የ26 ዓመት ወጣት በፖሊሶች ድብደባ ምክንያት ሀየወቱ ማለፉ ታወቀ፤ አምስት የሚጠጉ ፖሊሶች ነወጣቱ ህይወት ማለፍ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር እንደዋ ተጠቁሟል። ፖሊሶቹ የ14 ቀን ቀን ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል።

ሪፖርተር እንደዘገበው ይህ የሆነው ሟች  ሮቤል ዳዲ  ሰኔ 9 ቀን 2009 ዓ.ም. ከምሽቱ 4 ሰዓት አካባቢ  በጃክሮስ አደባባይ ወደ የረር ጎሮ በሚወስደው መንገድ፣  በግል ተሽከርካሪው  ወደ ቤቱ በመጓዝ ላይ እያለ ነበር።  መንገዱ በአንድ በኩል ተዘግቶ ተሽከርካሪዎች በሙሉ በአንድ መስመር እየተጓዘ መሆኑን የተመለከተው ሮቤል   በችኮላ ይሁን በሌላ ምክንያቱ በዜናው ባልተገለጸ ልዩ ጉዳይ የተዘጋውን መንገድ ጥሶ ማለፉን አሽከርከሯል።

Related stories   The Forces of Evil Arrayed Against Ethiopia ( (Part I of II)-By almariam

በአካባቢው የነበሩ አንድ የትራፊክ ፖሊስ ባልደረባ የፊሽካ ድምጽ ቢያሰሙም ሟች አልቆመም። ከዛም  በአካባቢው የነበሩ ፖሊሶች በሌላ ተሽከርካሪ ተከትለው እንዳስቆሙት የጋዜጣው ምንጮች ተናግረዋል። ለምን መንገድ እንደጣሰ፣ የፊሽካ ድምጭ ሲሰማ ለምን እንዳልቆመ ጠይቀውት ወደ ሲኤምሲ ፖሊስ ጣቢያ ይዘውት እንደሄዱ፣ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ለቤተሰቦቹ ደውሎ መታሰሩን እንዳሳወቀ ዜናው ያስረዳል።

ቤተሰቦቹ በበነጋታው ጠዋት ሲኤምሲ ፖሊስ ጣቢያ ሲደርሱ ሟች ሮቤል መናገር አይችልም ነበር።  እያቃሰተ ድብደባ እንደደረሰበት በመናገሩ ቤተሰቦቹ ወደ ህክምና ወስደውታል።በተደረገለት ምርመራም በጭንቅላቱ ውስጥ ደም መፍሰሱን እንደተነገራቸው ከሪፖርተር ዜና ለመረዳት ተችሏል።

Related stories   ህወሓት፤ የኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ጠላት!

በሲቲስካን ለማስመርመርና ለሕክምና ዕርዳታ ወደ ኮሪያ ሆስፒታል ሲወስዱት በወቅቱ  የሚፈለገውን ሕክምና ባለማግኘቱ ወደ ቤቴል ቲቺንግ አጠቃላይ ሆስፒታል ወስደውት ሕክምና የተደረገለት ቢሆንም፣ ሮቤል ሊተርፍ  አልቻለም። ሰኔ 11 ቀን 2009 ዓ.ም. ሕይወቱ ህይወቱ ያለፈው ሮቤል  በማግስቱ  ገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የቀብር ሥርዓቱ ተፈጽሟል።

ወጣቱን በመደብደብ ሕይወቱ እንዲያልፍ አድርገዋል ተብለው በቁጥጥር ሥር የዋሉ ከአምስት በላይ ፖሊሶች፣ ታስረው ምርምራ እየተደረገባቸው መሆኑንና ፍርድ ቤት ቀርበው የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንደተጠየቀባቸውም በዜናው ተመልክቷል። ይሁን እንጂ የተከሳሾቹ ፖሊሶች  ስም አልተዘረዘረም። የትኛው ምድብ ችሎት ቀጠሮ እንደሰጣቸውና ቀጣዩ ቀጠሮ የትና በትክክለኛው ቀነ መቼና ስንት ሰዓት እንደሆነ ዜናው አላመለክተም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *