“Our true nationality is mankind.”H.G.

መድፈኞቹ ፈረንሳዊውን አጥቂ የግላቸው ለማድረግ ተቃርበዋል ፤ ኦዚል እንደሚቀጥል ተስፋ ሰጠ

እንደ ታማኙ ስካይ ስፖርት ዘገባ ከሆነ ከአራት አመታት በፊት ሚሶት ኦዚልን በክለቡ ታሪክ ከፍተኛ በተባለ የዝውውር ሂሳብ ከሪያል ማድሪድ በ42.5 ሚሊየን ፓውንድ ማስፈረም የቻሉት መድፈኞቹ አሁን ደግሞ ሪከርዳቸውን በመስበር ፈረንሳዊውን አጥቂ የግላቸው ለማድረግ በእጅጉ ተቃርበዋል፡፡

via መድፈኞቹ የክለቡን ሪከርድ ሰብረው ፈረንሳዊውን አጥቂ የግላቸው ለማድረግ ተቃርበዋል — ኢትዮአዲስ ስፖርት

እንደ ታማኙ ስካይ ስፖርት ዘገባ ከሆነ ከአራት አመታት በፊት ሚሶት ኦዚልን በክለቡ ታሪክ ከፍተኛ በተባለ የዝውውር ሂሳብ  ከሪያል ማድሪድ በ42.5 ሚሊየን ፓውንድ ማስፈረም የቻሉት መድፈኞቹ አሁን ደግሞ ሪከርዳቸውን በመስበር ፈረንሳዊውን አጥቂ የግላቸው ለማድረግ በእጅጉ ተቃርበዋል፡፡

የአርሰናል ቆይታቸውን በሁለት ተጨማሪ አመታት ያራዘሙት አርሰን ዌንገር አሁን ትኩረታቸውን ተጫዋቾችን ወደ ክለባቸው ማምጣት ላይ አድርገዋል፡፡

የአርሰናሉ አለቃ ተቀዳሚ የክረምቱ የዝውውር መስኮት ኢላማ እንደሆነ የሚነገርለት ፈረንሳዊው  የኦሎምፒክ ሊዮን አጥቂ አሌክሳንደር ላካዜቴ ደግሞ ሁለተኛው የክለቡ ፈራሚ ለመሆን ተቃርቧል።

Related stories   መሠረታዊ የኮምፒውተር ደህንነት መጠበቂያ መንገዶች

መድፈኞቹ ፈረንሳዊውን የግብ አዳኝ የግላቸው ለማድረግ እስከ 50 ሚሊየን ፓውንድ ፈሰስ ለማድረግ የተሰናዱ ሲሆን ዝውውሩ እውን ከሆነም አሌክሳንደር ላካዜቴ በክለቡ ታሪክ ውዱ ተጫዋች ይሆናል፡፡

Image result for Lacazette

የ26 አመቱ ፈረንሳዊ ባሳለፍነው ወር ከኦሎምፒክ ሊዮን ጋር እንደሚለያይ በይፋ ያሳወቀ ሲሆን ቀጣይ ማረፊያውም የስፔኑ አትሌቲኮ ማድሪድ እንደሚሆን በስፋት ሲነገር ቢቆይም በመጨረሻም ግን አዲሱ መድፈኛ ለመሆን መቃረቡ ተሰምቷል፡፡

ባሳለፍነው የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች 45 ጨዋታዎችን  አድርጎ 37 ግቦችን ከመረብ ያዋሃደው ግብ አዳኙ አጥቂ በሊጉ የአርሰናል አራቱ የፊት መስመር ተሰላፊዎች ኦለቪየድ ጅሩድ ፣ ቲዎ ዋልኮት ፣ ዳኒ ዌልቤክ እና ሉካስ ፔሬዝ በሊጉ በጋራ ካስቆጠሩት ግብ በላይ እርሱ ብቻውን ማስቆጠር ችሏል፡፡

የአርሰናሉ የአማካይ መስመር ተጫዋች ሜሱት ኦዚል በኤምሬትስ የሚያቆየውን ኮንትራት በማራዘም በክለቡ ሊቆይ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል::

ጀርመናዊው አማካይ ከመድፈኞቹ ጋር የመጨረሻ 12 ወራቶች ቀርተውታል። እስካሁንም ድረስ ከክለቡ ጋር ምንም አይነት ኮንትራት የማራዘም ስምምነት አላደረገም።

Related stories   መሠረታዊ የኮምፒውተር ደህንነት መጠበቂያ መንገዶች

በአርሰን ቬንገር የንግስና ዘመን ሪከርድ በሆነ የዝውውር ዋጋ ( 42.5 ሚ.ዩሮ ) በ 2013 ነበር ክለቡን የተቀላቀለው። ነገር ግን አሁን ላይ ውል የማራዘም ውይይት ባለማድረጋቸው ክለቡን ለቆ የሚሄድ አስመስሎታል።

ይሁንና ተጫዋቹ በአርሰናል ደስተኛ መሆኑን፣ ስለ ቅድመ ውድድር ጨዋታዎች ያለውን ሀሳብ በመግለፅና ከአርሰናል ጋር ስለወደፊት ውጤታማነት አርቆ በማሰብ ጭምር ውሉን ሊያራዝም እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል።

የ28 ዓመቱ አማካይ በያዝነው ወር መጀመሪያ መድፈኞቹ ለቅድመ ውድድር ጨዋታዎች ወደ አውስትራሊያ በሚያደርጉት የቡድን ጉዞ ምን ያህል ደስተኛ እንደሆነም ሲናገር ቆይቷል።

“ሲድኒ ጥሩ ከተማ እንደሆነችና ነዋሪዎችም መልካም እንደሆኑ ሰምቻለሁ። ስለ አውስትራሊያ ብዙ አላውቅም። ነገር ግን ስለ ከተማዋ ለማውቅ ይሄ በጣም ጥሩ አጋጣሚ ነው። “እናም ከአርሰናል ጋር ወደ ዛው ለመጓዝ ዝግጁና ደስተኛም ነኝ።

Related stories   መሠረታዊ የኮምፒውተር ደህንነት መጠበቂያ መንገዶች

” ከቡድኑ ጋር የቅድመ ውድድር ጊዜን ማሳለፍ በእውነት ደስ ይላል። በእግር ኳስ ህይወቴም ይህ ጊዜ ሁሌም በደስታ የማሳልፈው።

“በተለይ እንደ ጀርመን ካለ ቡድን ጋር በትልልቅ ውድድሮች ላይ የምትሳተፍ ከሆነ የቅድመ ውድድር ጊዜን ከክለብህ ጋር የማሳለፍ እድልን ማጣትህ የማይቀር ነው::

“ከሁለት ዓመታት በፊት ወደ ሲንጋፖር ተጉዘን ነበር። እናም ከጥሩ ልምድ ጋር ጥሩ የሚባል ጊዜን አሳልፈናል። ከተማዋንና ደጋፊዎችንም ማየት በጣም ያስደስት ነበር።

“እናም ይሄንኑ በአውስትራልያ በድጋሚ ለማየትና የሚኖረንን ጊዜ በደስታ ለማሳለፍ በጉጉት እየተጠባበኩ ነው።” ሲል ከቡድኑ ጋር ረጅም ርቀት እንደሚጓዝ ፍንጭ ሰጥቷል:።

አርሰናል በቅድመ ውድድር ጨዋታዎች ሀምሌ 15 ዌስተርን ሲድኒ ዎንደረርስን ከመግጠሙ በፊት ሀምሌ 13 45,500 ተመልካቾችን በሚያስተናግደው አሊያንስ ስታዲየም ከሲድኒ እግር ኳስ ክለብ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል::

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0