶ ለመስማት ካልተፈቀደ አደጋ እራሱንና ቤተሰቡን ይታደግበታል።ለበለጠ መረጃ የቪዲዮ ሊንኩን ይመልከቱ።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *