በትግራይ በክረምት ወቅት የሚተከለው የዛፍ  ችግኝ  ኩታገጠምን መሰረት በማድረግ ይከናወናል

በትግራይ በክረምት ወቅት የሚተከለው የዛፍ ችግኝ ኩታገጠምን መሰረት በማድረግ ይከናወናል

በትግራይ ክልል በተየዘው የክረምት ወቅት ለመትከል የተዘጋጀ ከ71 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ኩታገጠምን መሰረት በማድረግ እንደሚከናወን የክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ገለጸ።

በቢሮው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና ልማት ዋና የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ሃፍቱ ኪሮስ ለኢዜአ እንዳሉት በክረምቱ  የሚተከለው ችግኝ ካለፉት ዓመታት በተለየ ሁኔታ ገበያ ተኮር ነው። ባለፉት ዓመታት በባለሙያ ግምት ይሰላ የነበረው የችግኝ ተከላ  በቀጣይነት እንክብካቤ ለማድረግ እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል።

ችግሩን ለመፍታት ዘንድሮ ተከላ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ከ71ሺህ 600 ሄክታር በላይ የሚሸፍን ካርታ መዘጋጀቱን ነው  አቶ ሃፍቱ ያመለከቱት።

ካርታው ለሚተከሉ ችግኞች ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ የሚያግዝ ነው።

Related stories   የበልግ ዝናብ በአንዳንድ አካባቢዎች ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ

በክልሉ ከሁለት ዓመት በፊት በተወሰኑ ወረዳዎች ውስጥ የተጀመረው ኩታገጠምን መሰረት ያደረገ ተከላና እንክብካቤ ውጤታማ በመሆኑ አሁንም ለተከላ በተመረጡ ቦታዎች ይቀጥላል።

ባለፈው ዓመት ከተተከለው ችግኝ 70 በመቶ መጽደቁን በተካሄደው ቆጠራ መረጋገጡን የገለጹት የስራ ሂደት ባለቤቱ ቀደም ባሉት ዓመታት እስከ 56 በመቶ የነበረውን የመፅደቅ እድል ማሳደጉንም ጠቁመዋል።

የማጽደቁ ሁኔታ የተሻሻለው  “በየአካባቢው የሚገኝው ህብረተሰብ  23 ሚሊዮን ለሚሆኑ ችግኞች  ፍግ በመጨመርና  ውሃ በማጠጣት  እንዲከታተላቸው በመደረጉ ነው “ብለዋል። ለተከላ ከተዘጋጀው ችግኝ መካከል  የቀርከሃ፣ የእሬት፣  የሞሪንጋ ፣የእጣንና የሙጫ ዝርያዎች ይገኙበታል፡፡

በትግራይ ደቡባዊ ዞን ሦስት ከተሞች የጎርፍ አደጋን ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራት ተከናወኑ

 በትግራይ ደባባዊ ዞን ሦስት ከተሞች በ60 ሚሊዮን ብር የጎርፍ አደጋን ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ፡፡ የጎርፍ መከላከያ ስራዎች የተካሄዱት በየዓመቱ ክረምት ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ናቸው ተብለው በተለዩ አላማጣ፣ ኮረምና ማይጨው ከተሞች ውስጥ መሆኑን የዞኑ ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት መምሪያ ገልጿል።

Related stories   የቻይናው ሮኬት ስብርባሪ በኢትዮጵያ ቢወድቅ ምን ዓይነት የጥንቃቄ እርምጃዎች ሊወስዱ ይገባል?

የመምሪያው ኃላፊ አቶ አስመላሽ ረዳ ለኢዜአ እንደገለፁት፣ ከተሞቹ በከፍተኛ ተራራ ስር የሚገኙና ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በመሆናቸው በየዓመቱ  የመከላከያ ግንባታ ይካሄዳል፡፡ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ለከተሞቹ የጎርፍ አደጋ መንስኤ በሆኑት በተፋሰሳማ ስፍራዎች በመካሄድ ላይ ያለው ከ10 ኪሎ ሜትር በላይ የውሃ መቀልበሻ ቦይ ግንባታ ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም በየከተሞቹ ውስጥ ለውስጥ የሚገኙ ሰፈሮችን ከጎርፍ አደጋ ለመከላከል ከዘጠኝ ኪሎ ሜትር በላይ የጎርፍ መውረጃ ቦዮች የመገንባት ስራም መካሄዱንም አስረድተዋል። በተለይ በኮረም ከተማ በሚገኘው ወንዝ ላይ የተካሄደው  የጎርፍ መካላከያ ግንባታ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

Related stories   የዓለም ጤና ድርጅት ለቻይናው ክትባት ይሁንታውን ሰጠ

የአለማጣ ከተማ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ረዳኢ ብርሃኑ በበኩላቸው፣ በከተማው በተካሄደው የጎርፍ መካላከያ ግንባታ ነዋሪው ህዝብ በጉልበቱ የቦዮች ቁፋሮ በማከናወን ከፍተኛ እገዛ አድርጓል ብለዋል።

የኮረም ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ሓዳስ ተስፋይ በሰጡት አስተያየት፣ ቀደም ሲል የጎርፍ መከላከያ ባለመሰራቱ በየዓመቱ ከአከባቢው ተራራማ ስፍራ በሚወርደው ጎርፍ በንብረታቸው ላይ ጉዳት ሲያደርስ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

የማይጨው ከተማ ነዋሪ አቶ አብርሃ ምሩፅ በበኩላቸው፣ በከተማው የጎርፍ መከላከያ ባለመኖሩ ከንብረት  ውድመት በተጨማሪ የሰው ህይወትም አደጋ ላይ እየጣለ እንደነበር ተናግረዋል። በአሁኑ ጊዜ በከተማው የጎርፍ መውረጃ ቦዮች እየተገነቡ በመሆናቸው ከስጋት ነፃ መሆናቸውን ተናግረዋል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *