via ዝውውር፡ የዕለተ እሁድ አጫጭር የዝውውር ወሬዎች — ኢትዮአዲስ ስፖርት
- • አርሰናል ለኪሊያን ምባፔ 125 ሚ.ፓ. በማቅረብ ሪያል ማድሪድ በሞናኮው ወጣት አጥቂ ላይ ያለውን ፍላጎት ለማስተጓጎል ተዘጋጅቷል።
- • ምባፔ ከግል የትዊተር ገፁ ላይ ሞናኮን ማስወገዱን ተከትሎ በዝውውር ወሬው ላይ ቤንዚን አርከፍክፏል።
- • አርሰናል በተከላካዩ ኪራን ጊብስ ላይ የ8 ሚ.ፓ የዝውውር ዋጋ ለጠፈ።
- • የርገን ክሎፕ ዳንኤል ስተሪጅ ሊቨርፑልን እንዳይለቅ ያግዳሉ። ምክኒያቱም እሱን ለመተካት ብዙ ገንዘብ ያስወጣቸዋል።
- • የርገን ክሎፕ ተከላካዩን በቅድመውድድር ዘመን ለመጠቀም ማሰባቸውን ተከትሎ ሊቨርፑሎች ለጆ ጎሜዝ የሚቀርብላቸውን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ የሚያደርጉ ይሆናል።
- • ዌስት ሃሞች የቀድሞውን የማንችስተር ዩናይትድ አጥቂ የኻቪየር ኸርናንዴዝ የውል ማፍረሻ የሆነውን 13 ሚ.ፓ በመክፈል ተጫዋቹን ለማስፈረም ሙከራ እያደረጉ ይገኛሉ።
- • ዌስት ሃሞች መረጋጋት ላይ የማይገኘውን የበርንሌይ አጥቂ አንድሬ ግሬይን በ15 ሚ.ፓ ለማዛወር እንቅስቃሴ ለማድረግ ተዘጋጅተዋል።
- • ኒውካሰሎች የቪላሪያሉን አጥቂ ሰድሪች ባካምቡን ለማስፈርም ቢፈልጉም ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ግን የዝውውር ክብረወሰናቸውን መስበር ይጠበቅባቸዋል።
- • ሞናኮዎች የማንችስተር ዩናይትድ ዒላማ ለሆነው ፋቢንሆ ከፒኤስጂ የቀረበላቸውን የ40 ሚ.ፓ የዝውውር ጥያቄ ውድቅ አደረጉ።
- • ዲያጎ ኮስታ ቼልሲ ከክለቡ ሊቀንሰው መዘጋጀቱን ተከትሎ በከፍተኛ የክብር ስሜት ወደአትሌቲኮ ማድሪድ ለመመለስ ራሱን አዘጋጅቷል።
- • የስዊንሲ ዒላማ የሆነው ሮኩ ሜሳ በ11 ሚ.ፓ ከላስ ፓልማስ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ወደእንግሊዝ ይበራል።
- • ኸደርስፊልዶች የቼልሲውን አማካኝ ካሲይ ፓልመርን ዳግም በውሰት ሊያስፈርሙ ሲሆን የኢዚ ብራውንንም ዝውውር እያጤኑበት ይገኛሉ።
- • የአርሰናሉ አማካኝ አሌክስ ኦክስሌድ-ቻምበርሌይን አዲስ የቀረበለትን ኮንትራት ውድቅ ያደረገ ሲሆን፣ ባልፈው አመት የፈረመውንና አሁን ከክለቡ ጋር ያለውን ኮንትራት ጠብቆ በሚቀጥለው ክረምት ኤመራትን ለመልቀቅ ፈልጓል።
- • አርሰን ቬንገር አሌክሲ ሳንቼዝ በዚህ ክረምት ማንችስተር ሲቲን እንደማይቀላቀል ነገረውታል።
- • ቼልሲ በሶስት ዓመት ጊዜያት ውስጥ ከ10 ጨዋታ በታች ከተስለፉ ተጫዋቾች ሽያጭ 100 ሚ.ፓ ማግኘት ችሏል።
- • አትሌቲኮ ማድሪዶች ዲያጎ ኮስታን ከቼልሲ ለማስፈረም የተዘጋጁ ቢሆንም በውሰት አሳልፈው ግን አይሰጡትም። ይህ ማለት ደግሞ የስፔኑ ክለብ ባለበት ተጫዋች የማስፈረም እገዳ ምክኒያት እስከጥር ወር ድረስ እግርኳስ የማይጫወት ይሆናል።
- • ዎልቭሶች በሊቨርፑልና ቼልሲ የሚፈለገውን የፖርቶውን ኮከብ ሩበን ነቨስን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀመሩ።
- • ጆን ቴሪ ለአስቶን ቪላ ለመፈረም ይፋዊ የሆነ ንግግር ጀመረ።
- • ኒውካሰል የማንችስተር ሲቲ እና እንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ የሆነው ጆ ሃርት ፈላጊ ሆኗል።
- • በርንሌዮች በኤቨርተን የተፈለገውን ማይክል ኪን ምትክ ይሆናቸው ዘንድ የሼፍልዱን ቶም ሊን እየማተሩ ነው።
- • ሆዜ ሞሪንሆ አልቫሮ ሞራታን ከሪያል ማድሪድ ቢያዛውሩም ባኤቨርተኑን አጥቂ ሮሜሉ ሉካኩ ላይ አሁንም ድረስ ፍላጎት አላቸው።
- • ዋይኒ ሩኒ የኮንትራት አማራጩን ከፍ በማድረግ በማንችስተር ዩናይትድ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ሊቆይ ይችላል።
- • ኤቨርተን በአስገራሚ ሁኔታ ለአርሰናሉ አጥቂ ኦሊቪየ ዥሩ 20 ሚ.ፓ የዝውውር ዋጋ ለማቅረብ ተዘጋጅቷል።
- • አርሰናል ለናፖሊው ኮከብ ጆርጊንሆ ያቀረቡት 15 ሚ.ፓ የዝውውር ዋጋ ውድቅ ተደረገበት።
- • የማንችስተር ሲቲው አለቃ ፔፕ ጋርዲዮላ እንግሊዛዊውን ግብ ጠባቂ፣ ጆ ሃርትን ወደተቀናቃኙ ዩናይትድ እንዲዛወር ፈቃደኛ ሆነ።
- • የአርሰናሉ ተከላካይ ሄክቶረ ቤለሪን በአውሮፓ ከ21 ዓመት በታች ፍፃሜ ላይ ሁለተኛ በመውጣታቸው ሜዳዩን ያደረገ ብቸኛ ተጫዋች በመሆኑ የማህበራዊ ሚዲያው መሳለቂያ ሆኗል።